TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2327 801
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


2004-2014 ድፍን አስር አመት በጟደኝነት


እሱ #ሙስሊም እኔ #ኦርቶዶክስ እሱ #የአርሰናል ደጋፊ እኔ #የማንችስተር_ዩናይትድ እሱ #ዝምተኛ እኔ #ቀውጢ እኔ #አሸናፊ ከሆንኩ በጣም አበሳጪ እሱ ደግሞ ለኔ #ስሜት የሚጨነቅ ብዙ ቅጣቶችን የሚያልፈኝ........ከአፋ ብዙ መጥፎ ነገርች የማይወጡት እኔ ደግሞ ሰው ከተናገረው አይደለም የተናገረው ከመሰልኝ አካኪ ዘራፍ የምል.....


ትውውቃችን ትምህርት ቤት ውስጥ ነው ኳስ ስንጫወት ተቃራኒ ሆነን ነው እሱ ተከላካይ እኔ አጥቂ ሁሌም ተቃራኒ ሆነን ነው ምንገባው ፍልሚያው የሌለ ይጦፋል እሱም አደገኛ ተከላካይ ነው እኔም ለማግባት ተደጋጋሚ ወደ ጎላቸው እደርሳለሁ ሁሌ እኔ ላይ ነው ፋዎል የሚሰራው እንደደመኛ ነው ምንተያየው........እንደዛ እያልን ጟደኛሞች ሆንን ሰው ጟደኛ ሲሆን ይተዛዘናል የኔና የሱ ግን ባሰ ጌም ውስጥ የምንሆነውን አይቶ ማንም መልሰው ያወራሉ አብረው ይሔዳሉ የሚል አልነበረም እኔ እና እሱ ግን ከጌም በኃላ እየተበሻሸቅን ምግብ ልንበላ አብረን እንሔዳለን ተሻምተን እንበላለን...........

በተለይ ደግሞ የማይቀረው #ዶናት ነው እየተመንታተፍን ነው የምንበላው..........

ማሜ የኔ ምርጥ ወንድም....🥰😍🥰


እኔ 7A..........እሱ 7B ክፍል ነበርን በትምህርትም እንፎካከራለን እኔ እዘርረዋለሁ እንጂ ሃሃሃሃሃሃ ውጤት ስንቀበል ሁሌ እንዳበሸኩት ነበር በጣም ነበር የምናጠናው ከትላንት የተሻለ ለመሆን ነበር ጥረታችን ለጨዋታ የምንሰጠው ጊዜ አለን ለትምህርታችን ደግሞ ትልቁን ጊዜ....ለዛም ነው ውጤታችን አመርቂ የነበረው እንደውም እንዳንዶች ይገርማቸው ነበር ክላስ ላይ ጠንካራ ስንሆን...
ትልቅ ህልም ነበረን....ልናሳካው የምንመኘው


ውይ እረስቼ ፕሌስቴሽን አልችለውም ነበር እንባዬን ነው የሚያመጣው ውውውው 3:0 4:0 ምናምን ነው የሚያሸንፈኝ የነበረው 😡😡😡


ቤተሰቦቻችን ይተዋወቃሉ እኛጋር ለበዓል ለማሜ ተብሎ ለብቻ ነው ምግብ የሚሰራለት በተለይ ለመስቀል በዓል ለዛ ለልጄ ላዘጋጅ ትላለች እናቴ😂😂 ለዛ ልጄ ብላ ለኛ የተሰራው ሁሉም ሳይቀር ለሱ ትሰራለች ሁሉንም ታስቀምጣለች ይኽው አንድ በዓል ሳይቀር ድፍን አስር እመት.........



ብጣም የምወደው ወንድሜ አድማጬ ወደመጥፎ ስሔድ በምክሩ የሚመልሰኝ መልካሙን የሚመኝልኝ ለህልሜ መሳካት ደፋ ቀና የሚልልኝ የኔ የሆኑትን የሚወድ ተቀናቃኜ አጥቼ ሊያየኝ የማይፈልግ እኔ የኔን አስቸጋሪ ፀባይ ችሎ እንደዚ መሆን አለበት እንዲ ቢሆን እንዲህ ነው እያለ እየመከረ ሲጨንቀኝ ተጨንቆ እኔን እያለ ክሩቅ እየመጣ ብቻ ስንቱን ስላንተ ማውራት ጉንጭ ማልፋት ነው.....::

ወንድሜ የኔ ሰው #መሐመድ_ዑመር


እንኳን ደስ አለህ እንኳን ለዚች ቀን አደረሰህ አንተ ከዚህም በላይ ነው የሚገባህ ያኔ ልጆች ሆነን ያለምነውን አሳክተነዋል ሁሌም እልህ የለ ጥሩ ሰዎች መልካም ነገር ይገባቸዋል ፈጣሪ ከነሱ ጋር ስለሆነ ያሰቡትን ያሳኩታል እልህ አልነበር እንኳን ደስ አለህ #ማሻ_አላህ


😍🥰🥰🥰😍😍🙏🙏🙏💪🏿💪🏿💪🏿😘😘
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →