ከትላንት ወዲያ ዳግማዊት ክፍሌን(ዳጊ ሾው) instagram ላይ live አውርቻት ነበር::
ከዛ ነትላንት አቤል ሲኒማ በተዘጋጀው የዳዊት ድሪምስ የማነቃቂያ ዝግጅት ላይ እሷ ተጋባዥ እንደሆነችና እዛ ብመጣ እንደምንገናኝ ነግራኝ እንደምመጣና ስጦታም እንድምሰጣት ነግሪያት በደስታ ተቀብላ እዛው እንገናኝ ተባብለን ተሰነባበትን::
እናም በቃሌ መሰረት ቦታው ድረስ ሔጄ የዳጊን አስገራሚ ታሪክ ሰምቼ ብዙ ነገር ተምሬ ስጦታዬን ሰጥቻለሁ በጣም ደስ ብሏት ነበር በጣም አሪፍ ጊዜ ነበር::
ይሔን ፎቶ ያነሳሁት ላንጋኖ ነው እዛ የሔዳችሁ ይህን ዘንባባ ላለመውደቅ ከማዕበሉ ጋር ምን ያህል ትንቅንቅ እንደሚያደርግ ሳታስተውሉ አትቀሩም እናም እንደ ዳጊ አይነት ደግሞ የህይወት ማዕበል በብርቱ ሲፈትናቸው ሳይወድቁ እዚ ደርሰዋል እናም ይህ ፎቶ እንደዳጊ አይነት ሴት እህቶቻችንን ይገልፃል ብዬ አሰብኩና ስጦታ ልሰጥ ወድድኩ::
ሴት ልጅ እንደዚ ጠንካራ ሆና ማየት ምንኛ ደስ ይላል.🥰🙏😍 ትልቅ ፍቅርና አክብሮት ዳጊ🙏🥰😍
እንደእግዚአብሔር ፈቃድ ደግሞ አንድ ቀን እንግዳሽ እንደምታደርጊኝ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ::
Post #2310
726




