AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
#ዛሬም_መበደል
ቀራኒዮን ስንመለከት በዓለም ላይ ክፉ የሆኑ ሁለት ሽፍቶችና የመጨረሻደግ ክርስቶስን እናገኛለን፡፡
ይቺ ምድር እነዚህን ወገኖች በፍርድ አስወግዳለች፡፡ እጅግ ደግና እጅግ ክፉ ለሆኑት ቦታ የላትም ፡፡ በዚህ አለም ላይ ስፍራ ያላቸው መካከለኞቹ ወይም ተጣጣፊዎቹ ናቸው፡፡ በጌታችን ቀኘና ግራ የተሰቀሉት ወንበዴዎች ጌታን ይሰድቡት ነበር፡፡
#ቅጣት_ሰውን_የተሻለ_አያደርገውም፡፡
እነዚህ ሰዎች ወደ ሞት እየሔዱ እንኳን ገና ይበድላሉ፡፡
ከሁለቱ ወንበዴዎች የቀኙ ወንበዴ( ፌያታዊ ዘየማን) በኀላ ተመልሷል፡፡ የተመለሰው ተዓምራት አይቶ አይደለም፡፡ ተዓምራት የተከናወነው ቆይቶ ነው፡፡
እርሱ ግን ያመነው ገዳዮች ባላሸነፉት በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ነው፡፡
ጌታችን:- "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ባለው ጊዜ ወንበዴው ተረታ ፡፡ የጌታ ፍቅር እንደአለት የጠነከረውን የወንበዴውን ልብ አቀለጠው፡፡ ገዳዮቹን ይቅር ያለ እኔንም ይቀበለኛል ብሎ አመነ፡፡
ተዓምራት ያዩ የጌታ ተከታይ መሆን አይችሉም ሰይጣን የበለጠ ተዓምራት ሲያሳያቸው እርሱን ይከተላሉ፡፡ ፍቅር ግን በእግዚአብሔር ቤት ይተክላል፡፡
በስተግራ በኩል የተሰቀለው ወንበዴ ግን እስከ መጨረሻው ልቡ ፀና፡፡ ጌታንም መውደድ አቃተው፡፡ በዚህም ምክንያት ከሕይወት ራሱን አገለለ፡፡ ሁለቱ ወንበዴዎች በዘመናት ሁሉ በአንድ ሀሳብ ተስማምተዋል፡፡ #እንግደል በሚል በሚል እቅድ እንኳን ተጣልተው አያውቁም፡፡ አሁን ግን በክርስቶስ ተለያዩ፡፡ በአንድ መንገድ የመጡ ቀራኒዮ ላይ ሲደርሱ በመንታ መንገድ ይሔዳለሁ፡፡
#ክርስቶስ_ልዩነት_ነው፡፡
ወንጀለኘነታችንን የወደዱልን አሁን ግን ታሪክ ለዋጩን ጌታ መውደድ ያቅታቸዋል፡፡
በቀኙ ወንበዴና በግራው ወንበዴ መካከል ያለው ልዩነት ኃጢያተኛ አለመሆን አይደለም፡፡ ምህረት ማግኘትና አለማግኘት ነው፡፡ በእኛ እና በዓለም ባሉት መካከል ያለው ልዩነትም ኃጢያተኛ አለመሆን አይደለም፡፡
እኛ #ምህረት_ያገኘን_ሀጢያተኞች_በመሆናችን_ብቻ_ነው፡፡
በግራ በኩል የተሰቀለው ወንበዴ:- "አንተ ክርስቶስ አይደለህምን?? እራስህንም እኛንም አድን" ብሎ ሰደበው፡፡ የክርስቶስን ጌትነቱን ካደ፡፡ የቀኙ ግን:- "ጌታ ሆይ" አለው ፍርድ የተዛባበትን ጌታሆይ ማለት እርቃኑን አብሮት ከተሰቀለው መንግስትን መለመን ትልቅ እምነትን ይጠይቃል፡፡ የቀኙ ወንበዴ በህይወት ዘመኑ ዛሬ ጓደኛውን ተቃወመው ፍቅርና ፍርድ በማይበግረው ማንነት ተደነቀ፡፡ ከዚህ በኀላ የቀረው የሰዓታት ዕድሜ ነው፡፡ እስከመጨረሻው ለግፍ ታማኘ በመሆኑ አሳዘነው፡፡
ሁሉም ነገር ገደብ ያስፈለገዋል፡፡
ሽፍታነትም ደንዳናነትም ክፋትም ምቀኘነትም ልክ ያስፈልገዋል፡፡ ያ ወንበዴ ግን ሀጢያትን ያለ ጡረታ እያገለገለ ነው፡፡
በእውነት ዛሬ ወደ ሞት እየሔዱ ቤተሰቦቻቸው በስንት ጭንቅ ውስጥ እያለፈ አሁንም እግዚአብሔርን የማይፈሩ አሁንም ለክፋታቸው ልክ ያጡ ስንቶች ይሆኑ?? አጠገባችኝ ስንቱ በሞት እየተንሸራተተ ስንቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ዘመኑ እየተቀጨ አሁንም ጌታን የማንፈራ ስንቶች ነን?? እነዚያ በሞኘነት የሞቱ እኛ ግን በብልጠት የቀረን የሚመስለን አያሌ ነን፡፡
ጌታ ሆይ እባክህ እንደቀኙ ወንበዴ በቀረን ዘመን አንተን ማመንና መታዘዝ ይሁንልን፡፡
አለም ለምኔ በሚያሰኘው ዘመን ገና ጭቃ እያላቆጥን ነውና እባክህን ይቅር በለን፡፡
ቅጣት የተሻለ ሰው አያደደርገንም፡፡በፍቅርህ መልሰን፡፡
የመፅሐፉን ርዕስ የፈለገ በውስጥ መስመር ያናግረኘ፡፡
@jahABP ነኘ ዛሬም ከመበደል እርሱ በቸርነቱ ይጠብቀን፡፡
መልካም ቀን ተመኘሁ፡፡😍😊😊🙏🙏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2315
642