TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #1798 · Back to latest

Older Posts 20 shown
Post #1797 861
ጥቆማ🗣🗣🗣

በፍቅር በመስጠት በመረዳዳት በመተባበር እንኑር😍🙏😍

ሰላም ለሀገራችን

@jahABP ነኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1793 974
🤲🤲🤲🤲➊
ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና
ብርታት ሆኖልኛል የስምሽም ምስጋና
እኖራለሁ ገና ንዒ ንዒ ስልሽ
ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፌ ማንለጥልሽ

❤️💓 😍😍😍🙏🙏🙏🙏
Post #1792 1.03K
30,000 ብር ቢሰጣችሁ ምን ታደርጋላችሁ🤔🤔🤔

ከእህቷ ጋር በሚለው ይስተካከልልኘ🙏


ይኸው እኔ ብሩን እንዲህ ከፋፈልኩት እናንተስ???

@jahABP ነኘ😍🙏🙏😊
Post #1791 1.16K
እስኪ ሌሎቹንም ስራዎቹን እዩለት @KirArts ቻናሉን join በሉለት
@portraitworld

ቲክቶክ ላይም ፎሎው በሉት @kirartsO

ማሳሰቢያ፡- አብይ ከዚህ ማስታወቂያ ምንም አይነት ክፍያ አልተቀበለም በመልካምነት ብቻ ነው፡፡

እባክህ በርታ ወንድሜ👏👏👌👌👌💪💪💪
Post #1790 928
👏👏👏👏👏👏👏
Post #1788 1.37K
AB PHOTOGRAPHY
ሸምቼዋለሁ
ከኤሉ የህይወት ባህር ያልሰማኀቸውን ታሪኮች ለማወቅ ጓጉቻለሁ😍

ጠብቁኘማ ወደናንተ አደርሳለሁ

ኤሉ የኛ የኛ

"እግዚአብሔርን ባገኘው ሙዚቃን እስከ መጨረሻ የማወቅ ስልጣን እንዲሰጠኘ እጠይቀው ነበር"

የከተማው መናኘ 😔😔😔😢😢😢😢😢
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1787 1.06K
"የባለቤትነት መብታችንን ካላስጠበቅን ኢትዮጵያ ተጎጂ ትሆናለች"
ዶ/ር መላኩ ወረደ ሳይንቲስት

በ1989 እ.ኤ.አ አለም አቀፍ "Alternative Noble Prize" ተሸላሚ🥇

ይደመጥ 👂👂
Post #1785 1.18K
ወንድሜ ያበደ ኮስሞቲክስ ቤት ከፍቷል ያበደ

ኦርጅናል ዕቃዎችን ብቻ የያዘ፡፡

እና እኔም ይህን በማስመልከት ሱቁን ልመርቅለት አሰብኩና እየተወሰኑ እቃዎችን ገዛሁኘ፡፡

ከዛ እሱ ለምን የቻናልህን ተከታዮች የሆነ ጥያቄ ጠይቀህ ብቻ እንደፈለክ አድርገህ ለምን አልሸልምልህም አለኘ ኧረ ትከስራለህ ገና መጀመርህ ነው ስለው የለም የለም ሞቼ እገኛለሁ አለኘ....እኔም እሺ በደስታ ወንድሜ አልኩት😍😍🙏🙏🙏😘😘


ዝግጁ ናችሁ🤔🤔

ለሴቶች........ውዱን vectoria ቻፕስቲክ💄💋💋👄


ለወንዶች.......እብድ ያለ ሽቶ🗼


ዝግጁ ናችሁ???

በኔ የብቃት ደረጃ የተነሱ ፎቶዎች በቅብ ቀን😊😊📸📷
Post #1780 1.07K
ክብራችን መዳኛችን እናታችን ተወለደችልን

ድንግል ሆዮ ልደትሽ ልደታችን ነው
ያንቺ መሆን ምንኛ መቻደል ነው

እንኳን አደረሳችሁ
Post #1776 1.19K
.....ስምዖን ጴጥሮስና ዮሐንስ መግደላዊት ማርያም ያመጣችውን የመሰረቁን ዜና ገና ሲሰሙ የአፏን ቃል ሳትጨርስጠወደ መቃብሩ ስፍራ ገሰገሱ፡፡
የኢየሱስ ስጋ አለመኖሩን ተረዱ መግደላዊት ማርያም የነገረቻቸውን አመኑ ፡፡ ልብ በሉ ያመኑት ግን ትንሳኤውን ሳይሆን ቅዱስ ስጋው በክፉ ሰዎች በጠላት መሰረቁን ያመኑተ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ሳይሆን በጠላቶቹ የክፋት ሀይል ነው፡፡ አለመኖሩን ካረጋገጡ በኀላ ወደቤት ተመለሱ፡፡

ከነገረቻቸው በኀላ በሦስተኘነተ የደረሰችው የመጨረሻዋ ሯጭ መግደላዊት ማርያም ግን ከእነርሱ ኀላ ብትደርስም ኢየሱስ ክርስቶስን ካላገኘሁ አልነቀሳቀስም ብላ በመቃብሩ ስፍራ ፍለጋዋን ቀጠለች.....በዮሐንስ ውጌል እንደምናነበው ኢየሱስን ያገኘችው ይቺው ሴት ናት፡፡ አንደኛ የመጣውም ሁለተኛ የደረሰውም አላገኙትም፡፡ የመጨረሻዋ ሯጭና ቆራጧ ሴት ግን ክርስቶስን አገኘችው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘውአንደኛ ለወጡት ሳይሆን ለሚፈልጉትና ቆርጠው ለወጡት ነው፡፡
መግደላዊት ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስን በብርቱ ትፈልገው ነበር፡፡ እርሱን ካላገኘች ወደቤቷ ለመግባት ጠልታ ዱር ቤቴ ብላ ትባዝናለች የምትፈልገው ጌታዬ እያለች እየመሰከረችለት የዕንባ ፈሳሽ እያፈሰሰች ነበር፡፡ መላዕክት ቢገለፁላትም እርሱን ግነ አልተኩላትም እርሱን እስክታገኘ ዕረፍት አልነበራትም፡፡

አንዳንዶች ክርስቶስን አውቀው ፍቅር ይግዛኘ ህለውናህ ይሰማኘ እያሉ በእንባ ይሹታል ለዘላለም ህይወት ይፈልጉታል፡፡
አንዳንዶች ስለ አስቤዛ ስለኑሮ መሟላት ብቻ ክርስቶስን የሚፈልጉት ናቸው፡፡

እኛስ ከየትኞቹ ፈላጊዎች እንመደብ ይሆን??

እሷ ክርስቶስን የፈለገችው በብርቱ ነው፡፡ የእርሱ የቅርብ ደቀመዛሙርት እነኳን ፍላጎታቸውን አቋርጠው ወደ ቤታቸው ቢመለሱም እርሷ ግን ተስፋ ቆርጣ አልተመለሰችም፡፡ በልቧ እንደ ጴጥሮስና ዮሐንስ እኔ ለእርሱ ቅርብ አይደለሁም እቤቴ ቁጭ ብዬ የሆነውን እሰማለሁ አላለችም፡፡ ከአምስት ገበያ ከሚያህል ህዝብ አንደ ፈላጊ ያጣውን ጌታ ብቻዋን መፈለግ ጀመረች፡፡

እርሱን በእውነት የሚፈልጉ የዘመናት ፈተናቸው ብኘነት ነው፡፡ ትልልቅ የሚባሉ ሰዎችም ብዙ የተማሩ መንፈሳውያን መሪዎች በሌሉበት እርሱን መፈለግ ማስተዋል ነው፡፡

መግደላዊት ማርያም የምታለቅስበት ምክንያቱ ጸጋን አጣሁ የሚል አልነበረም #ባለፀጋውን አጣሁት የሚል ነበር፡፡

ጌታ ኢየሱስ ከዚህ በላይ ተሰውሮ መቆየት አልሆነለትም፡፡ እርሱጠበእውነት ለሚሹ የቅርብ አምላክ ነውና፡፡ እርሷ፡አታየውም እርሱ ግን ያያታሌ አልተሰረቀም ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ እንጂ እርሱ ከመቃብር ስፍራ አይፈለግም ከመሬት በታች የለም ከሰማያት በላይ ገኗል፡፡
ኢየሩሳላም የገፋችው ዝናው በአለም ሁሉ ወጥቷል፡፡

የፍቅር ጌታ የማርያምን ሰቀቀን ችሎ መቆየት አልሆነለትም፡፡ በሀይሉ ጉልበት ሁሉ ሲረታ በፍቅር ግን ይሸነፋል ስለዚህ ተገለፀላት፡፡ ይህንም ብላ ዘወር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው ኢየሱስ እንደሆነ ግን አላወቀችም፡፡
ኢየሱስም:- "አንቺ ሴት ለምን ታለቅሻለሽ ማንንስ ትፈልጊያለሽ አላት"፡፡ የመላዕክቱን ጥያቄ ደገመላት አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ ማንን ፈልገሽ ታለቅሻለሽ አላት "ማን" ለሕያው የሚጠቀስ ነው፡፡ "ምን" ለቁሳቁስ ፍላጎት የሚጠቀስ ነው፡፡ እኛን ቢሆን "ምን" ፈልጋችሁ ታለቅሳላችሁ?" ይለን ነበር፡፡

መግደላዊት ማርያምም ግን አላወቀችውም፡፡ "እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት ጌታ ሆይ ንተ ወስደኸው እንደሆነ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኘ እኔም እወስደዋለሁ አለችው"

#እኔም_እወስደዋለሁ ለመሆኑ ትችለዋለች?? ወስዳ የት ታደርገዋለች ፍቅር ከመቻል ያልፋልበዚ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን መሰወር አልቻለም "ማርያም" አላት እርሷም በአካል ቢገለጥ ፣ጠይቃት አላወቀችውም፡፡ በስሟ ሲጠራት ግን አወቀችው የእርሹ አጠራር ከሌሎች አጠራር የተለየ ነው ቅላፄው የድምፁ ቃና የቃላቱ ፍሰት ዘላለማዊ ፍቅር የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ቃና ሲጠራት ነፍሷ ተላወሰ ልቧ ተቃጠለች፡፡

እነዚያ የሚፈጥሩት ቃላትሀዘኗ እንደ ጉም ሲበትኑት በቅፅበት ተሰማት፡፡ ከሦስት ቀን በፊት የምታውቀው ያ ድምፅ ነው፡፡ ይህ ድምፅማ ያኖረኘ ዕድሜ የቀጠለልኘ የመኖር ፍላጎቴ የጨመረልኘ ለራሴ ዋጋ እንድሰጠው ያደረገኘ ነው፡፡ በፍፁም ፍቅር እንዲህ ብሎ የሚጠራኘ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም የለም ብላ

#ረቡኒ አለችው፡፡ በሕብራይስጡ #መምህር ሆይ ማለት ነው፡፡

ለደቀመዛሙርቱና ለመላዕክቱ "ጌታዬ" ብላ ገልፃዋል፡፡ ራሱን ግን መህህሬ አለችው፡፡ በእርግጥም እርሱ ጌታም መምህርም ነው፡፡
ከአለም ላይ ከሚገኙ ጌቶች እርሱን ልዩ የሚያደርገው በፍቅር በርህራሔ የሚገዛ ጌታ መሆኑ ነው፡፡ መምህርነቱም ከመምህራን የተለየ ነው፡፡

መግደላዊት ማርያም #ሩቡኒ ስትለው አውቀዋለሁ የምለው እውቀቴ ዕድሜ ያስገነዘበኘ ነገር ሁሉ ያለወጠኘ አንተ ግን እራሱን ከሚያስፈፅም ቃልህ ጋር ወደእኔ የመጣህ የለወጥከኘ መምህሬ ነህ ማለቷ ነው፡፡ የሕይወትህን ሆሄ የቆጠርኩብህ ኑሮና አገርን ከሰው ጋር መግባባት ያስለመድከኘ ብርሃኔ ነህ፡ማለቷ ነው፡፡መሳሳቴ የማይቀበለውም ግትር ማንነቴ በትዕግስት በፍቅር ቃላትየመለስክልኘ ወድቃ ትማር ብለህ ያልተውከኘ በቀና ኞዳና የምትመራኘ የፍፃሜዬ አምላክ፡አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡

ለኛ ሲል የሞተውን ክርስቶስን እንደዚች ሴት ለመፈለግ ፍቅራችን ምን ያህል የፀና ይሆን??
እሷ ሞቶ ፈለገችው እኛስ ትንሳኤውን ያመንን በጥቂቱ እንኳን ፈልገነው ይሆን??😔😔😔😔

#መግደላዊት_ማርያም_አስደናቂዋ_ሴት

የዲ/ን አሸናፊ መኮንን
#ረቡኒ
ከሚለው ትንሽዬ መፅሐፍ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንዲህ አቀረብኩት፡፡
ሙሉ መፅሐፉን ታነቡት ዘንድ ግብዣዬ ነው
@jahABP ነኘ
መልካም በዓል
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1775 998
#መግደላዊት_ማርያም

መግደላዊት ማርያም መጌዶን በሚባለው የትውልድ አገሯ መግደላዊው ማርያም ተብላለች፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማርያሞች ስላሉ መግደላዊት ማርያም ተብላ ተለይታ ተጠቅሳለች፡፡ በውስጧም ታላቅ የፍቅር ትንታግ የሚቀጣጠልባት፡፡

መግደላዊት ማርያም እስከዚ ቀን ድረስ እንዴት ታግሳ ተቀመጠች? ስንል ጌታችን የተሰቀለው ዓርብ ማታ ነው፡፡ ቅዳሜ እንዳትመጣ የአይሁድ ሰንበት ነው፡፡ በሰንበት ከዠወሰኑ ኪ.ሜ በላይ መጓዝ ስለማይቻል በሕግ ገደብ ተይዛ በጭንቀት ሳትውል አልቀረችም፡፡ ሰንበት ካለፈ በኀላ ግን እሁድ ለሊት ነጋ አልነጋ እያለች ስትጠባበቅ ገና ጨለማ ሳለ ወደመቃብሩ ስፍራ ገሰገሰች፡፡

አይሁዳዊያን የሞተ ወዳጃቸውን በሦስተኛው ቀን መቃብሩ ላይ ሽቱ በማርከፍከፍ ለመጨረሻ ጊዜ ይሰናበቱታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በሕያውነቱ ሽቱን ተቀበለ እንጂ የሙታን መሰናበቻ የሆነውንሽቱ አልተቀበለም፡፡ እርሱ ሕያው ነውና፡፡ መግደላዊት ማርያም የመጨረሻ ሀዘኗን ለመግለፅ ሽቱ ለመቀባት ገና ሳይነጋ ወደ መቃብር ስፍራ ገሰገሰች፡፡

ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር ገሰገሰች ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደክርስቶስ መገስገስ ለብዙዎች ጣር ነው፡፡

ጨለማው እንዳለ ይሁን እኔ ግን ጌታዬን እፈልጋለሁ ጌታዬ ያስፈልገኛል፡፡ ከጨለማው በላይ ያለ እርሱ መኖር ይከብደኛል የሚሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ጨለማ ከተወገደ በኀላ እንጂ ጨለማው እያለ ሊያመልኩት የተሰናዱ ከጉዳያቸው ይልቅ የተሰቀለው ጌታ ራሱ ጉዳይ የሆነላቸው ጥቂትች ናቸው፡፡

ብዙዎች በማለዳ ወደ ጌታ መምጣት አይፈልጉም፡፡ ዕድሜያቸውን ከከሰሩ በኀላ የዕድሜያቸውን እንጥፍጣፊ በእግዚአብሔር ቤት ለማሳለፍ የሚያስቡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ብዙ ሞክረው ሲደክማቸው እንጂ ገና በጠዋቱ ለእርዳታ ወደ እርሱ የሚመጡ ጥቂቶች ናቸው፡፡

ክርስቶስ ለብዙዎቹ አማራጫቸው እንጂ ምርጫቸው አይደለም ስለዚህ በክብሩ አያዩትም፡፡

መግደላዊት ማርያም ወደ ክርስቶስ ስትገሰግስ ሴትነቷን የሚፈታተኑ ብዙነገሮች ነበሩባት፡፡ ጨለማው የመቃብሩ ስፍራ ትልቁ ቋጥኘ ስጋቶቿ ነበሩ፡፡ ሴት ልጅ ጨለማን ትፈራለች፡፡ እንኳን በጨለማ ብርሃን እንኳን አጥቂ አለባት፡፡ የመቃብርስፍራም እንኳን በጨለማ በቀንም የማይደፈርነው፡፡

ጌታን የከደነው ቋጥኘም በእርሷ ጉልበትም የሚገፋ አይደለም፡፡ የማትችለው ነገር ከፊት ለፊቷ ቢታያትም ፍቅር ግን ፍርሃትን አውጥቶ ጥሎላት ወደ ፊት ገሰገሰች፡፡

ዮሐንስ፡- "ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች"(ዮሐ. 20-1) በማለት ፅፎልናል፡፡ በመንገድ ሳለች ድንጋዩ የተፈነቀለው ጌታ እንዲነሳ አይደለም፡፡ መቃብሩ ባዶ መሆኑን ለማሳየት መሎዓኩ ፈንቅሎታል፡፡

ጌታ ግን መግነዝ ፍቱልኘ መቃብር ክፈቱልኘ ሳይል ተነስቷል፡፡ወንጌላዊው ማርቆስ እርስ በእርሳቸውም :- ደንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፡፡


መግደላዊት ማርያምበእርሷ እና በእርስቶስ መካከል ጋሬጣ የሆነውን ትልቅ ቋጥኘ በመንገዷ ሁሉ ያሳስባት ነበር፡፡
ዛሬም ጌታችንን እንዳናገኘ ብዙ ቋጥኞች አስጨንቀውን ይሆናል፡፡ መግደላዊት ማርያም ግን ቋጥኙን ባትችለውም አለመቻሏ ጉዞውን አላደናቀፈውም፡፡

ጥያቄና ስጋት የሆነባት ነገር ሕያው ቢሆንም ወደኀላ አልተመለሰችም፡፡ ውጤቱ ግን ሕያው የሆነው ቋጥኙ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር፡፡
ድንጋዩ ተፈንቅሎ አየች፡፡

ዛሬም ክርስቶስን ለማየት የሚከለክሉን ብዙ ቋጥኞች አሉ፡፡ ከክርስቶስ በላይ መከበር የሚፈልጉ የስመ ቁልል እንደ እንደ ተራራ የተጫናቸው ሰው ሳይሆኑ መልዐክ ተብሎ እንዲነገርላቸው የሚሹ ትልልቅ ቋጥኞች ዛሬም አሉ፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈልግ ትውልድ በስጋቶች አይቆምምናወደ ክርስቶስ መገስገስ ያስፈልጋል፡፡ ያን ጊዜቋጥኙ ተንከባሎ የተነሳውን ጌታ የምስራች እንሰማለን፡፡

ዛሬስ ክርስቶስንእንዳናይ ጋሬጣ የሆነብን ምንድነው?? ኀጢያትና ሱስ ይሆን? በእምነት እንጓዝ ቋጥኙ ይንከባለላል፡፡ ክርስቶስን ለምትፈልግ ነፍስ ትልቅ ሆኖ የሚያስፈራት ችግር የለም፡፡ ከትልቅ ችግራችን ይል ክርስቶስ ለኛ ትልቅ ነው፡፡

የምንፈልጋቸው እንዲሆኑልን የምንመኛቸው ብዙ መልካም ነገሮች ቢኖሩም ድንጋዩን ማን ያንከባልልናል የሚል ስጋት ግነ አለብን፡፡ ራዕያችን ትዳራችን ወዳጅነታችንጨየራሱ የሆነ የፈተና ቋጥኘ አለው፡፡ የማይቀር ሆኖብን ብንጀምረው እንኳን ልባችን ግነ ይፈራል፡፡

በእምነት ብንጓዝ ግን ድንጋዩ ተፈንቅሎ እናይ ነበር፡፡ የእስራኤል ልጆች ባህር የተከፈለላቸው በመጓዛቸው ነው፡፡ እግዚአብሔር ወደፊት ለሚሉት ባህር መክፈል ቋጥኘ ማንከባለል ልማዱ ነው፡፡

#ህይወት_በኛ_መቻል_ላይ_የተመሰረተች_አይደለችም፡፡
እኛ ምንም የማንችል ደካሞች ነን፡፡
ሕይወት ሂደት ብቻ ሳይሆን ተአምራዊ ድልም የሚያስፈልጋት ናት፡፡ እግዚአብሔር ወደፊት በእምነት ለሚገሰግሱ ባህር የመክፈል ድንጋይ የማንከባለል ኃይሉን ያሳያቸዋል፡፡

እየጓዝን ነው ወይስ ፍርሃታችን ከቃሉ ይልቅ ከምነን ቆመናል??

መግደላዊት ማርያም ሞቶም ትፈልገዋለች፡፡
የፈለገችው ገዳይ ነን ብለው የፎከሩትን ሳይሆን ስለፍቅር የሞተውን ኢየሱስ ክርስቶስነ ነው፡፡
ሞቱን እንደ መረታት አልቆጠረችውም፡፡
#ስለ_ፍቅር_የሚሞት_እሱከ_ገዳዮች_ይልቅ_እርሱ_ጀግና_ነውና፡፡

ሞቱ እንድትረሳው አላደረጋትም ፍቅሯን እንድትገልፅ ውለታው አስገደዳት የእርሷ ፍቅር ከጊዜ ጋር አልተለወጠም ከራሷ ይለቅ ስለ ክርስቶስ ፍቅር አሰበች፡፡
ፍፁም ፍቅር ራስን በመርሳት ስለክርስቶስ ማሰብ መሆኑን አሳየች፡፡



ለማንም ሰው መቃብር ቋጥኘ አይገጠምም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ግነ ቋጥኘ ተደርጎበታል፡፡ አለም ገድላም የፈራችው ቢኖር ኢየሹስ ክርስቶስን ነው፡፡ አስቸጋሪ የተባሉ ሰዎች ሁሉ ከሞቱ በኀላ አስጊነታቸው ያበቃል፡፡ ክርስቶስ ግን ሞቶም ያስፈራል፡፡

ሞቶም ፈለገችው የፈለገችው ተአምር ተአምር እንዲያደርግላት ከደዌ እንዲፈውሳት አበርክቶ እንዲመግባል አልነበረም፡፡ ስለራሱ ስለጌታ ስለፍቅሩ ስለፍቅሩ ስለ ማንነቱ ፈለገችው፡፡ የምታመልከው እርሱን እንጂ ጥቅሟን አልነበረም፡፡ ከጉድለት በላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ማጣት ትልቅ ጉዳት ሆኖ ተሰማት፡፡

የክርስቶስ የሆነውን መውደድና ራሱ ክርስቶስን መውደድ የተለያየ እንደሆነ ይችህ ሴት፡ትመሰክራለች፡፡ የዚች ሴት ፍቅርጨፍቅራችንን ይታዘበዋል፡፡ ሁላችንመ አምላካችን ገዳይ እንጂ ሟች እንዲሆንልን አንፈልግም፡፡ ጠላቶቻችንን የሚበቀል በተነሱብን ላይ ፈጥኖ የሚፈርድ እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ እኛስ አስከብሮ ራሱን ተፈሪ የሚያደርግ አምላክ እንሻለን፡፡

መግደላዊት ማርያም ሞቶም ጌታዬ ትለዋለች ሞቶ እንኳን ጌታዋ እንደሆነ አምናለች፡፡ በጣም የምናከብራቸው ሰዎች ተይዘው ሲታሰሩ በፍርድ ሲገደሉ በቀድሞ አጠራራቸው ሳይሆን በተለየ የንቀት አጠራር እንጠራቸዋለን፡፡ ማንም የምናከብረው ይዞ ሲገኘ ብቻ ነው፡፡ የተሸነፈን በቀድሞ ክብሱ አናከብረውም፡፡ ለጊዜው የተሸፈነ የሚመስለውን ይነሳል ብላ ያላመነችው ጌታዬ ማለቷ ይደንቃል፡፡

እኛ ትነሳዬውን የመንን ከእርሷ ይልቅ ጌታዬ ልንለው ይገባናል፡፡ ለእርሱ ያለን ፍቅርና አክብሮትም መቀጣጠልና መንደድ ይገባዋል፡፡
አሁንም ጌታዋ ነው አላፈረችበትም ሞቱ ለእርሱ ያላትን ክብር አልቀነሰባትም፡፡ ብዙዎችን ያሰናከለ ሞቱ አላሰናከላትም፡፡
ሞቶም በፍቅሩ የገዛት ክርስቶስ ነው፡፡
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →