#መግደላዊት_ማርያም
መግደላዊት ማርያም መጌዶን በሚባለው የትውልድ አገሯ መግደላዊው ማርያም ተብላለች፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማርያሞች ስላሉ መግደላዊት ማርያም ተብላ ተለይታ ተጠቅሳለች፡፡ በውስጧም ታላቅ የፍቅር ትንታግ የሚቀጣጠልባት፡፡
መግደላዊት ማርያም እስከዚ ቀን ድረስ እንዴት ታግሳ ተቀመጠች? ስንል ጌታችን የተሰቀለው ዓርብ ማታ ነው፡፡ ቅዳሜ እንዳትመጣ የአይሁድ ሰንበት ነው፡፡ በሰንበት ከዠወሰኑ ኪ.ሜ በላይ መጓዝ ስለማይቻል በሕግ ገደብ ተይዛ በጭንቀት ሳትውል አልቀረችም፡፡ ሰንበት ካለፈ በኀላ ግን እሁድ ለሊት ነጋ አልነጋ እያለች ስትጠባበቅ ገና ጨለማ ሳለ ወደመቃብሩ ስፍራ ገሰገሰች፡፡
አይሁዳዊያን የሞተ ወዳጃቸውን በሦስተኛው ቀን መቃብሩ ላይ ሽቱ በማርከፍከፍ ለመጨረሻ ጊዜ ይሰናበቱታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በሕያውነቱ ሽቱን ተቀበለ እንጂ የሙታን መሰናበቻ የሆነውንሽቱ አልተቀበለም፡፡ እርሱ ሕያው ነውና፡፡ መግደላዊት ማርያም የመጨረሻ ሀዘኗን ለመግለፅ ሽቱ ለመቀባት ገና ሳይነጋ ወደ መቃብር ስፍራ ገሰገሰች፡፡
ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር ገሰገሰች ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደክርስቶስ መገስገስ ለብዙዎች ጣር ነው፡፡
ጨለማው እንዳለ ይሁን እኔ ግን ጌታዬን እፈልጋለሁ ጌታዬ ያስፈልገኛል፡፡ ከጨለማው በላይ ያለ እርሱ መኖር ይከብደኛል የሚሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ጨለማ ከተወገደ በኀላ እንጂ ጨለማው እያለ ሊያመልኩት የተሰናዱ ከጉዳያቸው ይልቅ የተሰቀለው ጌታ ራሱ ጉዳይ የሆነላቸው ጥቂትች ናቸው፡፡
ብዙዎች በማለዳ ወደ ጌታ መምጣት አይፈልጉም፡፡ ዕድሜያቸውን ከከሰሩ በኀላ የዕድሜያቸውን እንጥፍጣፊ በእግዚአብሔር ቤት ለማሳለፍ የሚያስቡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ብዙ ሞክረው ሲደክማቸው እንጂ ገና በጠዋቱ ለእርዳታ ወደ እርሱ የሚመጡ ጥቂቶች ናቸው፡፡
ክርስቶስ ለብዙዎቹ አማራጫቸው እንጂ ምርጫቸው አይደለም ስለዚህ በክብሩ አያዩትም፡፡
መግደላዊት ማርያም ወደ ክርስቶስ ስትገሰግስ ሴትነቷን የሚፈታተኑ ብዙነገሮች ነበሩባት፡፡ ጨለማው የመቃብሩ ስፍራ ትልቁ ቋጥኘ ስጋቶቿ ነበሩ፡፡ ሴት ልጅ ጨለማን ትፈራለች፡፡ እንኳን በጨለማ ብርሃን እንኳን አጥቂ አለባት፡፡ የመቃብርስፍራም እንኳን በጨለማ በቀንም የማይደፈርነው፡፡
ጌታን የከደነው ቋጥኘም በእርሷ ጉልበትም የሚገፋ አይደለም፡፡ የማትችለው ነገር ከፊት ለፊቷ ቢታያትም ፍቅር ግን ፍርሃትን አውጥቶ ጥሎላት ወደ ፊት ገሰገሰች፡፡
ዮሐንስ፡- "ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች"(ዮሐ. 20-1) በማለት ፅፎልናል፡፡ በመንገድ ሳለች ድንጋዩ የተፈነቀለው ጌታ እንዲነሳ አይደለም፡፡ መቃብሩ ባዶ መሆኑን ለማሳየት መሎዓኩ ፈንቅሎታል፡፡
ጌታ ግን መግነዝ ፍቱልኘ መቃብር ክፈቱልኘ ሳይል ተነስቷል፡፡ወንጌላዊው ማርቆስ እርስ በእርሳቸውም :- ደንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፡፡
መግደላዊት ማርያምበእርሷ እና በእርስቶስ መካከል ጋሬጣ የሆነውን ትልቅ ቋጥኘ በመንገዷ ሁሉ ያሳስባት ነበር፡፡
ዛሬም ጌታችንን እንዳናገኘ ብዙ ቋጥኞች አስጨንቀውን ይሆናል፡፡ መግደላዊት ማርያም ግን ቋጥኙን ባትችለውም አለመቻሏ ጉዞውን አላደናቀፈውም፡፡
ጥያቄና ስጋት የሆነባት ነገር ሕያው ቢሆንም ወደኀላ አልተመለሰችም፡፡ ውጤቱ ግን ሕያው የሆነው ቋጥኙ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር፡፡
ድንጋዩ ተፈንቅሎ አየች፡፡
ዛሬም ክርስቶስን ለማየት የሚከለክሉን ብዙ ቋጥኞች አሉ፡፡ ከክርስቶስ በላይ መከበር የሚፈልጉ የስመ ቁልል እንደ እንደ ተራራ የተጫናቸው ሰው ሳይሆኑ መልዐክ ተብሎ እንዲነገርላቸው የሚሹ ትልልቅ ቋጥኞች ዛሬም አሉ፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈልግ ትውልድ በስጋቶች አይቆምምናወደ ክርስቶስ መገስገስ ያስፈልጋል፡፡ ያን ጊዜቋጥኙ ተንከባሎ የተነሳውን ጌታ የምስራች እንሰማለን፡፡
ዛሬስ ክርስቶስንእንዳናይ ጋሬጣ የሆነብን ምንድነው?? ኀጢያትና ሱስ ይሆን? በእምነት እንጓዝ ቋጥኙ ይንከባለላል፡፡ ክርስቶስን ለምትፈልግ ነፍስ ትልቅ ሆኖ የሚያስፈራት ችግር የለም፡፡ ከትልቅ ችግራችን ይል ክርስቶስ ለኛ ትልቅ ነው፡፡
የምንፈልጋቸው እንዲሆኑልን የምንመኛቸው ብዙ መልካም ነገሮች ቢኖሩም ድንጋዩን ማን ያንከባልልናል የሚል ስጋት ግነ አለብን፡፡ ራዕያችን ትዳራችን ወዳጅነታችንጨየራሱ የሆነ የፈተና ቋጥኘ አለው፡፡ የማይቀር ሆኖብን ብንጀምረው እንኳን ልባችን ግነ ይፈራል፡፡
በእምነት ብንጓዝ ግን ድንጋዩ ተፈንቅሎ እናይ ነበር፡፡ የእስራኤል ልጆች ባህር የተከፈለላቸው በመጓዛቸው ነው፡፡ እግዚአብሔር ወደፊት ለሚሉት ባህር መክፈል ቋጥኘ ማንከባለል ልማዱ ነው፡፡
#ህይወት_በኛ_መቻል_ላይ_የተመሰረተች_አይደለችም፡፡
እኛ ምንም የማንችል ደካሞች ነን፡፡
ሕይወት ሂደት ብቻ ሳይሆን ተአምራዊ ድልም የሚያስፈልጋት ናት፡፡ እግዚአብሔር ወደፊት በእምነት ለሚገሰግሱ ባህር የመክፈል ድንጋይ የማንከባለል ኃይሉን ያሳያቸዋል፡፡
እየጓዝን ነው ወይስ ፍርሃታችን ከቃሉ ይልቅ ከምነን ቆመናል??
መግደላዊት ማርያም ሞቶም ትፈልገዋለች፡፡
የፈለገችው ገዳይ ነን ብለው የፎከሩትን ሳይሆን ስለፍቅር የሞተውን ኢየሱስ ክርስቶስነ ነው፡፡
ሞቱን እንደ መረታት አልቆጠረችውም፡፡
#ስለ_ፍቅር_የሚሞት_እሱከ_ገዳዮች_ይልቅ_እርሱ_ጀግና_ነውና፡፡
ሞቱ እንድትረሳው አላደረጋትም ፍቅሯን እንድትገልፅ ውለታው አስገደዳት የእርሷ ፍቅር ከጊዜ ጋር አልተለወጠም ከራሷ ይለቅ ስለ ክርስቶስ ፍቅር አሰበች፡፡
ፍፁም ፍቅር ራስን በመርሳት ስለክርስቶስ ማሰብ መሆኑን አሳየች፡፡
ለማንም ሰው መቃብር ቋጥኘ አይገጠምም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ግነ ቋጥኘ ተደርጎበታል፡፡ አለም ገድላም የፈራችው ቢኖር ኢየሹስ ክርስቶስን ነው፡፡ አስቸጋሪ የተባሉ ሰዎች ሁሉ ከሞቱ በኀላ አስጊነታቸው ያበቃል፡፡ ክርስቶስ ግን ሞቶም ያስፈራል፡፡
ሞቶም ፈለገችው የፈለገችው ተአምር ተአምር እንዲያደርግላት ከደዌ እንዲፈውሳት አበርክቶ እንዲመግባል አልነበረም፡፡ ስለራሱ ስለጌታ ስለፍቅሩ ስለፍቅሩ ስለ ማንነቱ ፈለገችው፡፡ የምታመልከው እርሱን እንጂ ጥቅሟን አልነበረም፡፡ ከጉድለት በላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ማጣት ትልቅ ጉዳት ሆኖ ተሰማት፡፡
የክርስቶስ የሆነውን መውደድና ራሱ ክርስቶስን መውደድ የተለያየ እንደሆነ ይችህ ሴት፡ትመሰክራለች፡፡ የዚች ሴት ፍቅርጨፍቅራችንን ይታዘበዋል፡፡ ሁላችንመ አምላካችን ገዳይ እንጂ ሟች እንዲሆንልን አንፈልግም፡፡ ጠላቶቻችንን የሚበቀል በተነሱብን ላይ ፈጥኖ የሚፈርድ እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡ እኛስ አስከብሮ ራሱን ተፈሪ የሚያደርግ አምላክ እንሻለን፡፡
መግደላዊት ማርያም ሞቶም ጌታዬ ትለዋለች ሞቶ እንኳን ጌታዋ እንደሆነ አምናለች፡፡ በጣም የምናከብራቸው ሰዎች ተይዘው ሲታሰሩ በፍርድ ሲገደሉ በቀድሞ አጠራራቸው ሳይሆን በተለየ የንቀት አጠራር እንጠራቸዋለን፡፡ ማንም የምናከብረው ይዞ ሲገኘ ብቻ ነው፡፡ የተሸነፈን በቀድሞ ክብሱ አናከብረውም፡፡ ለጊዜው የተሸፈነ የሚመስለውን ይነሳል ብላ ያላመነችው ጌታዬ ማለቷ ይደንቃል፡፡
እኛ ትነሳዬውን የመንን ከእርሷ ይልቅ ጌታዬ ልንለው ይገባናል፡፡ ለእርሱ ያለን ፍቅርና አክብሮትም መቀጣጠልና መንደድ ይገባዋል፡፡
አሁንም ጌታዋ ነው አላፈረችበትም ሞቱ ለእርሱ ያላትን ክብር አልቀነሰባትም፡፡ ብዙዎችን ያሰናከለ ሞቱ አላሰናከላትም፡፡
ሞቶም በፍቅሩ የገዛት ክርስቶስ ነው፡፡
Post #1775
998