.....ስምዖን ጴጥሮስና ዮሐንስ መግደላዊት ማርያም ያመጣችውን የመሰረቁን ዜና ገና ሲሰሙ የአፏን ቃል ሳትጨርስጠወደ መቃብሩ ስፍራ ገሰገሱ፡፡
የኢየሱስ ስጋ አለመኖሩን ተረዱ መግደላዊት ማርያም የነገረቻቸውን አመኑ ፡፡ ልብ በሉ ያመኑት ግን ትንሳኤውን ሳይሆን ቅዱስ ስጋው በክፉ ሰዎች በጠላት መሰረቁን ያመኑተ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ሳይሆን በጠላቶቹ የክፋት ሀይል ነው፡፡ አለመኖሩን ካረጋገጡ በኀላ ወደቤት ተመለሱ፡፡
ከነገረቻቸው በኀላ በሦስተኘነተ የደረሰችው የመጨረሻዋ ሯጭ መግደላዊት ማርያም ግን ከእነርሱ ኀላ ብትደርስም ኢየሱስ ክርስቶስን ካላገኘሁ አልነቀሳቀስም ብላ በመቃብሩ ስፍራ ፍለጋዋን ቀጠለች.....በዮሐንስ ውጌል እንደምናነበው ኢየሱስን ያገኘችው ይቺው ሴት ናት፡፡ አንደኛ የመጣውም ሁለተኛ የደረሰውም አላገኙትም፡፡ የመጨረሻዋ ሯጭና ቆራጧ ሴት ግን ክርስቶስን አገኘችው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘውአንደኛ ለወጡት ሳይሆን ለሚፈልጉትና ቆርጠው ለወጡት ነው፡፡
መግደላዊት ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስን በብርቱ ትፈልገው ነበር፡፡ እርሱን ካላገኘች ወደቤቷ ለመግባት ጠልታ ዱር ቤቴ ብላ ትባዝናለች የምትፈልገው ጌታዬ እያለች እየመሰከረችለት የዕንባ ፈሳሽ እያፈሰሰች ነበር፡፡ መላዕክት ቢገለፁላትም እርሱን ግነ አልተኩላትም እርሱን እስክታገኘ ዕረፍት አልነበራትም፡፡
አንዳንዶች ክርስቶስን አውቀው ፍቅር ይግዛኘ ህለውናህ ይሰማኘ እያሉ በእንባ ይሹታል ለዘላለም ህይወት ይፈልጉታል፡፡
አንዳንዶች ስለ አስቤዛ ስለኑሮ መሟላት ብቻ ክርስቶስን የሚፈልጉት ናቸው፡፡
እኛስ ከየትኞቹ ፈላጊዎች እንመደብ ይሆን??
እሷ ክርስቶስን የፈለገችው በብርቱ ነው፡፡ የእርሱ የቅርብ ደቀመዛሙርት እነኳን ፍላጎታቸውን አቋርጠው ወደ ቤታቸው ቢመለሱም እርሷ ግን ተስፋ ቆርጣ አልተመለሰችም፡፡ በልቧ እንደ ጴጥሮስና ዮሐንስ እኔ ለእርሱ ቅርብ አይደለሁም እቤቴ ቁጭ ብዬ የሆነውን እሰማለሁ አላለችም፡፡ ከአምስት ገበያ ከሚያህል ህዝብ አንደ ፈላጊ ያጣውን ጌታ ብቻዋን መፈለግ ጀመረች፡፡
እርሱን በእውነት የሚፈልጉ የዘመናት ፈተናቸው ብኘነት ነው፡፡ ትልልቅ የሚባሉ ሰዎችም ብዙ የተማሩ መንፈሳውያን መሪዎች በሌሉበት እርሱን መፈለግ ማስተዋል ነው፡፡
መግደላዊት ማርያም የምታለቅስበት ምክንያቱ ጸጋን አጣሁ የሚል አልነበረም #ባለፀጋውን አጣሁት የሚል ነበር፡፡
ጌታ ኢየሱስ ከዚህ በላይ ተሰውሮ መቆየት አልሆነለትም፡፡ እርሱጠበእውነት ለሚሹ የቅርብ አምላክ ነውና፡፡ እርሷ፡አታየውም እርሱ ግን ያያታሌ አልተሰረቀም ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ እንጂ እርሱ ከመቃብር ስፍራ አይፈለግም ከመሬት በታች የለም ከሰማያት በላይ ገኗል፡፡
ኢየሩሳላም የገፋችው ዝናው በአለም ሁሉ ወጥቷል፡፡
የፍቅር ጌታ የማርያምን ሰቀቀን ችሎ መቆየት አልሆነለትም፡፡ በሀይሉ ጉልበት ሁሉ ሲረታ በፍቅር ግን ይሸነፋል ስለዚህ ተገለፀላት፡፡ ይህንም ብላ ዘወር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው ኢየሱስ እንደሆነ ግን አላወቀችም፡፡
ኢየሱስም:- "አንቺ ሴት ለምን ታለቅሻለሽ ማንንስ ትፈልጊያለሽ አላት"፡፡ የመላዕክቱን ጥያቄ ደገመላት አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ ማንን ፈልገሽ ታለቅሻለሽ አላት "ማን" ለሕያው የሚጠቀስ ነው፡፡ "ምን" ለቁሳቁስ ፍላጎት የሚጠቀስ ነው፡፡ እኛን ቢሆን "ምን" ፈልጋችሁ ታለቅሳላችሁ?" ይለን ነበር፡፡
መግደላዊት ማርያምም ግን አላወቀችውም፡፡ "እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት ጌታ ሆይ ንተ ወስደኸው እንደሆነ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኘ እኔም እወስደዋለሁ አለችው"
#እኔም_እወስደዋለሁ ለመሆኑ ትችለዋለች?? ወስዳ የት ታደርገዋለች ፍቅር ከመቻል ያልፋልበዚ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን መሰወር አልቻለም "ማርያም" አላት እርሷም በአካል ቢገለጥ ፣ጠይቃት አላወቀችውም፡፡ በስሟ ሲጠራት ግን አወቀችው የእርሹ አጠራር ከሌሎች አጠራር የተለየ ነው ቅላፄው የድምፁ ቃና የቃላቱ ፍሰት ዘላለማዊ ፍቅር የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ቃና ሲጠራት ነፍሷ ተላወሰ ልቧ ተቃጠለች፡፡
እነዚያ የሚፈጥሩት ቃላትሀዘኗ እንደ ጉም ሲበትኑት በቅፅበት ተሰማት፡፡ ከሦስት ቀን በፊት የምታውቀው ያ ድምፅ ነው፡፡ ይህ ድምፅማ ያኖረኘ ዕድሜ የቀጠለልኘ የመኖር ፍላጎቴ የጨመረልኘ ለራሴ ዋጋ እንድሰጠው ያደረገኘ ነው፡፡ በፍፁም ፍቅር እንዲህ ብሎ የሚጠራኘ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም የለም ብላ
#ረቡኒ አለችው፡፡ በሕብራይስጡ #መምህር ሆይ ማለት ነው፡፡
ለደቀመዛሙርቱና ለመላዕክቱ "ጌታዬ" ብላ ገልፃዋል፡፡ ራሱን ግን መህህሬ አለችው፡፡ በእርግጥም እርሱ ጌታም መምህርም ነው፡፡
ከአለም ላይ ከሚገኙ ጌቶች እርሱን ልዩ የሚያደርገው በፍቅር በርህራሔ የሚገዛ ጌታ መሆኑ ነው፡፡ መምህርነቱም ከመምህራን የተለየ ነው፡፡
መግደላዊት ማርያም #ሩቡኒ ስትለው አውቀዋለሁ የምለው እውቀቴ ዕድሜ ያስገነዘበኘ ነገር ሁሉ ያለወጠኘ አንተ ግን እራሱን ከሚያስፈፅም ቃልህ ጋር ወደእኔ የመጣህ የለወጥከኘ መምህሬ ነህ ማለቷ ነው፡፡ የሕይወትህን ሆሄ የቆጠርኩብህ ኑሮና አገርን ከሰው ጋር መግባባት ያስለመድከኘ ብርሃኔ ነህ፡ማለቷ ነው፡፡መሳሳቴ የማይቀበለውም ግትር ማንነቴ በትዕግስት በፍቅር ቃላትየመለስክልኘ ወድቃ ትማር ብለህ ያልተውከኘ በቀና ኞዳና የምትመራኘ የፍፃሜዬ አምላክ፡አንተ ነህ ማለቷ ነው፡፡
ለኛ ሲል የሞተውን ክርስቶስን እንደዚች ሴት ለመፈለግ ፍቅራችን ምን ያህል የፀና ይሆን??
እሷ ሞቶ ፈለገችው እኛስ ትንሳኤውን ያመንን በጥቂቱ እንኳን ፈልገነው ይሆን??😔😔😔😔
#መግደላዊት_ማርያም_አስደናቂዋ_ሴት
የዲ/ን አሸናፊ መኮንን
#ረቡኒ
ከሚለው ትንሽዬ መፅሐፍ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንዲህ አቀረብኩት፡፡
ሙሉ መፅሐፉን ታነቡት ዘንድ ግብዣዬ ነው
@jahABP ነኘ
መልካም በዓል
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1776
1.19K