TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #1775 · Back to latest

Older Posts 17 shown
Post #1770 778
AB PHOTOGRAPHY

#WEDDING_PHOTOGRAPHY

#CONGRA_EYOBA_MEKDIYEE
@abiy_yemaryam_leje

#street_photography

#best #awesome #timing

#photoshoot

#our #lovely😍 #ethiopia
#ADULALA_RESORT
Post #1769 807
በእውነት ነው ምላችሁ የትንሳዔ በዓል እስኪደርስ በጣም ቸኩዬ ነበር ምክንያቱም አንዲት ጠንካራ ሴት ላስተዋውቃችሁም በዛውም ስለትንሳዔው አንዳንድ የሚያስገርሙ ሁሌም ሳነበው ድንቅ የሚለኘን ነገር አይ እኔ🤦‍♂🤦‍♂😔😔ብዬ እራሴን የምወቅስበት ከአንድ ትንሽዬ (40 ገፅ መፅሐፍ) ያገኘሁዋትን በጣም ጥልቅ የሆነ ምክር ካገኘሁባት ድንቅ መፅሐፍ ላካፍላችሁ ጓጉቼ ነበር.....እንዳሰብኩት ሳይሆን ቀረና በስራ መደራረብ ሳልፅፈው ቀረሁ፡፡

"ለመሆኑ ይቺ ሴት ማነች??🤔🤔
ለምንስ ሁሉም መሰከረላት
ማነች ይቺ ሴት ፍፁሙ ፍቅር ራስን በመርሳት ስለ ክርስቶስ ማሰብ መሆኑን ያሳየች
ማነች ይቺ ሴት ሞቶ የፈለገችው??
ማነች ይቺ ሴት ከጉድለት በላይ ኢየሱስ ክርስቶስን ማጣት ትልቅ ጉዳት መስሎ ሆኖ የተሰማት??
ማነች ይቺ ሴት የክርስቶስ የሆነውን መውደድና ራሱን ክርስቶስን መውደድ የተለያየ እንደሆነ ያሳየች
የዚህች ሴት ፍቅር ፍቅራችንን ይታዘበዋል፡፡ ሁላችንም አምላካችን ገዳይ እንጂ ሟች እንዲሆንልልን አንፈልግም፡፡
ጠላቶቻችንን የሚበቀል በተነሱብን ላይ ፈጥኖ የሚፈርድ እንዲሆን እንፈልጋለን

በድካም የሞተውን ወይም ዝም ያለውን ክርስቶስ እንደዚህች ሴት ለመፈለግ ፍቅራችን ምን ያህል የፀና ይሆን?????"

ሁሌም ደጋግሜሜሜ እራሴን እጠይቀዋለሁ😔😔😔😔

ትልቅ ይቅርታ🙏🙏 በመጠየቅ አሁን ከመፅሃፉ ጀባ ልላችሁ ተመኘሁ፡፡

@jahABP ነኘ
ብዘገይም አልቀርም ጠብቁኘ፡፡

መልካመ የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ😍😍😍
Post #1768 795
እኛስ ኃጢአታችንን ለማስተሥረይ በሥጋ እንደታመመ፤ እንደሞተ፤ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ሥጋውን እንደገነዙ፤ ከሙታንም ተለይቶ በእውነት እንደተነሣ፤ ከተነሣም በኋላ በእውነት ወደ ሰማይም እንደ ዐረገ እናምናለን፡፡ ኋላም እርሱ በሚመጣው ዓለም በሕያዋን በሙታን ይፈርድ ዘንድ ይመጣል፤ የሰውን ወገኖች ሁሉ በሞቱበት፤ በተቀበሩበት ሥጋ ከሞት ያስነሣቸዋል፤ ከትንሣኤውም በኋላ ያለመለወጥ ሁል ጊዜ ይኖራል።

እንኳን ለ 2013 የትንሳኤ በዓል አደረሰዎ

ተከስተናል ለማለት ያክል ነው
@jahABP
Post #1764 864
ትላንት ካነሳኀቸው ልቤን የነካው ፎቶ😔😔😔💪💪💪💪👏👏
Post #1758 768
ሆሳዕና በአርያም😍😍😍😍😍



እስኪ በበዓሉ ያነሳኀቸውን ፎቶዎች፡ጀባ ልበላችሁ.........

ጠብቁኘማ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Post #1757 1.33K
25 ዓመት

ሰዎች ይወዱኛል....ለምን ካላችሁ እኔ ስሪት ነኘ የሰሩኘን መልካሙን ይዤ እየቀጠልኹኘ ነው፡፡

አያቴ ነች አሉ......(እናቴ ነች ይሔን ታሪክ ምታጫውተኘ)..........ወደ ረፋዱ ወደ እኛ ቤት በላይነሽ በላይነሽ እንዴት አረፈዳቹ
አቤት እማዬ አለች እናቴ ጋደም ካለችበት ትንሽዬ የሻር ፍራሽ እየተነሳች እኔ ሆድ ውስጥ እንዳለሁ የአያቴን ድምፅ ስሰማ ዘለልኩ ዘለልኩ ምን ዘለልኩ ብቻ ተከረባበትኩ በጣም መዝለሌን ያወኩት አብሮኘ ያለው መንታ ወንድሜን በካልቾ ብዬ ደም በደም ሳረገው እናቴ እዮዮዮ አዶተና አዶተና ብላ አንድ ጊዜ ሆድዋን አንድ ጊዜ ደግሞ ወገቧን ስትይዝ ነው😁😁😁

አያቴም እንዲህ አለቻት ዛሬ ነው ምቶልጂው ከዛሬም አታልፊም የአመቱ መድሀኒአለም አይደል ቤተክርስቲያን ልሔድ ነው ታቦትም ይወጣል እለቱም አርብ ነው ቅዳሴ ከሰዓት ነው ማስቀደሴም አይቀርም እስክመለስ ወልደሽ ጠብቂኘ ምንም እንዳትፈሪ አለቻት እናቴም፡እሺ እሺ አለች በልጅነት እድሜዋ እኛን ተሸክማ..............

አያቴ.....ያለችውም አልቀረም ከሰዓት እናቴ ጠብ አረገችን በለው ሁሉም ተደሰተ ተደሰተ የአይን ማረፊያ ተሰጠን አሉ ቆንጅዬ ልጆች ተወለዱልን አሉ ሁሉም ቤተዘመድ ተደሰተ..........😍😍

መድሀኒዓለም አባቴ ኑር ብሎ ፈቅዶ አመጣኘ፡፡

ፈጣሪ ከአራቱባህርያተ ስጋ እና ከሦስቱ ባህርያተነፍስ በጥበቡ ከፈጠረኘ በኀላ

እኔ የብዙ ሰው ስሪት ነኘ.........

ከልጅነቴ ጀምሮ ያሳደገችኘ አያቴ ከስሯ ማልጠፋዋ አያቴ ስሪት ነኘ

ሰው ወዳጅ ዘመድ ሰብሳቢ ለተቸገረ ደራሽ ለተቸገረ አጉራሽ ሰው በልቶ ሚጠግብ ማይመስላት እንግዳ ሲመጣ ሁሌም አዲስ ብላ ያስቀመጠቻቸውን እቃዎች አውርዳ አንድም ሳይከፋ አንድም ሳይጎልበት ተንከባክባ የምትሸኘዋ የኔ ቢጤዎች መተው እንደቤታቸው የምታስተናግደዋ ሁሌም፡ለሰዎች የተሻለ የምታስበዋ ሁሉን ወዳዷ እጇ ላይ ብር ካለ የተቸገረ ሰው ፈልጋ ምትሰጠዋ...ልንተኛ ስንል ቀሚሷን በአንድ እጄ ይዤ በእንቅልፍ ልቤ ወደ ውጪ አብሬያት ተከትያት ወጥቼ እራሷን በመቁጠሪያ እየደበደበች ወደ አምላኳ የምትፀልየዋ እራ ሷን ደብድባ ስትጨርስ በዚ ብርድ ማን ውጣ አለህ ተኘተህ አትጠብቀኘም(ሁሌ እንደዚ ነው ምትለኘ) ብላ እንዳይበርደኘ ሰብስባ ጭኗ ስር ከታ በል አባታችን ሆይ በል እና እንግባ የምትለኘ ሁሌም ተመሰገን ማለት ከአፏ የማይጠፋዋ፡፡ የፀሎትን ሀይል ያስረዳችኘ ከሰጠን ፈጣሪ አብዝቶ የሚሰጠን መሆኑን ሁሌ የምትነግረኘ ለስራ ደከመኘ የማታውቀዋ የሷ የውዷ የአያቴ ስሪት ነኘ፡፡(አያቴ አንቺ ህይወቴ ነሽ)

የእናት እና የአባቴ የእኩል ድርሻቸው ስሪት ነኘ፡፡

ፈጥረውኛል ከማንም በላይ ዝንጥ አድርገው አሳድገውኛል ለኔ ሲሉ ብዙን መከራ አይተዋል ተቀብለዋል ድሃ ናቸው በምን፡ሊያሳድጉ ነውም ተብለዋል እንደ ሰው አይደለም የነሱ መድሃኒዓለም ይኸው 25 አመት ላይ አድርሶኛል ታሪክን አጫውተውኛል (ብዙ ነው በጥቂቱ ልናገር) አባቴ እናንተን ለማሳደግ ብዙ ስራ ሰርቻለሁ ሸዋዳቦ ስሰራ ግን እረፍት እንኳን ስላልነበረኘ ሻወር ልግባ ብዬ ሻወር ከፍቼ ትንሽም ብትሆን የተኛሁበት ጊዜ አልረሳም ይለኛል..😢😢😢😔😔የኔ ሚስኪን አባቴ❤️.....እናቴ መንታ ተሸክሜ ብዙ ቦታ ቡና ለመሸጥ እሯሯጥ ነበር ደም እየፈሰሰኘ 😢😢😢😢😔😔🤦‍♂🤦‍♂ የኔ ጠንካራዋ እናቴ❤️
ሀይማኖተኛ ናቸው ለፀሎት አይደክሙም አባቴ ከማውቀው ጀምሮ አሁንም ድረስ ለሊት ስነቃ እየፀለየነው ፀሎቱን አያቋርጥም አስታውሳለሁ ልጆች ሆነን ጮክ ብሎ ይዘክራል እናምከሱ እኩል ለማለት እንሞክራለን በሱ ጎዳና ተጉዘን ይኸው አሁን ስንዘክር እሱ ሚላትን፡አንድም ቃል አናዛንፍም እራሷን ቁጭ በህፃንነት አንደበታችን አይምሯችን ላይ አስቀምጠናታላ፡፡

ከዘከረ በኀላ ከታናሽ ወንድሜ ጋሪ(ሲሩ😍😘) ፀሎት አድርጉ ይለናል እሺ እንላለን ግን አይናችሁን ጨፍኑ ይለናል እንደተባልነው እናደርጋለን ፀልየን አይናችንን ስንከፍት ከስር አንድ ብር ተቀምጦልናል አቤተ ደስታችንንን😁😁😃😃😃 እሱም እንዲህ ይለናል አስታውሱ ልጆቼ እግዚአብሔር አምላክ ከልብ ከለመናችሁት ምንም ነገር አይከለክላችሁም ይለናል ይኸው አሁንም ድረስ ለምኜ ማጣው አንዳችም ነገር የለም፡፡ እናታችን እንዲህ ትላለችበሉ ብሩን ለብቻ እንዳታጠፉት ሁሉንም ልጆች ጥሩና ለሁላችሁም የሚበቃ ነገር ግዙበት ትቻለች ተካፍሎ መብላትን ትዘራብናለች፡፡አባታችን እጁን ያሳረፈብን ቀን በጣትየሚቆጠር ቀን ነው(የኔ ሚስኪን🙏) እናታችን ግን በጣም ሀይለኛ ነች ሀይለኛ በጥርሷ ነው የምትበላን ይኸ ወደ መጥፎ እንዳንጓዝ አድርጎናል(💪🙏) የናንተ ስሪት ነኘ በፈጣሪ ተስፋ ማድረግ የፅናት ተስፋ አለመቁረጥ ድህነት ያልበገረው ትዳር ያፈራኘ፡፡


የታላቅ እህቴ ስሪት ነኘ

ልታይ ልታይ የማትለዋ እንደዘመኑ ሴት ያልቀበጠችዋ ስትናገር እርጋተዋ ስትበላ እርጋታዋ ጮክ ብላ ተናግራ ማታቀዋ አንድ ገር ልክ መሆኑን ካላረጋገጠች እርግጠኛ ሆና የማትናገረዋ ወንድሞቿን ከራሷ አስበልጣ የምትወደዋ ይሔን አድርጉልኘ ይሔን ይገዛልኘ ሳትል ሰፈር ውስጥ ድምፇ ሳይሰማ ከትምህርትቤት እቤት ከቤት ትምህርትቤት እዛ እዚ ሳትል የቤተሰቦቿን ስም ሳታስጠራ ደና አድርጋ ተምራ ቆብ የጫነችው የሷ ስሪት ነኘ፡፡

እንደእንቁላል የተንከባከበችኘ ችግር ውስጥ ስገባ አክስቴ ለገብሬልሽ ንገሪልኘ ብዬ ስላት ልመናዋ ቀናት ማይቆዩባት የሷ ስሪት ነኘ፡፡

አብዬ በቀን ብዙ ጊዜ ፀሎት ማድረግ ይኖርብን ይሆናል አኛ ግን ሰነፎች ነንና ሰአቱን ጠብቀን ለማድረግ አንችልም ግን ቢያንስ ስንበላ አንድ አባታችን ሆይ ማለት መልመድ አለብን አየህ በቀን ሶስት ጊዜ እንኳን ብንመገብ(ቀርስ ምሳ እራት) ሦስት ጊዜ አምላካችንን ማመስገኛ ጊዜ አለን ብላ ስበላ አባታችን ሆይ ማለትን ያስለመደችኘ የሷ የመንቢ😍 ስሪት፡፡

አቱንም ድረስ ብዙ ሰው የሚያስታርቀው አንደበተ እርዕቱው የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር ቀልብን የሚስበው.......
እእእ በስራ የሚያምነው ቤቴን ማለትን ያስተማሩኘ የነሱ የአጎቶቼ ስሪት ነኘ፡፡

በህፃንነቴ ልብሴን እያጠበች ኧረ ካካውን ወደዳር አውጪው አጨማለቅሺው ስትባል የአብዬን ብላ አንስታ ጉርስ ያደረገችው መውደድን በተግባር የገለፀችልኘ የሷ የፅግዬ ስሪት ነኘ፡፡


የዛሬ ዝቅ ማለት ለነገ ከፍታችን መሆኑን የምትነግሩኘ ከሁሉ አብልጣችሁ የምቶዱኘ ወንድሞቼ ከማንም በላይ የምትረዱኘ አንድሽ ብሩኬ ሲራኬ ያናንተ ስሪት ነኘ፡፡

የፒኮክ ሰፈር እናቶቼ እና አባቶቼ የእናንተ ስሪት ነኘ ሁላችሁም እኔ ላይ የራሳችሁ ድርሻ አላችሁ፡፡
አብሮአደግ ጓደኞች ሁላችሁም ይህ ነው የማይባል የራሳችሁ ድርሻ አላችሁ እስካሁን ያስተማራችሁኘ አስተማሪዎች በሙሉ እናንተም የመልካምነትን ድርሻ ትወስዳላችሁ፡፡

ከላይ ያሉት ሰዎች በመልካሙ ቀርፀው አሳድገውኛል እኔም መልካሙን ይዤ የሚበጀኘን አመዛዝኜ ይኸው የሆንኩትን፡አብይ ሆኛለሁ ፡፡

አስታውሱ መጥፎ ሆናችሁ ሰዎች ጥሩ ናችሁ ቢላችሁ ጥሩ ናችሁ ማለት አይደለም ጥሩ ሆናችሁ መጥፎ ናችሁ ብትባሉም መጥፎ ናተትሁ ማለት አይደለም የምትሆኑተ የሆናችሁትን ነው እንጂ፡፡

ትህትናሽ ግሩም የሆነ ህይወት አኗኗርሽ ሁሌ ትምህርት ቤቴ የሆነ ለአፍታ ከአፌ የማትጠፊ የአምላክ እናት ወላዲተ አምላክ ሁሌም ከልቤ አትጠፊም እናቴቴቴ የአንቺ ልጅ ነኘ፡፡ አቤት እድለኘነቴ😍🙏

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD
Post #1756 1.1K
AB PHOTOGRAPHY

የልደቴ ቀን በጠዋትትትት ያነሳሁት ፎቶ

የአባቴ ቤት
ኑር ብለህ ስለፈቀድክልኘ መድሐኒአለም ሆይ አመሰግንሃለሁ🙏🙏🙏😍😍😍


@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1755 1.03K
በነገራችን ላይ ዛሬ የተወለድኩበት ቀን ነው፡፡

የተወሰነ ነገር ልላችሁ እፈልጋለሁ፡፡

ስለተሰጡኘም ስጦታዎች ጭምር😍🙏
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →