TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #1754 · Back to latest

Older Posts 9 shown
Post #1753 1.03K
እሺ እናታችሁን ጠልታችሁ ታውቃላችሁ???

ያስገርማልም ያናዳልም አይደል ጥያቄው🤔😳😳😡😡..........

እንዴት እናት ትጠላለች ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ ግን እናቱን ሚጠላ የለም ማለት አይቻልም🤷‍♂🤷‍♂

እስኪ ቀጣዩን ታሪክ አንብቡና .... ትፈርዳላችሁ፡፡

🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ጠብቁኘማ

@jahABP ነኘ 😊😍😊
Post #1751 1.26K
AB PHOTOGRAPHY & GRSPHIC DESIGN

#ቅዳሴ_እና_ቀረርቶ

እንዴ ቢሆንስ ለምን ሁለት ሰዓት አይሆንም፡፡ ስሜት የማይሰጠኘን ሁለት ደቂቃስ ቢሆን ለምን አሳልፋለሁ? ደስታን የማይደምርልኘ የትም ቦታ መገኘቴን ራሴን እንደማባከን እቆጥረዋለሁ፡፡

በሰዎች በየቦታው ፍፁም ትክክል መስለው ሲታዩ ሰውኛ አይመስለኘም፡፡ ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሹን ያጣ አሳዛኘ ይመስለኛል፡፡ ለእያንዳንዱ ነገሩ የሚጠነቀቅ ሰው ራሱን እየሆነ እንዳልሆነ ነው የሚገባኘ፡፡

#ራስን_መሆን_እርማት_አይጠይቅም፡፡
#ራስን_ለመሆን_ጥንቃቄ_አያሻም፡፡

መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ጋር ጥቂት እብደት ጥቂትም ስህተት ጥቂትም ስህተት ጥቂቅም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ፡፡

የሰዎችን ጥሩነት በዝምድና ትስስር ስንለዋውሰው ግራ ያጋባኛል፡፡ በምን ሒሳብ በደም መቀላቀሉ የሰዎችን ውለታ እንደሚያከብደው አይገለጥልኘም፡፡ እንደእኔ እንደውም ያለ ምንም ደም ግምድ ደግ መሆናቸው ዋጋቸውን የሚጨምረው ይመስለኛል፡፡

አንዳንዴ ትክክል መሆን ብቻውን ዋጋ ትልቅ አይመስለኘም፡፡ የሚቀበለው ሰው ጋር የሚረግጠው ቁም ነገር ይመስለኛል ትክክል የሚያስብለው፡፡ ምንስ ልክ ቢሆን ከማቅናት ይልቅ ካደቀቀ ልክነቱ የቱ ጋር ነው???

አስቀያሚ አይደለሁም ፡-

እግዜር የስሜት ባለቤት ከሆነ የእርሱ ፈገግታ የመሰለ ውበት አለሽ ባሉኘ ማግስት ምን ያደርጋል የሰከነች እይደለችም ይሉኛል ፈገግታሽ የሰማይ መልዕክትን መጎናፀፊያ ይመስላል ባሉኘ ማግስት እንደሸርሙጣ ታስካካለች ይሉኛል የሰውነቴን መዋቅር ከምርጥ ቀራፂ ውብ ቅርፅ ጋር ባነፃፀሩት ማግስት ክብሯን አትጠብቅም ለስሜቷ ትተኛለች ይሉኛል፡፡

ያላዋቂ አይደለሁም:-

ቤተሰቦቼ እና በደቦ ያሳደጉኘን የሰፈሬን ሰዎች ጨምሮ የሚያውቁኘ ሁሉ ከመዋዕለ ህፃናን ጀምሮ እስከ ማስተርስ በማዕረግ መጨረሴት አድንቀው ሳይጨርሱ ምን ያደርጋል ቆማ መቅረቷ ነው ይላሉ፡፡ ማወቅ የሚሹት ነገር ሲኖር እንዳልጠየቁኘ የዕለት መፍትሔ ሲሹ እንዳላማከሩኘ በኪሎ የሚበልጣትን መፅሐፍ ይዛ የምትዞር ጉረኛ ናት ይሉኛል፡፡

ስሜት አልባ አይደለሁም፡-

ዛር እንዳለበት ባለውቃቢ አብሮኘ እንዳላበደ የሚያደርገኘ ጠፍቶት በስሜት እንዳልከሰረ የሱ እብደት ጎበዝ ሲያስብለው የእኔ ያለመሾኮርመም ብዙ ወንድ የምታውቅ ባለጌ ያስብለኛል፡፡

አመለ ቢስ አይደለሁም፡-

ግልፅነቴ ደንቆት አንቺን ያገኘ ወንድ አፈሰ ባለኘ ቅፅበት "ለምን ታዲያ አንተ አታፍሰኘም?" ስለው "ሴስ ልጅ አንዲ አትልም" ይለኛል፡፡

አላማኘ አይደለሁም፡-

ሀይማኖቴ ፍቅር ነው፡፡ የሰውን ልጅ ሁሉ መውደድ፡፡ ራሴን እወዳለሁ ለዛ ነው ሌሎችን የሚወድ ልብ ያለኘ፡፡ ለራሱ ፍቅር የሌለው ለሌላ ተርፎት የሚለግሰው መውደድ አለው ብትሉኘ ያንቀኛል፡፡ በሰውኛ ልኬት ሰውን የመውደድ ጣሪያ ራስን ከመውደድ ልክ መሆኑን ለማሳየት ይመስለኛል ክርስቶስ ከሕግ ሁሉ የበላይ ሕግ የትኛው መሆኑን ሲጠየቅ 'ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ ያለው፡፡

የፈጣሪ ትርጉሙ ለኔ ፍቅር ነው፡፡
የማላየውን ፈጣሪ ማምለክና መውደድ በአምሳሉ በፈጠራቸው በሰዎች ሁሉ ውስጥ አለ ብሎ ማመን እነርሱን ማክበርና መውደድ ነው፡፡

#ፍቅር_ከክፋፍ_በብዙ_የራቀ_ነውና_ለክፋት_የሆነ_ልብ_የለኘም፡፡

አንዳንዶች ግን እንደ እነርሱ በሀይማኖት ካባ ራሴን ደብቄ አለማስመሰሌን እኔኑ እያሙ እዛው ካባቸው ውስጥ ይደበቃሉ፡፡ በልባቸው ጠብታ ቅንነት ሳይኖር ለፍቅርና እግዜርን ለመፍራት የሚኖሩ ያስመስሉታል፡፡ እኔ ግን ከክፉ ልብ ከመነጨ ምርቃት ይልቅ በአንድ ልኩ ከቅን ልብ የሆነ እርግማን ይሻላል ባይ ነኘ፡፡

የእኔ ስም የኔ መጠሪያ ሳይሆን የወላጆቼ ተረክ ነው፡፡ያለፈ ታሪካቸው የውልደቴ ፈንጠዝያቸው ፡፡
ምን አለፋችሁ ያደለው 'የሕይወቴ እርምጃ ከአፍ እስከደገፉ እያለ' መፅሐፍ ይፅፋል የእኔ ቤተሰቦች የሕይወት ታሪካቸውን ለዓመታት እንዲነበብ በኔ ስም በደማቁ ፅፈውታል፡፡
የሚጠራኘ ሁሉ ያነብላቸዋል፡፡

እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል፡፡ ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል፡፡
ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም፡፡ ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ፡፡ ልብህን ከከፈትክላቸው የድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ፡አልባ ያደርጉሃል፡፡

በህይወቴ አንዲት የምደምቅበት ቅፅበት እንዲኖረኘ እመኛለሁ፡፡
ከስሜ ቀድሞ #ኢትዮጵያዊነቴ የሚጠራበት ቅፅበት፡፡
ተሳካልኘ የምለው የሀገሬን ስም የማስጠራበት አንዲት የደመቀች ቅፅበት በህይወቴ ሲፈጠር ነው፡፡
አላማው ማሸነፍ አይደለም፡፡ መወዳደሩ ላይ ነው ፡፡ #ኢትዮጵያዊ ተብሎ ውድድሩ ላይ መገኘት፡፡
በህይወቴ አንድ የድምቀት ቅፅበት ነው የምመኘው፡፡
የእኔ መድመቅ ውብ የሚሆነው #የሀገሬን ስም ስሸከም ነው፡፡
ስሜ ብቻውን መጠራቱ የእኔ ቅፅበት ይሆናል፡፡ ከስሜ በፊት የሀገሬ ስም መቅደሙ የሚጨምረው ክብር ግን የተለየ ነው፡፡....#ኢትዮጵያዊቷ...🇲🇱🇲🇱🇲🇱💚💛❤️

ሜሪ ፈለቀ😍😘😘👏👏🙏🙏
ጠበኛ እውነቶች
#ቅዳሴና_ቀረርቶ

@jahABP😍😊🙏ነኘ

ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀረብኩት መፅሐፉን ገዝታቹ አልያ ተበድራችሁ አንብቡት ትወዱታላቹ ራሳችሁን ምታስቡትን ሐሳብ በድንቅ አገላለፅ እና ታሪክ ተዋቅሮ ታገኙበታላች ሴት ልጅ እንዲህ በነፃነት ድንቅ ሀሳቦችን ስታስተላልፍ እንዴት ደስ ይላል ሜሪዬ(ኢትዮጵያዊቷ) ለሀገርሽ የሆነ ነገር፡አበርክተሻል በርቺልን በሌላ ድንቅ ስራ እንደምትመጪ ባለሙሉ ተስፋ ነኘ እንዳንቺ አይነቶቹን ያብዛልን አቦ...😍😍

እያነበብን እያነበብን...ከመፅሐፉ...እንቀጥላለን
🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
ቆዩልኘ😍😁😊😊👏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1750 849
ያልተኛችሁ ይኸው ከጠበኛ እውነቶች ተካፈሉ....

ጀባ ጀባ😍😍😍🏃‍♂🏃‍♂
Post #1748 1.14K
ሜሪ ፈለቀ #ጠበኛ_እውነቶች

አነበብኩትና ይኸን ላካፍላችሁ ወደድኩ

መፅሐፉን አንብቤ አልጨረስኩትም ግን

እኛ ሰነፍን እንጂ

ሀሳብ እኮ አለ.....ይመችሽ አቦ

እያነበብን እያነበብን📖📚📖

@jahABP ነኘ
Post #1741 1.34K
AB PHOTOGRAPHY

መልካም ልደት #ኤልያና_ሮቤል

ረጅም ዓመት ከጤና ጋር እመኘልሻለሁ ሁሉም፡የሚንቃት ሳይሆን ሁሉም የኔ በሆነች ብሎ የሚመኛት እንድትሆኚ የዘወትር ምኞቴ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ኤልያና ብዬ ስም ያወጣሁላት እኔው ነኘ፡፡😍😍😍😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →