በእውነት ነው ምላችሁ የትንሳዔ በዓል እስኪደርስ በጣም ቸኩዬ ነበር ምክንያቱም አንዲት ጠንካራ ሴት ላስተዋውቃችሁም በዛውም ስለትንሳዔው አንዳንድ የሚያስገርሙ ሁሌም ሳነበው ድንቅ የሚለኘን ነገር አይ እኔ🤦♂🤦♂😔😔ብዬ እራሴን የምወቅስበት ከአንድ ትንሽዬ (40 ገፅ መፅሐፍ) ያገኘሁዋትን በጣም ጥልቅ የሆነ ምክር ካገኘሁባት ድንቅ መፅሐፍ ላካፍላችሁ ጓጉቼ ነበር.....እንዳሰብኩት ሳይሆን ቀረና በስራ መደራረብ ሳልፅፈው ቀረሁ፡፡
"ለመሆኑ ይቺ ሴት ማነች??🤔🤔
ለምንስ ሁሉም መሰከረላት
ማነች ይቺ ሴት ፍፁሙ ፍቅር ራስን በመርሳት ስለ ክርስቶስ ማሰብ መሆኑን ያሳየች
ማነች ይቺ ሴት ሞቶ የፈለገችው??
ማነች ይቺ ሴት ከጉድለት በላይ ኢየሱስ ክርስቶስን ማጣት ትልቅ ጉዳት መስሎ ሆኖ የተሰማት??
ማነች ይቺ ሴት የክርስቶስ የሆነውን መውደድና ራሱን ክርስቶስን መውደድ የተለያየ እንደሆነ ያሳየች
የዚህች ሴት ፍቅር ፍቅራችንን ይታዘበዋል፡፡ ሁላችንም አምላካችን ገዳይ እንጂ ሟች እንዲሆንልልን አንፈልግም፡፡
ጠላቶቻችንን የሚበቀል በተነሱብን ላይ ፈጥኖ የሚፈርድ እንዲሆን እንፈልጋለን
በድካም የሞተውን ወይም ዝም ያለውን ክርስቶስ እንደዚህች ሴት ለመፈለግ ፍቅራችን ምን ያህል የፀና ይሆን?????"
ሁሌም ደጋግሜሜሜ እራሴን እጠይቀዋለሁ😔😔😔😔
ትልቅ ይቅርታ🙏🙏 በመጠየቅ አሁን ከመፅሃፉ ጀባ ልላችሁ ተመኘሁ፡፡
@jahABP ነኘ
ብዘገይም አልቀርም ጠብቁኘ፡፡
መልካመ የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ😍😍😍
Post #1769
807