TGViewer
Channel ✦ Verified Channel
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

@ethpress

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Subscribers
24.8K
Photos
41.3K
Videos
346
Links
5.8K

Showing posts older than #46875 · Back to latest

Older Posts 10 shown
Post #46872 4.5K
የሕዳሴ ግድብን አንድ ሦስተኛ ኃይል የማመንጭት አቅም ያለው የኮይሻ ግድብ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ ደርሷል
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተገነባ የሚገኘውና የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል ተብሎ የሚጠበቀው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሽብር ባልቻ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለመገናኛ ብዙኃን ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ግድቡን በታቀደለት ጊዜ አጠናቆ ወደ ሥራ ለማስገባት በልዩ ትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

በሦስት ቢሊዮን ዩሮ ወጪ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ አፈጻጸሙ ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

የኮይሻ ግድብን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በከፊል ሥራ ለማስጀመር ግብ ተይዞ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብን አንድ ሦስተኛ ያህል ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ግድብ፣ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

የኮይሻ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ፣ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት ከመቀየር ባለፈ ለዘላቂ ልማት ትልቅ ምሰሶ እንደሚሆን ይጠበቃል።

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኮይሻ_ግድብ #ኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል #የውኃ_ኃይል_ማመንጫ #የሕዳሴ_ግድብ #የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ኢትዮጵያ
  • ❤ 8
Post #46869 3.13K
የጎቤ እና ሺኖዬ በዓል የአዲስ ዓመት ብስራት
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - የጎቤ እና የሺኖዬ በዓል የአዲስ ዓመት ብስራት የሚነገርበት የወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች ባህላዊ ጨዋታ መሆኑን የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ገለጹ።

የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታ በኦሮሞ ባህልና እሴት መሠረት ሊከበር የሚገባውና የዘመን መለወጫ ማብሰሪያ ባህላዊ ጨዋታ ነው።

ባህላዊ ጨዋታው ጥንታዊ የኦሮሞ ባህልና እሴቶችን የተከተለ መሆን እንዳለበት የጠቀሱት አባ ገዳ ጌቱ፤ ጎቤ እና ሺኖዬን ከባህላዊ እሴቱ ውጭ ለገቢ ማስገኛነት መጠቀም እንደማይቻል ተናግረዋል።

የጎቤ እና ሺኖዬ በዓል ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 ያሉ ልጃገረዶችና ወጣቶች ተሰባስበው የሚጫወቱት ባህላዊ ጨዋታ መሆኑን የገለጹት አባ ገዳው፤ በዓሉ ከጭጋጋማው የክረምት ወራት ወደ ፀደይ ብርሃን የመሸጋገሪያ ብስራት የሚበሰርበት መሆኑንም አብራርተዋል።

የዘንድሮው የጎቤ እና ሺኖዬ በዓል በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ እየተከበረ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ሀደ ሲንቄ ዘውዲቱ ጌታቸው በበኩላቸው፤ ጎቤ እና ሺኖዬ በመንገዶች ላይና ቤት ለቤት በመሄድ የአዲስ ዓመት ብስራት የሚነገርበት፣ እንዲሁም አንድነትና ፍቅር በአደባባይ የሚታይበት በዓል መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት በዓሉን ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚረዳ መሆኑንም ሀደ ሲንቄ ዘውዲቱ አክለው ተናግረዋል።

በማርቆስ በላይ

#ጋዜጣ_ፕላስ #ጎቤና_ሺኖዬ #የኦሮሞ_ባህል #የገዳ_ሥርዓት #ኦሮሚያ #ኢፕድ #ኢትዮጵያ
  • ❤ 1
Post #46868 3.49K
ቃል ሐሳብን ይቀርጻል፤ ሐሳብ ደግሞ ዓለምን ይለውጣል። ንግግሮች የጊዜን ወሰን ሰብረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የሕዝቦች የማንነት ማኅተምና የዘመን ምስክር ናቸው።

በመሪዎች መነጽር ሲታይ ቃል ቀላል ድምፅ ሳይሆን፣ ታሪክን የሚወስን፣ ማኅበረሰብን የሚቀይር እና ሀገርን የሚገነባ የኃይል ምንጭ ነው። በመሪዎች ቃል ውስጥ ህዝብ የሀገርን ተስፋና የመሪዎቹን ርዕይ እንዲቃኝ ያስችላል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዘጋጅነት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከ2017 እስከ 2018 ዓ.ም ያደረጓቸውን ንግግሮችና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶች «ከመስከረም እስከ መስከረም» በተሰኘው መጽሐፍ 8ኛ ቅጽ በይፋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

እርስዎም በመጽሐፉ ዘልቀው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያየ አቅጣጫ ሀገር ለማቅናት የተጓዟቸውን የዓመት ጉዞ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ቁልፍ ንግግሮችና ያስተላለፏቸውን አቅጣጫ ጠቋሚ መልዕክቶች ይቃኙ።

ሙሉ መጽሐፉን ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:-https://share.google/uTjPqcMG1OFDWj7Xq
#PMOEthiopia
  • ❤ 8
  • 😁 1
Post #46862 3.01K
ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 32 ነጥብ 3 በመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ 1ኛ ደረጃን መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ የዛሬ 12 ዓመት ያቋቋምነው የኦሮሚያ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ዘንድሮም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100% ማሳለፍ ችሏል።

ተማሪ ጃለላ ግርማ ኩሳ 591.6 ወጤት በማምጣት እንደ ሀገር ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ አንደኛ ወጥቷል።

በከተማ አስተዳደሩም የእቴጌ መነን የሴቶችና ገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 24 ትምህርት ቤቶች ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100 ፐርሰንት ማሳለፍ ችለዋል ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ ሳይንስ ከሴት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛው ውጤት 569.1 ያመጣችዉ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኘው ከቦሌ ሱፕር ሆሊ ሴቪየር ት/ቤት ተማሪ መቅደላዊት ሱራፌል ማሞ መሆኗንም ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣይ ከዚህ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመረውን ስትራቴጂ በአግባቡ መተግበር፣ የትምህርት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት፣ ወላጆች ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና ለትምህርት ልማት ስራው ስኬት ባለቤት ሆኖ መስራትና ተማሪዎች ለላቀ ውጤት መትጋት ይጠበቅባቸዋል።
  • ❤ 7
Post #46859 3K
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮው ማየት ይቻላል
- የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
+++++++++++

ጋዜጣ_ፕላስ- የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽበት አድራሻ ይፋ ማድረጉን የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ

በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል እንደሚችሉ አመልክቷል።

#Ethiopia #ExaminationResult #12Class #ExamResult #education #EthiopiaProgress
  • ❤ 1
Post #46858 3.61K
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
++++++++++++++++++

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ።

የነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ መክፈል፤ የተጠሩበትን ለሌሎች ማካፈል፤ የተጠሩበትን አክብሮ መኖር - እነዚህ ሁሉ ሺ መጻሕፍት የሚወጧቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

ነቢዩ የተጠሩበትን ዓላማ በሚገባ ስለተገነዘቡ አክብረው ኖረዋል፡፡ የተጠሩት ለተራና ርካሽ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የተጠሩት ትውልድን ለመቅረጽና ታሪክን ለመቀየር መሆኑን አምነዋል፡፡ ያንንም በቃላቸው፣ በሥራቸውና በኑሯቸው አክብረውት ነኖረዋል፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ተጠርተናል ብለን የምናምን ከሆነ ይህ የነቢዩ ሕይወት ታላቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡ የተጠራንበትን ዓላማ በንግግራችን፣ በሥራችንና በሕይወታችን እንግለጠው፡፡

ነቢዩ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ከቦታቸው ተሰደዋል፤ ምግብና መጠለያ ተነፍገዋል፤ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፡፡ ለሞት በሚያበቁ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአላህ ኃይል አሸንፈዋል፡፡ ክብር ያለ መከራ አይገኝምና፡፡ እውነተኛ ሰው ለዓላማው እንደ ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ)ዋጋ ይከፍላል፡፡ ዓላማው የሚያስገኘውን ክብርና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ዓላማው የሚያስከፍለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ይሆናል፡፡

ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ከአላህ የደረሳቸውን መልእክት ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፡፡ የተጠሩበትን ለሌሎች ለማካፈል ተግተዋል፡፡ መጀመሪያ በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በኋላም ለቅርብ ሱሐባዎች፣ በመጨረሻም ለዓለም መልእክቱን አዳርሰዋል ፡፡ እሳቸው የዘሩት ዘር እያፈራና እየጎመራ ተጉዟል፡፡ ዓላማችንን እኛ ማወቃችንና ማመናችን ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ልክ እንደነቢዩ ተገትተን መድከም አለብን፡፡

የነቢዩን መውሊድ ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፤ የተማርነውንም ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን እየተጠቀምን እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡ በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
  • ❤ 10
  • 😁 3
Post #46855 3.44K
አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ሪከርድን ሰበረ
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቦነስ አይረስ በተካሄደው ውድድር የግማሽ ማራቶን ሪከርድ ሰብሯል። አትሌቱ ርቀቱን በ56 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በማጠናቀቅ አዲስ የዓለም ሪከርድ አስመዝግቧል።

በዚህም አትሌት ዮሚፍ ዩጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ ከዚህ በፊት አስመዝግቦት የነበረውን 57 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ የዓለም ሪከርድ በ29 ሴከንዶች በማሻሻል የርቀቱ የዓለም ፈጣን አትሌት መሆኑን አረጋግጧል።

#WorldAthletics #TrackAndField #Athletics #TrackNation #DiamondLeague #World #Championships #DistanceRunning #TrackField #RoadToVictory
  • ❤ 14
  • 👍 3
  • 🔥 1
Post #46852 3.5K
ሀገራዊ ምክክሩ ለቀጣናው ሰላምና ዘላቂ ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዳለው ኡሁሩ ኬንያታ ገለጹ

+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- ሀገራዊ ምክክሩ ለቀጣናው ሰላምና ዘላቂ ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዳለው የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ገለጹ። ምክክሩ ብዝሃ ድምጾች የተሰሙበትና የሀገር ፍቅር ስሜት የተንጸባረቀበት እንደሆነም ጠቅሰዋል።

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሀገራዊ ምክክር የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት ምልክት ከመሆኗም በላይ "ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ የምትገኝ አገር ብቻ ሳትሆን የጥንታዊ የአፍሪካ ሥልጣኔ መገለጫም ናት" ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለሉዓላዊነቷና ለአንድነቷ በየጊዜው ያሳየችው ጥረት ለመላው አፍሪካውያን አብነት መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ታሪክ ቢሆንም የሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ድል መሆኑን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በባህል፣ በቋንቋ፣ በታሪክ፣ በሥልጣኔ እንዲሁም በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች አገር መሆኗን ገልጸው፤ ለአብነትም የአክሱም ሥልጣኔን፣ የታላቁን አባይ ወንዝ፣ የዓድዋን ድልና የልዩ ልዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ የዳኝነትና የአስተዳደር ሥርዓቶች ጠቅሰዋል።

«አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የመላው አህጉሪቱ መዲና ናት» ያሉት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት፤ የተካሄደው ሀገራዊ ምክክር በአገሪቱም ሆነ በቀጣናው ዘላቂ ሰላምና ዕድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል።
  • ❤ 11
  • 👍 2
  • 👏 2
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →