TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46869 3.14K
የጎቤ እና ሺኖዬ በዓል የአዲስ ዓመት ብስራት
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - የጎቤ እና የሺኖዬ በዓል የአዲስ ዓመት ብስራት የሚነገርበት የወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች ባህላዊ ጨዋታ መሆኑን የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ገለጹ።

የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታ በኦሮሞ ባህልና እሴት መሠረት ሊከበር የሚገባውና የዘመን መለወጫ ማብሰሪያ ባህላዊ ጨዋታ ነው።

ባህላዊ ጨዋታው ጥንታዊ የኦሮሞ ባህልና እሴቶችን የተከተለ መሆን እንዳለበት የጠቀሱት አባ ገዳ ጌቱ፤ ጎቤ እና ሺኖዬን ከባህላዊ እሴቱ ውጭ ለገቢ ማስገኛነት መጠቀም እንደማይቻል ተናግረዋል።

የጎቤ እና ሺኖዬ በዓል ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 ያሉ ልጃገረዶችና ወጣቶች ተሰባስበው የሚጫወቱት ባህላዊ ጨዋታ መሆኑን የገለጹት አባ ገዳው፤ በዓሉ ከጭጋጋማው የክረምት ወራት ወደ ፀደይ ብርሃን የመሸጋገሪያ ብስራት የሚበሰርበት መሆኑንም አብራርተዋል።

የዘንድሮው የጎቤ እና ሺኖዬ በዓል በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ እየተከበረ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ሀደ ሲንቄ ዘውዲቱ ጌታቸው በበኩላቸው፤ ጎቤ እና ሺኖዬ በመንገዶች ላይና ቤት ለቤት በመሄድ የአዲስ ዓመት ብስራት የሚነገርበት፣ እንዲሁም አንድነትና ፍቅር በአደባባይ የሚታይበት በዓል መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት በዓሉን ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚረዳ መሆኑንም ሀደ ሲንቄ ዘውዲቱ አክለው ተናግረዋል።

በማርቆስ በላይ

#ጋዜጣ_ፕላስ #ጎቤና_ሺኖዬ #የኦሮሞ_ባህል #የገዳ_ሥርዓት #ኦሮሚያ #ኢፕድ #ኢትዮጵያ
  • ❤ 1
More from @ethpress
  1. Sep 29, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል።…
  2. Sep 29, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ፦ ኢትዮጵያን በአንድ የተወሰነ ዘመን፣ በአንድ ጊዜያዊ ፈተና ወይም በ…
  3. Sep 29, 2026photo post
  4. Sep 29, 2026የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ትስስርና ለኢኮኖሚያዊ ውህደት +++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያና ጅ…
  5. Sep 26, 2026የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል +++++++++++++++++ በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ…
  6. Sep 26, 2026"ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር +++++++++ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →