TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46858 3.61K
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
++++++++++++++++++

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ።

የነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ መክፈል፤ የተጠሩበትን ለሌሎች ማካፈል፤ የተጠሩበትን አክብሮ መኖር - እነዚህ ሁሉ ሺ መጻሕፍት የሚወጧቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

ነቢዩ የተጠሩበትን ዓላማ በሚገባ ስለተገነዘቡ አክብረው ኖረዋል፡፡ የተጠሩት ለተራና ርካሽ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የተጠሩት ትውልድን ለመቅረጽና ታሪክን ለመቀየር መሆኑን አምነዋል፡፡ ያንንም በቃላቸው፣ በሥራቸውና በኑሯቸው አክብረውት ነኖረዋል፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ተጠርተናል ብለን የምናምን ከሆነ ይህ የነቢዩ ሕይወት ታላቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡ የተጠራንበትን ዓላማ በንግግራችን፣ በሥራችንና በሕይወታችን እንግለጠው፡፡

ነቢዩ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ከቦታቸው ተሰደዋል፤ ምግብና መጠለያ ተነፍገዋል፤ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፡፡ ለሞት በሚያበቁ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአላህ ኃይል አሸንፈዋል፡፡ ክብር ያለ መከራ አይገኝምና፡፡ እውነተኛ ሰው ለዓላማው እንደ ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ)ዋጋ ይከፍላል፡፡ ዓላማው የሚያስገኘውን ክብርና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ዓላማው የሚያስከፍለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ይሆናል፡፡

ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ከአላህ የደረሳቸውን መልእክት ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፡፡ የተጠሩበትን ለሌሎች ለማካፈል ተግተዋል፡፡ መጀመሪያ በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በኋላም ለቅርብ ሱሐባዎች፣ በመጨረሻም ለዓለም መልእክቱን አዳርሰዋል ፡፡ እሳቸው የዘሩት ዘር እያፈራና እየጎመራ ተጉዟል፡፡ ዓላማችንን እኛ ማወቃችንና ማመናችን ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ልክ እንደነቢዩ ተገትተን መድከም አለብን፡፡

የነቢዩን መውሊድ ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፤ የተማርነውንም ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን እየተጠቀምን እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡ በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
  • ❤ 10
  • 😁 3
More from @ethpress
  1. Sep 29, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ፦ ኢትዮጵያን በአንድ የተወሰነ ዘመን፣ በአንድ ጊዜያዊ ፈተና ወይም በ…
  2. Sep 29, 2026photo post
  3. Sep 29, 2026የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ትስስርና ለኢኮኖሚያዊ ውህደት +++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያና ጅ…
  4. Sep 26, 2026የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል +++++++++++++++++ በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ…
  5. Sep 26, 2026"ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር +++++++++ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ…
  6. Sep 24, 2026‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →