"የኮሪደር ልማት በርካታ በሥራ የተፈተኑ ኢንጂነሮችን ፈጥሯል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር በሥራ የተፈተኑ በርካታ ወጣት ኢንጂነሮችን በተግባር ማፍራት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
የኮሪደር ልማቱ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ግቦችን የያዘ መሆኑን ያነሱት ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ፕሮጀክቱ ወጣቶች ዩኒቨርሲቲ ገብተው ከሚያገኙት በላይ የተግባር እውቀት እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸዋል።
ወጣቶቹ የአዲስ አበባን ኮሪደር ከሠሩ በኋላ፣ በክልል ከተሞች ላይ መቶ በመቶ የራሳቸውን ዲዛይን በማውጣት ሠርተው ለማጠናቀቅ የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸውም አብራርተዋል።
የኮሪደር ልማቱ ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከገቢ ምንጭነት በተጨማሪ፣ የዕውቀትና የክህሎት ማዳበሪያ እንዲሁም የኢኖቬሽንና ፈጠራ ማጎልበቻ መሆኑን አክለው አስረድተዋል።
በልጅዓለም ፍቅሬ
++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ኮሪደር_ልማት #ኢንጂነሪንግ #አዲስ_አበባ #ወጣቶች #gazetteplus
Post #46304
2.69K

- ❤ 5