TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #47034 1.21K
መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሐብትን ይጠብቃል፣የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል። ይህ ዓይነቱ ሥራ ከሳተላይት ምልከታ ያለፈ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለፁት፣ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ለመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፤ ተቋሙ የተሟላ የአየር ትንበያ አገልግሎት በመስጠት ለሀገሪቱ ልማትና አቅም ወሳኝ ሥራዎችን የሚያከናውን የረጅም ዘመን እድሜ ያለው ተቋም ነው።

‎እንደ ኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማትን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ ነው። ግብርና፣ ውሃ፣ ጤና፣ አቪዬሽንና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎች የሚደገፉባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችና በመረጃ መሠረተ-ልማት ላይ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ ወሳኝ ነው።

በተለይም አደጋዎችን አስቀድሞ ለበተንበይ፣ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን፣ ወቅታዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንቀሳቀስ ለማድረግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች ያላቸው ጠቀሜታ አበረታቶኛል። አስተማማኝ መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሕይወትን ይታደጋል፣ ሐብትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል።

‎ይህ ዓይነቱ ሥራ ከሳተላይት ምልከታ ያለፈ ነው። ሥራው መረጃዎች ተሰብስበው፣ ተቀናብረውና ተተንትነው ወቅታዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያግዙ በመላ ሀገሪቱ ባሉ ጠንካራ የመረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎችና የመረጃ ማዕከላት መረብ ላይ ጭምር የተመሰረተ ነው።

ጉብኝቱ እየተለዋወጠ ያለውን የአየር ፀባይና የአየር ንብረት ሁኔታዎችን ለመረዳትና ምላሽ ለመስጠት ያለንን አቅም ለማጠናከር ሚቲዎሮሎጂያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የሳይንሳዊ ምርምርና የቴክኖሎጂ ዕድገት ያለውን የላቀ ጠቀሜታ ያረጋገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
‎
#የመደመርመንግሥት #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #Ethiopia #Tigray #Mekelle #peace
  • ❤ 4
More from @ethpress
  1. Oct 13, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተቋም አመራሮች ሹመት ሰጡ ++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (…
  2. Oct 13, 2026photo post
  3. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  4. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
  5. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
  6. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →