የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ
++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል።
የአየር መንገዱ አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ መቀሌ ከተማ አርፏል።
ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በረራ መጀመሩን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደስታቸውን እየገለጹ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።
#ትልቅ_ሀገር ፣ #ትልቅ_ህዝብ፣ #ታላቅ_ርዕይ
Post #47023
494

- 👍 2
- 👎 1