TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #47008 1.64K
በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ
++++++++++++++

#ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት አሃድ በማስረከብ ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፤ ኮሚሽኑ ከህዳር 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ በማቋቋም ወደ መደበኛ ሕይወት እንዲመለሱ አድርጓል።

መንግስት በትግራይ ክልል ከፍተኛ ሃብት በመመደብ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም በርካታ ስራዎችን ቢያከናውንም ህገወጡ የሕወሓት ቡድን በፕሪቶሪያው ስምምንት የፈረመውን ትጥቅ የማስፈታት ስምምነት በማፍረስ ወደ ተሃድሶ ማዕከል ለመግባት ፈቃደኛ የነበሩ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና እንዳይወስዱ ሲያደናቅፍ መቆየቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ወጣቶችን አስገድድዶ በማፈስ ለሌላ ጦርነት ሲያዘጋጅ እንደነበርም ነው የገለጹት።

በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ መንግስት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት የመልሶ ማቋቋም መርሃ ግብሩ እንዳይቋረጥ ሰፊ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ለሚመጡ የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ መደበኛ ሕይወት ለማስገባት መንግስት አሁንም በሩ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዚህም በትግራይ ክልል የሰላም መንገድን መርጠው ወደ ፌደራል መንግስት የሚመጡ በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም በትግራይ ክልል የቀደሞ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት አሀድ እያስረከቡ ወደ የተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡም ጥሪ አቅርበዋል።

ለዚህም መንግስት በርካታ ሃብት መድቦ ዜጎችን ወደ መደበኛ ሕይወት ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተቋቋመ ሲሆን፤ በግጭት ውስጥ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ማህበረሰቡ በዘላቂነት መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን የሚያከናውን ተቋም ነው።

#የመደመር_መንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ጋዜጣፕላስ
  • ❤ 4
  • 👏 3
More from @ethpress
  1. Oct 6, 2026photo post
  2. Oct 6, 2026የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ +++++++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- የናይጄሪያ ም…
  3. Oct 6, 2026#የመደመር_መንግሥት "በግንባርም፣ በሚዲያም፣ በሰይፍም በሰልፍም ፣ በውሸትም፣ በሀሜትም፣ በተንኮልም፣ በሽረባም፣ ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉ…
  4. Oct 6, 20268ቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፤ ✅ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የ…
  5. Oct 5, 2026ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) +++++++++++ ‎ ዛሬ የመደመር…
  6. Oct 5, 2026አዲስ የመንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል ++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- አዲስ የመንግሥት ምሥረታና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →