አዲስ የመንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል
++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- አዲስ የመንግሥት ምሥረታና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይካሄዳል።
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን ይደነግጋል።
የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ይታወቃል፡፡
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ
Post #46985
1.09K

- ❤ 2
- 👍 1