TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46977 1.24K
"የዘንድሮው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በስኬት ተጠናቅቋል"
- የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ በሆራ ሀርሰዴ የተከበረው የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ መጠናቀቁን የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ገለጹ።

አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ የበዓሉን መጠናቀቅ ተከትሎ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በሆረ ፊንፊኔና በሆረ ሀርሰዴ በልዩ ሁኔታ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት በመሆን ባህሉን በጠበቀ መልኩ ወደ ስፍራው በማቅናት ፈጣሪውን አመስግኗል። መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በቦታው ተገኝተው በአንድነት ማክበራቸውንም ጠቁመዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው፤ የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያ በዓል ከመሆን ተሻግሮ ዓለም አቀፍ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።

ወደ ኢሬቻ ማክበሪያ ቦታ ይወስድ የነበረውን አንድ መንገድ ወደ ሦስት ማሳደግ መቻሉ ለዘንድሮው በዓል ልዩ ድባብ እንደሰጠው የገለጹት ከንቲባው፤ በከተማዋ የተከናወነው የኮሪደር ልማትም በዓሉ ያለምንም መገፋፋት በድምቀት እንዲከበር እንዳስቻለ ገልጸዋል።

በዓሉ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ዓለም አቀፍ ዜጎች መታደሙን ጠቁመው፤ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዮሐንስ መልካሙ (ከቢሾፍቱ)

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢሬቻ #ሆራ_ሐርሰዴ #ቢሾፍቱ #አባ_ገዳ #ባህል #ኢትዮጵያ #Irreecha #Horafinfinnee #Horaharsadee #Irreecha #Irreechaa #festivity #celebration #holiday #holidayseason
  • ❤ 5
More from @ethpress
  1. Oct 4, 2026photo post
  2. Oct 4, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ #ጋዜጣ_ፕላስ #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  3. Oct 3, 2026https://youtu.be/oXi2-SwdwbY
  4. Oct 3, 2026የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ም…
  5. Oct 3, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →