የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
+++++++++++++++++++
#ጋዜት_ፕላስ- የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
በቆይታቸው መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ። በልማት ዘርፎች የልምድ ልውውጥ ማድረግና ቁልፍ ተቋማትንና ልማቶችን እንደሚጎበኙ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
#የመደመር_መንግሥት #Ethiopia #Nigeria #NigeriaEthiopiaRelations #Diplomacy #AddisAbaba
Post #47004
1.4K



- ❤ 1