“ከተሞች የሀገር መኳያ እና የአብሮነት ቤተሙከራዎች ናቸው”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ከተሞች የሀገር መኳያ፣ የስልጣኔ መስታወት እና የአብሮነት ቤተ-ሙከራዎች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተሞች በአዲስ ምናብ በሚል ርዕሰ ጉዳይ የኢትዮጵያ የከተማ ልማት የለውጥ ሥራዎችን በተመለከተ ከቃና ቴሌቭዥን ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ቆይታ እንዳሉት፣ ቀደም ሲል ከተሞችን እንደ ስጋትና ነዋሪዎቻቸውን እንደ ወላዋይ የመመልከት የተሳሳተ ዝንባሌ ተቀይሮ፣ አሁን ላይ ከተሞች የሀገር ዕድገት መለኪያና የስልጣኔ መስታወት ተደርገው በትኩረት እየተሠራባቸው ነው፡፡
ከተሞች የሀገር "እጅና አእምሮ" የሆኑና ግማሹ የሀገር ኢኮኖሚ የሚንቀሳቀስባቸው በመሆኑ፣ ከተማን ያገለለ የብልጽግና ጉዞ ሊሳካ እንደማይችል አስረድተዋል።
ከተሞች ለዘመናዊ ፈጠራ፣ ለውጥና ቀልጣፋ አሠራር መገኛ ከመሆናቸው ባለፈ፣ የአንድ ሀገር ስልጣኔና ዕድገት የሚለካው በከተሞቿ ውበትና ስልጣኔ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
ከተማ ከተለያየ አካባቢ የመጡ ዜጎች በቋንቋ፣ በባህልና በሃይማኖት ሳይገደቡ በጋራ የሚኖሩባትና አብሮነት በተግባር የሚታይባት ስፍራ በመሆኗ፣ ሀገርን ለመገንባት እንደ ትልቅ መነሻ እንደምትወሰድም አክለዋል።
የከተማ ነዋሪ ለለውጥ ዝግጁ፣ ጥሮ ግሮ ለመለወጥ የሚተጋና ችግር ፈቺ በመሆኑ፣ መንግሥት የከተማውን ነዋሪ እንደ ዋና ማኅበራዊ መሠረት በመውሰድ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
ከተሞች የሀገር መኳያ መገለጫ በመሆናቸው፣ እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከተሞችን ውብ በማድረግ የሀገርን ክብርና ውበት ከፍ ለማድረግ የተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡
Post #46303
2.33K

- ❤ 4