TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46248 2.45K
“የትግራይ ወጣቶች ጦርነት በቃን የሚል ድምጽ እያሰሙ ነው”

- አቶ ጌታቸው ረዳ
++++++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች የኋላቀር ቡድኑን የጦርነት ጉሰማ "በቃን" በሚል ድምፅ እየተቃወሙት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

አቶ ጌታቸው አዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ወጣቶች ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፤ ትግራይ ውስጥ ያለው ወጣት አሁንም ጦርነት በቃን የሚል ድምፁን እያሰማ በመሆኑ፣ ጦርነት የሚሰብከውን ኋላቀር ቡድን "ሰላም" በሚል ቃል ልናሸንፈው ይገባል።

ባለፉት 30 ዓመታት ጦርነትን በመሸሽ የተጀመረው ስደት ወጣቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሄዱ ማድረጉን ያስታወሱት አማካሪው፤ አሁን ባለው ሁኔታም በትግራይ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ተሰድደው ለማለቅ ሦስት ዓመት የሚፈጅባቸው እንደማይመስል በመግለጽ የሁኔታውን አሳሳቢነት አብራርተዋል።

ውይይት መፍትሔ ማስገኛ ዘዴ ቢሆንም ወደ ተግባር ካልተቀየረ ልምድ ሆኖ እንደሚቀር የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፤ የተደራጁ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ በጦርነት ቀስቃሾች ላይ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ ጌታቸው በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ማንኛውንም ፓርቲ ወይም አደረጃጀትን ወክለው ሳይሆን፤ ትግራይን በማዳኑ ሂደት የሁሉም ድርሻ አስፈላጊ መሆኑን ስለሚያምኑ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጦርነትን አንፈልግም የሚለው የወጣቶች ድምፅ መቐለ መሽጎ ጦርነት የሚሰብከውን ቡድን ሊያስደነግጠው እንደሚችል የገለጹት አማካሪው፤ ወጣቱ ድምፁን ይበልጥ ማሰማትና ለሰላም መደራጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በሔርሞን ፍቃዱ
+++++++++++++++++++

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ #ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰላም #ጦርነት_በቃን #ጌታቸው_ረዳ #ኢትዮጵያ
  • ❤ 3
  • 😁 1
More from @ethpress
  1. Oct 13, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተቋም አመራሮች ሹመት ሰጡ ++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (…
  2. Oct 13, 2026መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሐብትን ይጠብቃል፣የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) +++++++…
  3. Oct 13, 2026photo post
  4. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  5. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
  6. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →