TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46242 2.77K
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Photo
“ወድቆ መቅረት የለም”፤ ከሥልጣን እስከ መቄዶንያ
+++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ሕይወት እንዲህ ናት፤ ከፍታን በቀኟ ከያዘች በግራዋ ዝቅታን ይዛ እንካችሁ ማለት ልመዷ ነው።
ይህ አባባል የቀድሞው ባለስልጣን አሁን በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት የአቶ መላኩ አሰፋ የሕይወት ምስክርነት ሊሰጡበት የሚያስችል ነው።
አቶ መላኩ አሰፋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ሲወጡ ትልቅ ራዕይ አንግበው ነበር የወጡት።
በኢትዮጵያ ማዕድን ሀብት ልማት ኮርፖሬሽን ውስጥ ለ10 ዓመታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። የኢትዮጵያን ሠራተኞች ኮንፌዴሬሽንን በምክትል ፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን ወክለው ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሚኒስትሮች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተደራድረዋል፤ ተወያይተዋል።
የሰው ልጅ ሕይወት ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለምና በኋላ ግን የአቶ መላኩ ሕይወት በዚህ ልትቀጥል አልቻለችም።
አቶ መላኩን ከባድ የአዕምሮ ሕመም ገጠማቸው። ያ ሁሉ ዝና፣ ያ ሁሉ ሥልጣንና እውቀት በሕመሙ ጥላ ሥር ተሸፈነ።
በአንድ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚሟገቱት ግለሰብ፣ ሕመም አሸንፏቸው ጎዳና ላይ ለመውደቅ በቁ።
ከውድቀትም በኋላ ትንሳኤ ከሕመምም በኋላ ፈውስ አለና አቶ መላኩ በሕመሙ ተሸንፈው አልቀሩም። ወደመቄሄዶንያ ገቡ፡፡
በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር ባገኙት ፍቅር፣ እንክብካቤና ሕክምና ዳግም ለመወለድም ታደሉ። አእምሯቸው ተመልሶና ማንነታቸውን መልሰው በማግኘት ዛሬ ለመቄዶንያ ትልቅ ውለታ እየመለሱ ይገኛል።
በአሁኑ ጊዜ አቶ መላኩ በመቄዶንያ ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያና የስክሪፕት ጸሐፊ ናቸው።
በፋና እና በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚተላለፉ የመቄዶንያ የአየር ሰዓቶች ላይ ከ70 በላይ ስክሪፕቶችን አዘጋጅተዋል። በተጨማሪም ዶክመንተሪዎችንና ቃለ መጠይቆችን በብቃት ያከናውናሉ።
አቶ መላኩ መቄዶንያ ከበጎ አድራጎት ማኅበርነት አልፎ ወደ "ቻሪቲ ቪሌጅ" (Charity Village) እንዲያድግ የራሳቸውን ሙያዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ያስረዳሉ።
"መቄዶንያ የኢትዮጵያውያን የበጎነት ጥግ የታየበት፣ የሀገርን ሸክም የተሸከመ ተቋም ነው" ሲሉ መቄዶንያን ይገልጹታል።
"እኔ ድኜ ዛሬ እዚህ ሥራ ላይ ብገኝም፣ ነገ ለማንም ምን እንደሚመጣ አይታወቅም። ስለዚህ ሰውን አትናቁ፣ መቄዶንያን ደግሞ ደግፉ" ሲሉም መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ።
በክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ የተመሰረተው መቄዶንያ እንደአቶ መላኩ አይነት በርካታ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፉ ግለሰቦችን ያስጠለለ ተቋም ነው፡፡
ተቋሙ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልል ከተሞችም ቅርንጫፎችን ከፍቶ ሰውን ከጎዳና እያነሳ እየጦረ ይገኛል፡፡
መቄዶንያ ከመጋቢት 6 ጀምሮ የገበያ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህም ተቋሙ ለጀመረው ባለ 15 ወለል ሆስፒታል እና በክልል ከተማ እየተገነቡ ላሉ ቅርንጫፎች ማስጨረሻ የሚሆን ነው፡፡
መላው ኢትዮጵያውያንና ሌሎችም በገቢ ማሳባሰቢያው በመሳተፍ ተቋሙን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በሄለን ወንድምነው
  • ❤ 9
  • 👏 2
  • 🥰 1
More from @ethpress
  1. Oct 13, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተቋም አመራሮች ሹመት ሰጡ ++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (…
  2. Oct 13, 2026መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሐብትን ይጠብቃል፣የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) +++++++…
  3. Oct 13, 2026photo post
  4. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  5. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
  6. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →