ቦርዱ ባደረገው ማጣራት የፓርቲ አባል በሆኑ የምርጫ አስፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ወሰደ
+++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የምርጫ አስፈጻሚዎች ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ነፃ መሆን ያለባቸው ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባደረገው ማጣራት የፓርቲ አባል ሆነው በተገኙ አስፈጻሚዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዛሬ ማምሻውን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ ቦርዱ ምርጫው ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን በትኩረት እየሠራ ይገኛል። በዚህም መሠረት በተደረገ ማጣራት የፓርቲ አባል መሆናቸው የተረጋገጠባቸው አስፈጻሚዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።
እርምጃ ከተወሰደባቸው ግለሰቦች መካከል ከፓርቲ አባልነት ባለፈ የፓርቲ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ጭምር እንደሚገኙበት ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል።
ቦርዱ በማጣራት ያገኛቸውን እነዚህን ግለሰቦች ከአስፈጻሚነት ያሰናበተ ሲሆን፤ የማጣራት ሥራውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ፓርቲዎች የምርጫውን ሂደት የሚታዘቡላቸውን ወኪሎች እንዲልኩ ጥሪ ተደርጎ ባጅ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ እስካሁን ወኪሎቻቸውን የላኩት ውስን ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸውን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።
ቦርዱ በሂደቱ የሚያጋጥሙ ማንኛውንም ችግሮች ለመፍታት ከቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ያሉ አሠራሮችን እንደሚጠቀም ተናግረዋል።
በልጅዓለም ፍቅሬ
+++++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ጋዜጣ_ፕላስ #ምርጫ_2018 #ምርጫ_ቦርድ #ገለልተኝነት #ኢትዮጵያ #ምርጫ_አስፈጻሚ
Post #46230
2.36K

- 👍 4