TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46223 2.61K
“የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የሀገር ሕልውና ጉዳይ እንጂ ጠብ አጫሪነት አይደለም” - የዓለም አቀፍ ንግድ ከፍተኛ ጠበቃና አማካሪ
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የሀገር ሕልውና ጉዳይ እንጂ ጠብ አጫሪነት አይደለም ሲሉ በለንደን የዓለም አቀፍ ንግድ ከፍተኛ ጠበቃና አማካሪ ሀማድ ቤይግ ገለጹ፡፡

ሀማድ ቤይግ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ኢኮኖሚያዊ አስፈላጊነትና የሀገር ሕልውና ጉዳይ እንጂ ጠብ አጫሪነት አይደለም።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋ መልስ እንዲገኝ በሕግና በድርድር የተደገፈ መፍትሄዎችን እንደምትከተል የገለጹት ሀማድ፤ የባሕር በር በኃይል አማራጭ ልታገኝ ነው የሚለው ኢ-ምክንያታዊ ነው።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን ባነሳች ማግስት ጸብ አጫሪ አድርገው ሊመለከቷት የፈለጉ ሀገራት መኖራቸውን ጠቅሰው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰላማዊ እና በሕጋዊ ድርድር የባሕር በር ለማግኘት ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ታሪክን፣ መልክዓ ምድርንና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይን መሰረት በማድረግ የባሕር በር ጥያቄ የማንሳት መብት አላት። የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፍ ሕጎችን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በየትኛውም መመዘኛ ፍትሃዊነት ያለው ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ይፋዊ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በዲፕሎማሲ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመግለጽ፤ ኢትዮጵያ ወደ ግጭት የመግባት ፍላጎትም ዝግጅትም እንደሌላት ማረጋገጧን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ለመሆን እያነሳች የምትገኘው ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኝ መስራት እና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የሀገራትን ድጋፍ ለማግኘት መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

በኢማኑኤል ጆርጌ
#ባህር_በር #ኢትዮጵያ #gazette_plus
  • ❤ 9
  • 👍 3
More from @ethpress
  1. Oct 16, 2026የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ተመሠረተ ++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የፌዴ…
  2. Oct 13, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተቋም አመራሮች ሹመት ሰጡ ++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (…
  3. Oct 13, 2026መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሐብትን ይጠብቃል፣የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) +++++++…
  4. Oct 13, 2026photo post
  5. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  6. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →