የሀገር ጉዳይ አይሸጥም ብሎ የሚያምን ህዝብ የባህር በር ጥያቄን እውን የሚያደርግበት ጊዜ ቅርብ ነው
++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | “የሀገር ጉዳይ አይሸጥም፤ አይለወጥም” ብሎ የሚያምን ህዝብ ያላት ሀገር የባህር በር ጥያቄን እውን የሚያደርግበት ጊዜ ቅርብ ነው ሲሉ የታሪክ ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ተናገሩ፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ለጋዜጣ ፕላስ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በዓመት ለወደብ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና እየተዳረገች ነው፡፡
60 ኪሎ ሜትር ብቻ የሚርቅ የባህር በር እያለ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለኪራይ ማውጣት አግባብ አይደለም የሚሉት የታሪክ ተመራማሪው፤ ጥያቄውም የ130 ሚሊዮን ህዝብ ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡
የታሪክ ተመራማሪው ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ንጉስ ናት፡፡ የህዝቡ ጥያቄ ያለአግባብ ያጣነው የባህር በር ወደ ባለቤቱ ይመለስ የሚል ነው፡፡ ይህም ተቀባይነት ያለው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሴራ ያጣነውን የባህር በር መልሶ ለማግኘት በአንድነት መቆም እንደሚገባ በመግለጽ፤ የባህር በር ጥያቄው በሰላማዊና በበሳል የዲፕሎማሲ መንገድ መፈታት እንዳለበት አሳስበዋል።
የባህር በር ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጠናው ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ያሉት ተመራማሪው፤ የቀይ ባህር ሰላም መሆን ለገልፍ ሀገራት ጭምር ወሳኝ በመሆኑ በድርድር መፈታቱ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን በአድዋ ጦርነትና በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ያሳዩትን የማይበገር አንድነት፣ አሁንም ለሀገሪቱ የባህር በር ጥያቄ ስኬታማነት ሊደግሙት ይገባል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባለቤት እንድትሆን የሚከለክላት የታሪክም ሆነ የፍትህ ምክንያት የለም እንደለሌለም አመለክተዋል፡፡
በታደሠ ብናልፈው
Post #46217
2.47K

- 👍 2