“የካራማራ ድል የኢትዮጵያ ታላቅነት ማሳያ ነው”
- በኢትዮ- ሶማሊያ ጦርነት የፓራኮማንዶ ብርጌድ አዛዥ
+++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የካራማራ ድል መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሀገሩ ነፃነት ያለውን ፍቅርና ታላቅነት በተግባር ያሳየበት የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን በኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት የአንደኛ የፓራኮማንዶ ብርጌድ አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማሪያም ገለጹ።
ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማሪያም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ በወቅቱ የነበረው የጦር ሁኔታ ተመጣጣኝ ባልነበረበትና ሀገሪቱ በውስጥ ችግሮች ተወጥራ በነበረችበት ወቅት ወራሪውን የሶማሊያ ኃይል በአጭር ጊዜ ዝግጅት ድል ማድረግ መቻሉ ተአምራዊ ነበር።
ሶማሊያ ጅግጅጋ ለመድረስ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ብትገሰግስም፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ካራማራ ላይ ባደረገው ተጋድሎና ምሽግ በመያዝ የጠላትን ጉዞ መግታት መቻሉን አውስተዋል።
የክተት አዋጁን ተከትሎ ከ120 ሺህ በላይ ሕዝብ በ48 ሰዓታት ውስጥ ታጠቅ ጦር ሰፈር በመክተት ያሳየው ወገንተኝነት የድሉ መሠረት መሆኑን ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ገልጸዋል።
በወቅቱ ሐረርና ድሬዳዋን ከመከላከል ባለፈ፣ የወገን ጦር ባደረገው ከፍተኛ ጥቃት ጠላት ተሸንፎ እስከ ሐርጌሳ እንዲገባ መደረጉንና በኦጋዴን አካባቢዎች የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዳግም መውለብለቡን ተርከዋል።
ትውልዱ ከዚህ የታሪክ አጋጣሚ በመማር፣ ለሀገር ሉዓላዊነትና ሰላም ዘመናዊና በሚገባ የሠለጠነ የሰው ኃይል ያለው ሠራዊት የመገንባት አስፈላጊነትን ሊገነዘብ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በበኃይሉ አበራ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ካራማራ #ኢትዮጵያ #የካራማራ_ድል #ሶማሊያ #ታሪክ #ተስፋዬ_ሀብተማሪያም #ሉዓላዊነት
Post #46179
2.14K

- 👍 6
- ❤ 2