የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግ የዘመናችን ዓድዋ ነው
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የዘመናችን የዓድዋ ድል ተደርጎ የሚቆጠር መሆኑን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ሰለሞን ተፈራ ገለጹ።
ምሁሩ ሰለሞን ተፈራ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የዓድዋ ድል የሀገሪቱን የግዛት ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተደረገ ታላቅ ተጋድሎ እንደነበረ ሁሉ፣ እውነተኛ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው ደግሞ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነፃነት ማረጋገጥ ሲቻል ነው።
የባሕር በር ማጣት ኢትዮጵያን የጂኦግራፊ እስረኛ በማድረግ የኢኮኖሚ ነፃነቷን እንደሚገድብ የጠቀሱት ምሁሩ፣ ይህንን ጥያቄ መፍታት የዘመናችን የዓድዋ ድል ተደርጎ እንደሚወሰድ አስረድተዋል።
እንደ ሰለሞን ማብራሪያ፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በዓድዋ መንፈስና በአንድነት በመቆማችን የተመዘገበ ሁለተኛው የዓድዋ ድል ነው።
በተመሳሳይ የባሕር በር ጉዳይም መላው ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመው ሊያሳኩት የሚገባ ብሔራዊ አጀንዳ መሆኑን ጠቁመዋል።
አየር መንገድ ያስጀመረው አዲስ አየር ማረፊያ እና የኒውክሌር ኃይል ግንባታ ጥረቶችም የአባቶቻችንን የፖለቲካ ድል በኢኮኖሚ በማጀብ የሀገርን ክብር የሚያጸኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።
በፋንታነሽ ክንዴ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ዓድዋ_ድል #ኢትዮጵያ #የባሕር_በር #ሉዓላዊነት #ኢኮኖሚ #ሰለሞን_ተፈራ
Post #46168
2.65K

- ❤ 4
- 👍 3