TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.7K subscribers
Post #46137 2.17K
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ130ኛው የዐድዋ ድል በዓል ያስተላለፉት መልዕክት
++++++++++++
የዐድዋ ድል የኢትዮጵያውያንን የማይቀየር ዐቋምና ዐቅም ያሳየ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅም፣ ነጻነትና ሉዓላዊነት ላይ የማይቀየር ዐቋም አላቸው። ይሄንን ዐቋማቸውን በጽኑ መሠረት ላይ ለመትከል ደግሞ ሁሉንም አቅማቸውን ይጠቀማሉ።

ሥርዓታትና መሪዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፤ በአንዳንድ ጉዳዮች ልዩነቶች ይኖሯቸው ይሆናል፤ ስለ ሀገራቸው ያላቸው ዐቋምና ለሀገራቸው የሚያወጡት አቆም ግን አይቀየርም።

ወደ ዐድዋ የዘመቱ ጀግኖቻችን ሁሉ በሁሉም ነገር የተስማሙ አይደሉም። አንድ ዓላማ ነበራቸው እንጂ አንድ ዓይነት አልነበሩም። አንድ ሀገር ነበራቸው እንጂ አንድ ባህልና እምነት አልነበራቸውም።

በዚያ ጊዜ ሀገራቸውን ከድተው ከጠላት ጋር ያበሩ ባንዳዎች ነበሩ። ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ ዘላቂ የሀገራቸውን ጥቅም የሸጡ ምንደኞችም ነበሩ። ከባዳ ጋር ወግነው ወገናቸውን ያስማሙ ደላሎችም ነበሩ።

ጀግኖች እናቶቻችን እና አባቶቻችን የተዋጉት ከወራሪው የጣሊያን ጦር ጋር ብቻ አልነበረም። ከምንደኞች፣ ከባንዳዎች እና ከሀገር ደላሎች ጭምር እንጂ። ዐርበኝነት ማለት ባዳና ባንዳን ማሸነፍ ማለት ነው። ዐርበኝነት ማለት ለሀገር ጥቅም ሲባል የግል ጥቅምን ማሸነፍ ማለት ነው። ዐርበኝነት ማለት ለሀገር ክብር ሲባል የራስን ክብር መሠዋት ነው።

የዐድዋ ድል በዓል እነዚህን ሁሉ የምናስታውስበት ነው። የዐድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያንን ዐቅምና አቋም እንደገለጠው ሁሉ ዛሬም በጸና አቋም፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዐቅም የምንገልጥበት ጊዜ ነው። በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን እና በዲጂታል ሀገራችን ያላትን ዐቅም መግለጥ አለብን። የዐድዋን ድል በሁሉም ዘርፍ ለመድገም፣ የኢትዮጵያ ዐቅም ጽኑ መሠረት ሊኖረው ይገባል።

ሀገርን ዐቅም ያሳድጋታል፤ ዐቅም ይገነባታል። ሀገርን ዐቅም ይሠራታል። ዐቋም ያጸናታል። ሀገርን ዐቅም ያራምዳታል፤ ዐቋም ያሻግራታል።

የዐድዋ ድል በዓላችን የኢትዮጵያን ዐቅም ይበልጥ የምንገነባበትና የኢትዮጵያውያንን ዐቋም ይበልጥ የምናጸናበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
  • ❤ 7
More from @ethpress
  1. Oct 16, 2026የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ተመሠረተ ++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የፌዴ…
  2. Oct 13, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተቋም አመራሮች ሹመት ሰጡ ++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (…
  3. Oct 13, 2026መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሐብትን ይጠብቃል፣የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) +++++++…
  4. Oct 13, 2026photo post
  5. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  6. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →