TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.7K subscribers
Post #46084 2.68K
በአሜሪካ የምሥራቃዊ ግዛቶች በጣለው ከባድ በረዶ ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰረዙ
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በአሜሪካ የምሥራቃዊ ግዛቶች በጣለው ታሪካዊና ከፍተኛ የበረዶ ዝናብ ምክንያት ከ5 ሺህ 700 በላይ በረራዎች መቋረጣቸውንና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፍተኛ የትራንስፖርት መስተጓጎል መዳረጋቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ የአየር ንብረት አገልግሎት (NWS) አስታወቀ።

የብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት እንዳስታወቀው፤ በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ የተከሰተው ከባድ ማዕበል፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የበረዶ ዝናብ በማምጣቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለችግር ዳርጓል፡፡

በምስራቃዊ የባህር ዳርቻ የሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ ቤቶች እና የንግድ ተቋማት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ሲሆን፣ ኒው ጀርሲ እና ማሳቹሴትስ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል።

በአንዳንድ የሮድ አይላንድ እና የማሳቹሴትስ ክፍሎች ወደ 37 ኢንች (94 ሳ.ሜ) የሚጠጋ የበረዶ ዝናብ፤ በኒውዮርክ ሲቲ ሴንትራል ፓርክ ደግሞ ከ19 ኢንች በላይ በረዶ ወርዶ የታዬ ሲሆን የኒውዮርክ ግዛት የአደጋ ጊዜ ቢሮም የጣለው በረዶ "ለጉዞ የማይቻል" ሁኔታ ፈጥሯል ብሏል፡፡

የማሳቹሴትስ አስተዳዳሪ ማውራ ሄሊ (ገዥ) በሰጡት መግለጫ፣ መንገዶች እጅግ አደገኛ በመሆናቸውና የነፍስ አድን ሠራተኞች ለመድረስ ስለሚቸገሩ ዜጎች ከቤታቸው እንዳይወጡ በጥብቅ አሳስበዋል።

"ኋይት-አውት" (White-out) በተሰኘው እጅግ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት አሽከርካሪዎች መንገዱን ማየት የማይችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ከአውሮፕላን በረራ ክልከላ በተጨማሪ ከአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎቶች ውጭ ማንኛውም የየብስ ጉዞ እንዳይደረግም እገዳ ተጥሏል።

የክረምት ማዕበል ማስጠንቀቂያ ከሰሜን ካሮላይና እስከ ሰሜናዊ ሜይን ድረስ የተዘረጋ ሲሆን፣ አንዳንድ ማስጠንቀቂያዎች ደግሞ በምስራቃዊ ካናዳ ክፍሎችም ጭምር ተሰጥተዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

በታደሠ ብናልፈው

++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት @ጋዜጣ-ፕላስ #ጋዜጣ_ፕላስ #አሜሪካ #የበረዶ_ማዕበል #በረራ #ኒውዮርክ #ሮድ_አይላንድ
  • ❤ 7
  • 👍 1
More from @ethpress
  1. Oct 16, 2026የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ተመሠረተ ++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የፌዴ…
  2. Oct 13, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተቋም አመራሮች ሹመት ሰጡ ++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (…
  3. Oct 13, 2026መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሐብትን ይጠብቃል፣የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) +++++++…
  4. Oct 13, 2026photo post
  5. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  6. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →