የትግራይ ወጣት የተደቀነውን አጥፊ ጦርነት በማክሸፍ ሰላም እንዲያሰፍን ጥሪ ቀረበ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የታጠቀውም ሆነ ያልታጠቀው የትግራይ ወጣት የተጋረጠውን አጥፊ ጦርነት በመቃወም እጁን ለሰላም እንዲዘረጋ የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ጥሪ አቀረቡ።
ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በክልሉ የተጋረጠውን የጦርነት ሥጋት ማስቀረት የሚቻለው ጦርነትና እልቂትን "እምቢ" በማለትና በአንድነት በመሰለፍ ብቻ ነው።
ወጣቱ ዓላማ ቢስ ወደሆነ ጦርነት ከመግባት ይልቅ የመኖር መብቱን ሊያስጠብቅ እንደሚገባ ያሳሰቡት ወይዘሮ ኬርያ፤ የታጠቀው ወጣትም "ለማን ዓላማና ምኞት ነው ሕይወቴን የምገብረው?" ብሎ ራሱን ሊጠይቅ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የተሳሳተ የትግራይ ወጣት ማለት ከታሪካዊው የሕዝብ ጠላት ሕወሓት ጋር ተሰልፎ ጥቁር ታሪክ ለማስመዝገብ የሚዘጋጅ መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ኬርያ፤ ወጣቱ በስሜት ሳይሆን በብስለትና በስሌት በመራመድ ሕዝቡንና ሀገሩን ከጥፋት ሊታደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አሁን ላይ የዳግም ጦርነት ሥጋት መግዘፉን ጠቁመው፤ ይህንን ጥፋት በምኞት ሳይሆን ጦርነትን በመጸየፍና በሰላማዊ መንገድ በመታገል ብቻ ማስቀረት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
በሔርሞን ፍቃዱ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰላም #ወጣቶች #ኬርያ_ኢብራሂም #ኢትዮጵያ #ጦርነትን_አይሆንም
Post #46081
2.23K

- ❤ 7
- 👎 1