TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46078 2.21K
ኢንስቲትዩቱ በከተሞች የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በዘንድሮው የበልግ ወቅት በሚኖረው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በከተሞች የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በበልግ ወቅት ከሚኖረው ከፍተኛና ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ ዝናብ የተነሳ በተለይም በቆላማ ስፍራዎችና በከተሞች ቅጽበታዊ ጎርፍ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው።

አዲስ አበባን ጨምሮ በደቡብና ምሥራቅ ትግራይ፣ በምሥራቅ አማራ፣ በአፋርና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እንደሚጠበቅ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ በጉጂ፣ በቦረና፣ በሲዳማና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስከ 55 በመቶ የሚደርሰው ዓመታዊ የዝናብ መጠን የሚስተዋለው በዚህ ወቅት መሆኑን አሳምነው (ዶ/ር) አስረድተዋል።

የበልግ ዝናብ ተለዋዋጭነቱ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ችግሩን ለመከላከል የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ማከናወንና ኢንስቲትዩቱ የሚያወጣቸውን የትንበያ መረጃዎች በመጠቀም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በአማን ረሺድ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ሚቲዎሮሎጂ #ጎርፍ #ከተሞች #ዝናብ #የበልግ #አካባቢ_ጥበቃ
  • ❤ 1
More from @ethpress
  1. Oct 16, 2026የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ተመሠረተ ++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የፌዴ…
  2. Oct 13, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተቋም አመራሮች ሹመት ሰጡ ++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (…
  3. Oct 13, 2026መረጃ ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየር ሐብትን ይጠብቃል፣የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) +++++++…
  4. Oct 13, 2026photo post
  5. Oct 12, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐ19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ++++++++++ ‎ ‎“ሠን…
  6. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →