TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #2033 · Back to latest

Older Posts 18 shown
Post #2031 591
ዛሬ ሰማይ ላይ ይህን ያስተዋለ
Post #2030 690
𝐀𝐁 𝐏𝐇𝐎𝐓𝐎𝐆𝐑𝐀𝐏𝐇𝐘 & 𝐆𝐑𝐀𝐏𝐇𝐈𝐂 𝐃𝐄𝐒𝐈𝐆𝐍

ቀጣይ ክፍል

መፅሐፍ ቅዱስ እራሱ ሰማያት በፊቱ ንጹህ አይደሉም ብሎ ይነግረናል፡፡ ስለዒህ ሰማያት ሳይቀሩ በደካማነት በተነፀሩበት የእግዚአብሔር ቅድስና ስንመረምር ማድረግ የምንችለው እግዚአብሔር እያንዳንዱን ምላስ ፀጥ እንዲያሰኘ እና እኔ ጥቁር ነኘ ለሚለው ቃል ጆሮ እንዲሰጥልን መለመን ብቻ ነው፡፡

ይሁንና እያንዳንዱን ኃጢያት በሚያጥበው በእየሱስ ክርስቶስ ደም እኔ ውብ ነኘ፡፡ ይህ ሁሉ ጥቁረት ቢኖርብኘም ያማረውን ፈትል ያለብሰኛል ንፁህና ነጭ የሆነውን ልብስ ይሰጠኛል ክቡር ሥጋውን እንድመስል የተዋረደውን ስጋዬን ይለውጣል፡፡

በጎ ምግባሮቻቸውን እስከ ፍፃሜ ላደረሱ ለነዛ ቅዱሳን ይህ ይገባቸዋል፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን አንዳንዶች በሰዎች ፊት ደካማ ኃጢያተኛና የተናቁ ለመሆን ሞክረዋል፡፡
ይሁንና ነፍሶቻቸው ውብ ነበሩ፡፡

በርካታ የቅዱሳን ታሪኮች እንደ ደደብ እና በሽተኞች እንደሆኑ ስለተቆጠሩ ቅዱሳን ይነግሩናል፡፡ በርካታ ቅዱሳን ይህ ምግባር አላቸው፡፡ ምግባሮቻቸውን ስንጠቅስም ምግባራቸውን የሚደብቁ ኃጢያቶቻቸውን እና ጥፋቶቻቸውን የሚገልፁ ወይም የእነርሱ ያልሆነውን ሀጢያት በሐላፊነት የሚወስዱ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

በእርግጥም እያንዳንዳችሁ ይህን ማድረግ አትችሉም፡፡ ይሁንና እነዚህን ሙሉ ለሙሉ እና ያለማመንታት የዓለምን ከንቱ ኃላፊ እና ብልጭልጭ ክብር የናቁ ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

ታላቁ አባ መቃርስ መናኘ ብቸኛ ሰው ነበሩ፡፡ ወንድሞች አንድ ዋንጫ ወይን እንዲጠጡ በገፋፋቸው ጊዜ የእነርሱ ስሜት እንዳይጎዱ በመፍራት ወይኑን ተቀበሏቸው፡፡

በዚህ ፋንታ ግን ለአንድ ሙሉ ቀን ራሳቸውን ውሃ ከመጠጣት ይከለክሉ ነበር፡፡ እነዛ ወንድሞች ሁለት ወይም ሶስት ዋንጫ ወይን እንዲጠጡ ሲገፏፏቸው ራሳቸውን ለሁለት ወይም ለሶስት ቀን ያህል ውሃ ከመጠጣት ይከለክሉ ነበር ማለት ነው፡፡

ይህም በሰዎች አይን እኚህ ሰው ወይን እንደሚጠጡ የሚያሳይ ምሳሌ ነው፡፡ በመሰረቱ ግን እኚህ ሰው ራሳቸውን ውሃ በመከልከል እና እውነተኛ የብሕትውና ሕይወት በመኖር የሚቀጡ መሆናቸውን ያሳየናል፡፡

የእርሳቸው ተግባር ጥቁር ግን ውብ የሚለውን መገለጫ በእጅጉ ሊገልፀው የሚችለ ምሳሌ ነው፡፡

በርካታ ሰዎች ለእርዳታ ድርጅቶች በሕዝብ ፊት እና በግልፅ ገንዘብ ከመስጠት ይቆጠባሉ፡፡ ይሁንና በግል ያደርጉታል፡፡ ዐሌሎች ሰዎች ዓይን እንደስግብግብ ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ ገንዘብ መስጠት የማይፈልጉ ተደርገው ሊታዩ ይችላሉ ይሁንና ለታይታ ስለማያደርጉት ነፍሶቻቸው ግን ውቦች ናቸው፡፡

ይህ ከሌሎች ሰዎች፡ዓይን ርቆ የሚደረግ የእያንዳንዱ መልካም ምግባር ሁኔታ ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች ስለአንድ ስለተወሰነ ሰው ሥንመ የተለየ ነገር የለውም የሚል እሳቤ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ያ ሰው አንድ ተራ ሰው ነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ወይም ከተራ ሰውነት ያነሰ አድርገው ሊመለከቱት ይችላሉ፡፡ ለሁሉም አይነት ገፅታዎች የእንደዚህ ያለ ሰው ነፍስ ጥቁር ተደርጋ ልትወሰድ ትችላለች ነገር ግን በእውነታው ውብ ናት ምክንያቱም ያ ሰው ለታይታ አላደረገም፡፡

ወደራሱ ውስጡን የሚመለከትና እና በራሱ የሚፈርድ በታማኘነት የደካማነቱን እና የጥፋቱን እውነተኛ ዋጋ የሚያምን እና የሚሰጥ እንደዚህ ያለው ፀፀት የተሞላበት መንፈስ ነው፡፡ በብዙ የፀፀት እንባዎች የታየ ሰው ጥቁር ቢመስልም እንኳን እንደዚህ ያለ ሰው ውብ ነው፡፡

ዳግመኛም ጥቂርና ውብ ለእግዚአብሔር ሲል ሁቹን የተወ ሰው የሚመራው ራስን የመካድ ህይወትን ለማመልከት ያገለግላል፡፡
ለእርሱ ሲል አንድ ሰው ራሱን ከሁሉም ነገር ሊከለክል ይችላል፡፡

ዳግመኛም ራሳቸውን ማንኛውም ነገር ከልክለው በብሕትውና የሚኖሩ እነርሱ ውብ ናቸው፡፡ ያላቸውን ሁሉ ሸጠው፡ለድሆች፡የሚሰጡ በማጣት እና በመራቆት ሕይወታቸውን የሚመሩ በመራብና በመጠማት በራቁትነት እና በብርድ ራሳቸውን ምግብ ድሎት እና የህይወት ጣዕም ሁሉ ከልክለው ለእግዚአብሔር ሲሉ በማጣትና በችግር ለመኖር የወሰኑ ሁሉ ውብ ናቸው፡፡

በእንደዚህ ያለ አስከፊ የድህነት የበታችነት እና የውርደት ሁኔታ ሳሉ ጎስቋላ እና ጥቁር ሆነው ሊታዩ ይችላሉ፡፡

በእግዚአብሔር ዕይታ ግን ንፁህ እና ውቦች ናቸው፡፡

#ነፍሴ_የወደደችውን_አያችሁትን???

በቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ዘኤልያስ ወልደ ሚካኤል እንደተረጎመው፡፡

ለንባብ እንዲመች አድርጌ ቀነጨብኩት፡፡

ሁላችሁም ገዝታችሁ ታነቡት ዘንድ እጋብዛለሁ፡፡

@jahABP እኔም እላለሁ ሰው ላይ ከመፍረድ እንቆጠብ ምክንያቱም ጥቁር ግን ውብ ሊሆኑ ይችላሉና😍😍😘🙏🙏

መልካም ጊዜ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2029 535
AB PHOTOGRAPHY

ከ10% ይገባዋል የምትሉትን ስጡልኝ

ቅዱሴ ወንድሜ ይህን የመሰለ ፎቶ እንዳነሳ ላደረከውን መስዋትነት ቃል የለም ቡናህን ስላቀዘቀዝኩብህ ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏🙏🙏😍😍🥰

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #2028 561
𝐀𝐁 𝐏𝐇𝐎𝐓𝐎𝐆𝐑𝐀𝐏𝐇𝐘 & 𝐆𝐑𝐀𝐏𝐇𝐈𝐂 𝐃𝐄𝐒𝐈𝐆𝐍

#እናንተ_የእየሩሳሌም_ቆነጃጅት_ሆይ_እ_ጥቁር_ነኘ_ነገር_ግን_ውብ_ነኘ

ጥቁር ነኘ የሚለው በተለየ ሁኔታ እንግዳ እና ያልተለመደ ሐረግ ነው፡፡
ይህ ሐረግ ትሑት በሆነች ባልተጠበቀች እና ፀፀት በተሞላበት ነፍስ ማለትም በፍጥነት ኃጢያቶችን እና ድክመቷን ለመናዘዝ እና ድክመቶቿን ለማመን የማያስችል ክብደት ወይም ሐፍረት አይሰማትም፡

ብዙ ሰዎች በጎ ምግባራቸውን ይናገራሉ ድክመታቸውን ለመግለፅ ግነ ያቅታቸዋል፡፡ እውነተኛ ምስሏን ለማንፀባረቅ የተራበች የከበረችና ፃድቅ ነፍስ ፦ኔ ጥቁር ነኘ ለማለት ውርደት እና ክብር ማጣት መስሎ አይሰማትም፡፡

ያለማቋረጥ ስለታላቅነታቸው እና ስለበጎ ምግባራቸው ከሚያወሩ ሰዎች የበለጠ ጨቋኞችና አመፀኞች ማንም ሊኖር አይችልም፡፡ ስህተቶቻቸውን ወይም ድክመቶቻቸውን ሲገለጥባቸው በተከታታይና ያለማቋረጥ የሚከራከሩ ሰዎች ሸክሞችና አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ ስህተቶቻቸውን ለመሸፈንና ለመደበቅ ይሞክራሉ ወደ ውሸትና ወደማጭበርበር ሊዞሩ ይችላሉ፡፡

ይሁንና ግን ድክመቶቿን እኔ ጥቁር ነኘ ስትል የገለፀችው ይህቺ ነፍስ ውብ ናት ፈፅማ ውብ ናት፡፡ በኃጢያቶቼ ምክንያት እኔ ጥቁር ነኘ በድክመቶቼ ምክንያት እኔ ጥቁር ነኘ፡፡ ይሁንና እያንዳንዱን ድክመት በሚሸፍነው በአንተ ፍቅር እኔ ውብ ነኘ ድክመቶቼን እኔ አልሸፍናቸውም እገልጣቸዋለሁ ፍቅርህ ግን ይሸፍነኛል፡፡

ፍቅር ብዙ ኃጢያትን ትሸፍናለች፡፡

ኃጢአቶቿን እና ድክመቶቿን ስትናዘዝ እኔ ጥቁር ነኘ ነገር ግን ውብ ነኘ ለምን አለች? ምክንያቱም ሰብአዊ ፍጡራን ኃጢአቶቻቸውን በተናዘዙበት ቅፅበት ጨለማቸው ይጠፋል ኃጢአትቻቸውን ይረሱላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ያመናችኀቸውን እያንዳንዳቸውን ድክመቶች ያጠፋቸዋል የተናዘዛችኀቸውን ኃጢያቶች ከዚያ በኀላ አያስታውስባችሁም፡፡

በኑዛዜ አማካኘነት ነፍሳችሁ ትነፃለች ትታጠባለች ነጭም ትሆናለች፡፡ ስትናዘዙ እና ጥቁር እንደሆናችሁ ስታምኑ ብቻ ይህን የውበት ደረጃ ታገኛላችሁ፡፡

የሰው ነፍስ ጥፋቶቿን በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጥቁር ነኘ በማለት ልትናዘዝ ትችላለች አንተን ብቻ በደልኩ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ ዳግመኛም ድክመቶቿን ልታሳውቅ እና በሰዎች ፊት እኔ ጥቁር ነኘ ልትል ትችላለች ይህንንም የምታደርገው እብሪተኛ ጉረኛ ወይም ትዕቢተኛ ላለመሆን ነው፡፡

በውስጧም እንኳን ትዕቢተኛ እና ራሷን ከፍ ያደረገች ላለመሆን ለራሶ ማንነት ጥቁርነቷን ልትናገር እና እኔ ጥቁር ነኘ ልትል ትችላለች፡፡

ይህን በማድረጓ ነፍስ ፀፀት የተሞላባት እና ትሁት ትሆናለች ሰውም በራሱ ዓይን ፃድቅ የመሆንን ግብዝነት ያስወግዳል፡፡ በራሳቸው እይታ ጻድቅ እና ንፁህ የሆኑ ሰዎች ድክመቶቻቸውን ፈፅመው አያምኑም ለእነርሱ እኔ ጥቁር ነኘ ማለት የማይቻል ነው፡፡

ሁለቱም አዳምና ሔዋን በእግዚአብሔር በተጠየቁ ጊዜ ወንጀላቸውን ለመናገር ተቃወሙ ስህተታቸውን ለማመንም አመነቱ፡፡ ከሁለቱ አንዳቸው እንኳን እኔ ጥቁር ነኘ ለማለት የቻለ የለም፡፡

ስለዚህ እኔ ጥቁር ነኘ ነገር ግን ውብ ነኘ ከሚለው ዛሬ መማር የምንችለው የመጀመሪያው ትምህርት ጥፋቶችን ማመንን እና ሀጢያቶችን መናዘዝ ነው፡፡
ይሁንና አንድ ሰው ጻድቅ ሊሆን ቢችልም የተወሰኑ ጥፋቶችን እና ሊናዘዛቸው የሚገቡ ጥቁር ነጥቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ በተግባሮቼ በፈቃዴ እና በምርጫዬ እኔ ጥቁር ነኘ፡፡

ግን ለሱ ለተናዘዝኩት እያንዳንዷ ብቸኛ ሀጢያት በሚያጠፋው በእግዚአብሔር ውብ ነኘ፡፡

የእግዚአብሔርን ቅድስና በማስተዋል አንድ ሰው የራሱን አደገኛና አስከፊ ድክመቶች ወደመረዳት በእርግጠኘነት ይመጣል፡፡

በየጊዜው ስመረመር በጨለማ ጥቁረት ውስጥ እንዳለሁ እና ገና ምንም ነገር እንዳላገኘሁ ይሰማኛል ፀሀይ መልኬን አክስሎታልና፡፡

አንደ ሰው ራሱን በጽድቅ ጉዳይ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሲያነፃፅር እርካታ ሊሰማው ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ራሱን ከሐዋርያት ከቅዱሳን ከነቢያት ጋሬ ሲያነፃፅር ምስሉ በእጅጉ ይለወጣል፡፡ በርካታ ጥቁር እድፎችን እና የቆሸሹ ነጥቦች በሕይወቱ ውስጥ ይገለበጣሉ፡፡ ራሱን ከመላዕክት ጋር ሲያነፃፅር ፈጥኖ በውስጡ ያለውን ጥቁረት እና ቆሻሻ ሲገነዘብ ብቻ እናንት የኢየሩሳሌም ቆነጃጅት ሆይ እኔ ጥቁር ነኘ ነገር ግን ውብ ነኘ ፀሀይ መልኬን አክስሎታልና ይላል፡፡
.
.
.
ይቀጥላል
Post #2027 522
卂乃 卩卄ㄖㄒㄖᎶ尺卂卩卄ㄚ

#እናንተ_የእየሩሳሌም_ቆነጃጅት_ሆይ_እኔ_ጥቁር_ነኝ_ነገር_ግን_ውብ_ነኝ ::

የሰለሞን መዝሙር 1:5

ሊነበብ የሚገባው ድንቅ ፅሁፍ


#ነፍሴ_የወደደችውን_አያችሁትን??? ከሚለው
ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ መፅሐፍ

ዘኤልያስ ወልደ ሚካኤል እንደተረጎመው


አስደናቂው ፅሁፍ ጠብቁኝማ 🦶🏿🦶🏿👣🦶🏿🦶🏿
Post #2024 580
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


ባለፈው ሳምንት ከምወዳት ልጅ ጋር ተገናኘተን ነበር እናም ለጨዋታችን ይረዳን ዘንድ ፀጥ ወዳለው ብዙ በጥባጭ ወደሌለበት ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሎቢ ላይ ተቀምጠን የሆድ የሆዳችንን እያወራን በመሃል ስለ አንድሽ ማውራት ጀመርንና እንዲህ አለችኘ በእውነት ነው የምልህ አብዬ አንድሽ ምን ያህል እንደሚወድህ አታውቅም ፈገግ አልኩ የምሬን ነው እኔ አንተ ሴት ብትሆን ኖሮ በፍፁም ጓደኛው ብቻ ነህ ብዬ አላስብም......

እና ስላት😂😂

ፍቅረኛው ነች ብዬ ነበር የምደመድመው ማርያምን 😂😂😂 በቃ ስላንተ አውርቶ አይጠግብም እውነቴን ነው አብዬ አለችኘ፡፡

እኔ፡- በሳቅ ፍርፍር😂😂😂

ትዝ ይልሃል ቅዱሴን እዚ እንዳለሁ በምን አወክ ስትለው አብይ ካለ ትኖራለህ ብዬ ነው ያለህን😂😂😂

አንድሽዬ የኔ መልካም ወንድም ስላንተ ምን ብዬ እንደምናገር አላውቅ ብቻ ፈጣሪ አምላክ አንተን በህይወቴ ስለሰጠኘ ሁሌም ቢሆን አመሰግነዋለሁ የኔን ሁሉ ነገሬ የምታውቅ ደህንነቴ የሚያሳስብህ፡፡

ሁሌም ቀናውን መንገድ የምታሳየኘ ከምንም በላይ የፈጣሪን ትልቅነት የምትነግረኘ ዘወትር ሁሌም እግሮቼ ከቤቱ እንዳይለኘ የምትነግረኘ ይህን ነገር ግን ፈጣሪ ይደግፈዋል ትላለህ ብለህ ወደ መጥፎ ስጓዝ የምትመልሰኘ በምንም መልኩ ይሁን መጥፎ ያረኩ መስሎ ከተሰማህ የማትደግፈኘ ከማንም በላይ እንደፈለኩ የማዝ(ለኔ ብቻ አይደለም ለሁሉም ነው) የምቀብጥብህ፡፡

ታታሪነትህ የሚያስደንቀኘ ሰለቸኘን የማታውቅ ስራን መስራትስ እንደሱ የሚባልልህ በሁሉም ቦታ ተወዳጅ የሆንክ ጥሩነትህ መጥፎችን የማሸነፍ አቅም ያለው ተስፋ ያለመቁረጥ ልኩ የኔ ሳቅ ፈጣሪዬ እንደ አንድሽ ሁኑ ተብለን ያደግን ነን በአንተ መስመር ለመሔድም እየጣርንም ነው የኔ መልካም ሰው የኔ አስተዋይ ሰው የኔ ራዕዩን ሳያሳካ ወደኀላ የማታውቀው ሰው የኔ ቆራጡ ሰው የኔ ታማኙ ሰው የኔ የኔ የኔ የኔ የኔ..............አንድሽዬ እንኳንም ተወለድክልኘ መልካም ልደትእንኳንም ተወለድክልኘ፡፡

ኧረ በቃኘ አበዛሁባቸው መሰለኘ😜

#በእውነት_ፈጣሪ_አንተን_የሰራህ_ካንተ_በላይ_ለኔ_አስቦ_ነው፡፡

ይኸው ይሔን ሙዚቃ ተጋበዝልኘ

ጥሮ አዳሪ ለፍቶ አዳሪ
የእግዜር ድሃ ደክሞ ኗሪ
ደግ ሩህሩህ ልበ ቀና
በሰው ኑሮ የማይቀና
.
.
አስተዋይና ርቆ ሀሳቢ
ዘመድ አዝማዱን ሰብሳቢ
አስተማሪ ሁሉ አዋቂ
መካሪ ነው አስታራቂ
አዛኘ ሰው ነህ የምትሳሳ
ክፉ ደጉን የማትረሳ

ተርፎ ባይተርፈውም
አውቃለሁ ደሃ ነው
አያንስም ለራሱ
የጤና ሀብታም ነው
ሁሉን መስሎ ኗሪ
ፀባዩ ጉልበቱ
ደስታው ስራ ነው
ጎጆው ነው ኩራቱ
.
.

አሃሃሃ
የማትገዛ
አሃሃሃ
ለብልጭልጩ
አሃሃሃ
የድሃ ጎበዝ
አሃሃሃ
የኩራት ምንጩ
አሃሃሃ
የማትደነቅ
አሃሃሃ
ባረባ ነገር
አሃሃሃ
እጁን የማይሰጥ
አሃሃሃ
የማይበገር

የኔ ጎበዝ የኔ ደሃ
ፍቅሩ ማይደርቅ የምንጭ ውሃ
ሀበታም ለበቅ ቢያቀናጣም
ደሃ እንዲያድር ከእጁ አያጣም

ጥረው ግረው ያገኙት
ይጣፍጣል ሲበሉት
ቆሎም ሽሮም ጮማ ናቸው
ሰው ተፋቅሮ ከበላቸው፡፡

ብቻ ይገልጥሃልና አድምጥልኘ አንተ መልካም ሰው፡፡

😍😍😍🙏🙏🙏😘😘😘

@jahABP ነኘ 😘😘
Post #2022 489
እንኳን አደረሳችሁ🌷🌺🌹🌷🌹🌹🌺🌷🌷🌹
Post #2019 542
አክሊለ ፅጌ ማርያም😍😍😍😍😍🙏🙏😍👏
Post #2015 541
live ጠብቁኝ 👣👣👣
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →