TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #2024 580
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


ባለፈው ሳምንት ከምወዳት ልጅ ጋር ተገናኘተን ነበር እናም ለጨዋታችን ይረዳን ዘንድ ፀጥ ወዳለው ብዙ በጥባጭ ወደሌለበት ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሎቢ ላይ ተቀምጠን የሆድ የሆዳችንን እያወራን በመሃል ስለ አንድሽ ማውራት ጀመርንና እንዲህ አለችኘ በእውነት ነው የምልህ አብዬ አንድሽ ምን ያህል እንደሚወድህ አታውቅም ፈገግ አልኩ የምሬን ነው እኔ አንተ ሴት ብትሆን ኖሮ በፍፁም ጓደኛው ብቻ ነህ ብዬ አላስብም......

እና ስላት😂😂

ፍቅረኛው ነች ብዬ ነበር የምደመድመው ማርያምን 😂😂😂 በቃ ስላንተ አውርቶ አይጠግብም እውነቴን ነው አብዬ አለችኘ፡፡

እኔ፡- በሳቅ ፍርፍር😂😂😂

ትዝ ይልሃል ቅዱሴን እዚ እንዳለሁ በምን አወክ ስትለው አብይ ካለ ትኖራለህ ብዬ ነው ያለህን😂😂😂

አንድሽዬ የኔ መልካም ወንድም ስላንተ ምን ብዬ እንደምናገር አላውቅ ብቻ ፈጣሪ አምላክ አንተን በህይወቴ ስለሰጠኘ ሁሌም ቢሆን አመሰግነዋለሁ የኔን ሁሉ ነገሬ የምታውቅ ደህንነቴ የሚያሳስብህ፡፡

ሁሌም ቀናውን መንገድ የምታሳየኘ ከምንም በላይ የፈጣሪን ትልቅነት የምትነግረኘ ዘወትር ሁሌም እግሮቼ ከቤቱ እንዳይለኘ የምትነግረኘ ይህን ነገር ግን ፈጣሪ ይደግፈዋል ትላለህ ብለህ ወደ መጥፎ ስጓዝ የምትመልሰኘ በምንም መልኩ ይሁን መጥፎ ያረኩ መስሎ ከተሰማህ የማትደግፈኘ ከማንም በላይ እንደፈለኩ የማዝ(ለኔ ብቻ አይደለም ለሁሉም ነው) የምቀብጥብህ፡፡

ታታሪነትህ የሚያስደንቀኘ ሰለቸኘን የማታውቅ ስራን መስራትስ እንደሱ የሚባልልህ በሁሉም ቦታ ተወዳጅ የሆንክ ጥሩነትህ መጥፎችን የማሸነፍ አቅም ያለው ተስፋ ያለመቁረጥ ልኩ የኔ ሳቅ ፈጣሪዬ እንደ አንድሽ ሁኑ ተብለን ያደግን ነን በአንተ መስመር ለመሔድም እየጣርንም ነው የኔ መልካም ሰው የኔ አስተዋይ ሰው የኔ ራዕዩን ሳያሳካ ወደኀላ የማታውቀው ሰው የኔ ቆራጡ ሰው የኔ ታማኙ ሰው የኔ የኔ የኔ የኔ የኔ..............አንድሽዬ እንኳንም ተወለድክልኘ መልካም ልደትእንኳንም ተወለድክልኘ፡፡

ኧረ በቃኘ አበዛሁባቸው መሰለኘ😜

#በእውነት_ፈጣሪ_አንተን_የሰራህ_ካንተ_በላይ_ለኔ_አስቦ_ነው፡፡

ይኸው ይሔን ሙዚቃ ተጋበዝልኘ

ጥሮ አዳሪ ለፍቶ አዳሪ
የእግዜር ድሃ ደክሞ ኗሪ
ደግ ሩህሩህ ልበ ቀና
በሰው ኑሮ የማይቀና
.
.
አስተዋይና ርቆ ሀሳቢ
ዘመድ አዝማዱን ሰብሳቢ
አስተማሪ ሁሉ አዋቂ
መካሪ ነው አስታራቂ
አዛኘ ሰው ነህ የምትሳሳ
ክፉ ደጉን የማትረሳ

ተርፎ ባይተርፈውም
አውቃለሁ ደሃ ነው
አያንስም ለራሱ
የጤና ሀብታም ነው
ሁሉን መስሎ ኗሪ
ፀባዩ ጉልበቱ
ደስታው ስራ ነው
ጎጆው ነው ኩራቱ
.
.

አሃሃሃ
የማትገዛ
አሃሃሃ
ለብልጭልጩ
አሃሃሃ
የድሃ ጎበዝ
አሃሃሃ
የኩራት ምንጩ
አሃሃሃ
የማትደነቅ
አሃሃሃ
ባረባ ነገር
አሃሃሃ
እጁን የማይሰጥ
አሃሃሃ
የማይበገር

የኔ ጎበዝ የኔ ደሃ
ፍቅሩ ማይደርቅ የምንጭ ውሃ
ሀበታም ለበቅ ቢያቀናጣም
ደሃ እንዲያድር ከእጁ አያጣም

ጥረው ግረው ያገኙት
ይጣፍጣል ሲበሉት
ቆሎም ሽሮም ጮማ ናቸው
ሰው ተፋቅሮ ከበላቸው፡፡

ብቻ ይገልጥሃልና አድምጥልኘ አንተ መልካም ሰው፡፡

😍😍😍🙏🙏🙏😘😘😘

@jahABP ነኘ 😘😘
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →