TGViewer
Channel Public Channel
Phenomenal pictures & graphic design

Phenomenal pictures & graphic design

@abpgd

FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Subscribers
1.08K
Photos
1.8K
Videos
8
Links
16

Showing posts older than #1818 · Back to latest

Older Posts 20 shown
Post #1817 637
እኔማ #አትፍረድ የሚለውን የብፁዕነታቸው የአቡነ ሺኖዳ መፅሐፍ እያነበብኩ ነበርና ከዛ ላይ ቀንጭቤ ላቀርብ ነበር ግን

ጉንፋን ይዞኘ አታምኑኘም አንጠባጥቦ፡አንጠባጥቦ ጠቅልሎ ጣለኘ ጉድ ሰራኘ 🤧🤥🤭😢ደሞ ሲያመኘ እንባዬ የጉድ ነው(ያንተ ዕንባ አፍንጫህ ጋር ነች ጭራሽ አሞህ እያሉ እቤት ሙድ ይይዙብኛል) እና ትላንት ቀኑን ሙሉ አስተኘቶኘ #የድንግል_ልጅ የተመሰገነ ይሁን ዛሬ ነቃ ነቃ ብያለሁ 🙏🙏💪💪💪

😷😷 የፊት መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አይረሳ እላለሁ፡፡


የምር ግን ደስ ብሎኛል ጤንነቴ አሳስቧችሁ ደውላችሁ ተሻለህ ወይ ላላቹ ለሁላችሁም ማርያምን አመሰግናለሁ ክብር ይስጥልኘ ትለያላችሁ😍🙏🙏አመሰግናለሁ፡፡

አሁን ጠብቁኘ መጣሁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

@jahABP ነኘ 😊😍🙏
Post #1816 715
በጣም በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ ትንሽ ስላመመኘ ነው 😔😔😔😔 እንደተሻለኘ ወደናንተ አደርሳለሁ💪💪💪
Post #1815 699
🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ጠብቁኘ ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Post #1814 821
አስደናቂው ሰውዬ

ክፍል ሁለት ➋

Voice:- heluyeeee😍🙏😊
Post #1813 776
አስደናቂው ሰው ክፍል ➋ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Post #1811 853
አስደናቂው ሰውዬ

ክፍል አንድ ➊

Voice:- heluyeeee😍🙏😊
Post #1810 809
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አድን ሰው በአካል ሳታውቁት ለመገናኘት ናፍቃችሁ አታውቁም???

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ይጠቀማሉ ከሚባሉት ሰዎች አንዱ ነኘ ለማለት እደፍራለሁ፡፡


ከነዚህም ውስጥ አብዝቼ ቴሌግራምን እጠቀማለሁ ታዲያ በቴሌግራም ያወኳቸው በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡😍🙏

በጣም የሚያስገርሙ ገራሚ ዕውቀት ያላቸው እንደዚህ አይነትም ሰው አለ እንዴ የሚያስብሉኘ ጀግኖቹን ደግሞ በጣም እቀርባቸዋለሁ ከአብዛኞቹ ጋር ደግሞ ልክ የቤተሰብ ያህል ነን በየጊዜው እንደዋወላለን እንገናኛለን እቤት ይመጣሉ ምናምን፡፡

መጥፋታቸው እኔን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቼንም ያሳስባቸዋል ማዘርንም እንዴ #ሳሚ የት ጠፋ #የማ ትምህርቱን ጨረሰ ያቺ ስሟ ጠፋኘ ባለፈው የነገርከኘ ልጅስ እንዴት ሆነች?? ሲስተርም ትዝታ ከውጪ መታለች እንገናኛለን ቤት ትመጣለች አላልከኘም ትለኛለች ወንድሜም ያ የነገርከኘ ልጅ አንዴትሆነ መፅሐፍ ማንበብ ጀመረ ተገናኛቹ ይለኛል?? የቤተሰብ ያህል ቅርብ ነን..............
#ሳሚሾ #የማ #አንዱ

#ትዙዬ_የኔ(የምወድሽ😊🙏😘)

#ማፊሾዬ😍😘(መፅሐፍን አንቺ አንብቢያት)

#ሔሉዬ(ጋዜኛዋ..ውድ ነሽ)

#ሮዚ(ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ነገር እንጠቀም)

#ኤልሲዬ(ምርጧ)

#ሐያትዬ(ሳንገናኘ ልቴጂብኘ ነው አ😔😢)

#Hana_SH(እንዳባቷ ተጠራጣሪ😄ዋ)

ብቻ ያልጠራኀቹንም ጨምሮ ሁላቹም እናንተን ስላወኩ በጣም ደስተኛ ነኘ ከምላቹ በላይ ብዙ ነገሮችን አስተምራችሁኛልና አመሰግናችኀለሁ ከናንተ ያገኘሁት ማገኘው ብዙ ነውና አትጥፉብኘ 😍🙏😊ኦዳቹዋሎሎ


አድን ሰው በአካል ሳታውቁት ለመገናኘት ናፍቃችሁ አታውቁም??? እንዲሁ በወሬ የዛሬ ይሔን ፅሁፍ እንድፅፍ መነሻ የሆነችኘ #ሔሉዬ(ጋዜጠኛዋ😂😂 ግን ገና ተማሪ ናት) እሷ ነች በጣም ነው የምናወራው ምንከራከረው ስለሁሉም ነገር ስለ ቀን ውሎአችንም ጭምር እና በዚ ሰሞን አንድ ሰው ተዋወቀችና በጣም ስላስደነቃት ቃላት እያጠራት አንድ የድምፅ መልዕክት ላከችልኘ ከፈትኩት ትንሽ እረዘም ይል ነበርና ሔሉዬ አሁን ስራ ላይ ስለሆንኩ በኀላ ሰምቼ ምላሽ እሰጥሻለሁ አልኳት፡፡

እኔ የመሰለኘ የሬዲዮ ፕሮግራሞቿን አስተያየት ስጠኘ ብላ ስለምትልክችኘ እንደሱ መስሎኘ ነበር ማታ ላይ ከፍቼ ስሰማው ግን እኔም ደነቀኘ ሦስት አራት ጊዜ ሰማሁት ግን ለሷ ምላሽ እስካሁን አልፃፍኩላትም፡፡

ምክንያቱም የምር እንደዚአይነት ሰው አለ እንዴ ብዬ እራሴን ጠየኹ ደነቀኘ ገረመኘ ተመስገንም አልኩ እራሴን ፈተሽኩበት ድክመቴ እጥፉኑ ገኖ ታየኘ እራሴን ወቀስኩ አምላኬን ስንቴ እንዳማረርኩት ቆጠርሁ አዘንኩም ሰውየውንም ማየት ፈለኩ ያለችበት እሱም ያለበት #ወላይታ_ሶዶ ሔጄ አጠገቡ ቁጭ ብዩ ብዙ ነገር መማር እሷ እንዳለችኘ ዝም ብሎ መስማት መስማት መስማት ፈለኩ ረጅም ጊዜን ማሳለፍ ወደድኩኘ😃😃😃😃😍

ሔሉ ለምን እኔ ብቻ ብላ አይደል ለኔ የነገረችኘ እኔም ለምን እኔ ብቻ ብዬ ይሔን ሰውዬ ከእናንተ ጋር ላስተዋውቃችሁ ፈለኩኘ በእርግጠኘነት ብዙ ምትማሩበት ነገር አለ ትገረሙበታላቹ ብዬ ላስተዋውቃችሁ ፈለኩኘ.........

ሔሉ የሚከፋት አይመስለኘም ቀጥታ እሷ የላከችልኘ የድምፅ መልዕክት ለናንተ ባስተላልፍ የሷ አገላለፅ ይበልጡኑ ያጎላዋች ብዬ ሰለለማስብ ነው፡፡

ጠብቁኘማ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

መልካም ሰዎች ሁላችሁም በያላችሁበት ምስጋናና አክብሮቴ ይድረሳችሁ ያው የመልካምነት ወጋ ከፋይ እሱ አንድዬ ፈጣሪ ነውና እሱ ፀጋውን ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣቹ እላለሁ፡፡

@jahABP ነኘ መልካም ምሽት

አስተያየታችሁን አድርሱኘ

ድንቁን ሰው ተዋወቁት🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1809 840
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ወዳጄ_ሆይ


ይህ ዓለም የጨዋታ ሜዳ ሳይሆን ጦር ሜዳ መሆኑን አስብ፡፡

መቁሰል አለ መድማት አለ ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ትግል የሌለበት በጥያቄ የማይሞገት ማንም የለም፡፡ ራስወዳድ ስለሆንክ የራስህን ብቻ ታገነዋለህ እንጂ ሁሉም እንዳንተ በጥያቄ የሚኖር ነው፡፡

#በዚህ_ዓለም_ላይ_የሚያኖርህ_አለማወቅህም_ነውና ሁሉን ለማወቅ አትሻ፡፡ ነገ የሚሆንብህን ክፉ ገጠመኘ ብታውቅ መኖርህን በጠላህ ነበር፡፡
ከሰው ወገን የነገን ወዳጅህ ማን መሆኑን በእርግጠኘነት መናገር አትችልም እግዚአብሔር ግን የዘላለም ወዳጅህ ነው፡፡

ሰዎች ብዙ ደክመህላቸው ሊረግሙህ ልታስደስታቸው በጣርህ ቁጥር ሊበሳጩብህ ባደረክላቸው መጠን ላይረኩ ይችላሉ አንተ ግን አምላክህን ለማስደሰት ኑር እግዚአብሔር የሚያውቅ ይደሰትብኃል

#ደግሞም_በፈጠረው_ጌታ_ያልረካ_ሰው_በአንተ_እንዲረካ_መጠበቅ_ስህተት_ነው፡፡
ለሞተለት ጌታ ፍቅር ያልተሸነፈ ምንም ላላደረክለት ላንተ ምላሹ ይህ ቢሆን አይደንቅም፡፡

በዓለም ላይ የመከራ መከራ መደነቅና መፈለግ ነው፡፡ በክፉ አትደነቅ መደነቅ ጉልበት ይጨርሳል ጠላትህን ለሌላ ተንኮል ያነሳሳል #የሆነን_ነገር_አለመቀበል_ሞኘነት_ነው፡፡ የሰውን ደረት እየመቱ ማዘን አያምም የራስን ደረት እየመቱ ማዘን ግን ያማል አንተም በሰው ችግር ፈራጅ አትሁን፡፡

ዛሬ የምትናገረው ዘር ነው ነገ በራስህ ወይ በልጅህ ታጭደዋለህና ለምትናገረው ተጠንቀቅ፡፡

ይላል #ታዴ በስጦታ ያበረከተልኘ መፅሐፍ
አመሰግናለሁ ወንድሜ😊🙏😍

የመፅሐፉን ርዕስ የፈለገ በውስጥ መስመር ያናግረኘ፡፡


@jahABP ነኘ 😊🙏😍

በመልካምነት በመረዳዳት በፍቅር በመታገስ በተስፋ እንኑር እላለሁ፡፡

አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1808 624
ይነበብ ይነበብ ጠብቁኘማ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Post #1807 785
.......#ጾም........

ብዙዎች ጾምን የምግብ ለውጥ ወራት ብቻ አድርገው ያስቡታል፡፡ ከሥጋ ምግቦች ወደ አትክልት ከቅባት ወደ ደረቅ የሚደረግ ሽግግር፡፡ ጾም ስላለው መንፈሳዊ ፋይዳ ግድ የሌላቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡

በመሠረቱ ፆም ለተወሰኑ ጊዜያት ራስን ከምግብ መከልከል ከዚያም በአልሚ ምግብጠ በይዘታቸው ዕውቅ ከሆኑ ምግቦች በስተቀር በጥቂቱ መመገብ መነሻ ያደርጋል፡፡

አንተ ከምግብማ ከመጠጥ መከልከልን ሞክረኸዋል?
ከባድ የረሃብ ስሜት ደረጃ ላይ ደርሰህ ታግሰኸዋል?

ይህ የመጀመሪያ መልመጃ ነው፡፡ "ረሀብና ጥምን" መታገስ" ጌታ አምላክም ተራበ ተብሏል፡፡

በተራብክ ጌዜ ደካማነትህን ትረዳለህ፡፡ በኃይልህ መመካት ይቀራል፡፡ በእግዚአብሔርም መደገፍ ትጀምራለህ፡፡
እየራበህ ሳለህ ስትፀጸና #ትዕግስትን #ራስን_መግዛት የተባሉትን የመንፈስ ፍሬዎች እያፈራህ ነው፡፡ ስለዚህም እየጾምክ ሳለህ የረሀብ ስሜት ስለተሰማህ አትብላ፡፡ ይልቁንም ትዕግስትና ራስን መግዛትን ተማርበት፡፡

የረኃባቸው ዋጋ በትዕግስት ካገኙ አባቶች በረከት ተካፈል፡፡ ከዚህም በላይ በረሃብ ምንም የሚቀምሱት ምግብና መጠጥ አጥተው የሚሰቃዩ ወገኖችህን ስቃይ ታስብበታለህ ትረዳበታለህ፡፡ ታዝንላቸዋለህ፡፡

#ባትጾም_ትበላው_የነበረውን_ትሠጣቸዋለህ፡፡

እና ለተወሰኑ ሰዓታት ከምግብ መከልከል ማለት ይህ ነው፡፡

ጉዞ ወደ እግዚአብሔር(the spiritual mean) ከሚለው
ከብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ መፅሐፍ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተቀነጨበ፡፡

ተርጓሚ ዲ/ን ግርማ ባቱ

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም ጊዜ
Post #1806 720
ጾም

ጉዞ ወደ እግዚአብሔር (the spiritual means)

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ተርጓሚ ዲ/ን ግርማ ባቱ

@jahABP ነኘ መልካም ጊዜ
Post #1805 679
ታላቅ ሆነህ ኖረህ ታናሽ ሆነህ እንዳትሞት ተጠንቀቅ፡፡

@jahABP 😊😉 ነኘ

መልካምነት ይለምልም
Post #1804 668
ጠብቁኘማ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Post #1802 717
የሚመስል ነገር

ይኽን መፅሐፍ ፈልጋችሁ እንድታነቡ ብዙ ጊዜ ወትውቻለሁ አሁንም እወተውታሁ

ራዕይ ያለው ትውልድ:-
ዲ/ን አሸናፊ መኮንን
@jahABP ነኘ
Post #1801 653
🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

እባካችሁ ተጋበዙልኘ😊🙏
Post #1799 876
የማርቲን ሉተር ጊንግን ጁኒየር

ተጋበዙልኘማ😍😍😍👏👏👏👏👏💪💪💪💪
ጥቁር ብሆንም ቆንጆ ነኘ( But i am #black and #BEAUTIFUL )

ሰው ከሚለው የኃይለጊዮርጊስ ማሞ መፅሐፍ የተቀነጨበ


በፍቅር በመስጠት በመረዳዳት እንኑር ለህልማችን መሳካት ሁሌም እንሩጥ

@jahABP ነኘ😊🙏
Post #1798 738
ይቺን የማርቲን ሉተር ጊንግን ጁኒየር

ንግግር ተጋበዙልኘማ😍😍😍👏👏👏👏👏💪💪💪💪
ጥቁር ብሆንም ቆንጆ ነኘ( But i am #black and #BEAUTIFUL )
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →