AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
#ወዳጄ_ሆይ
ይህ ዓለም የጨዋታ ሜዳ ሳይሆን ጦር ሜዳ መሆኑን አስብ፡፡
መቁሰል አለ መድማት አለ ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ትግል የሌለበት በጥያቄ የማይሞገት ማንም የለም፡፡ ራስወዳድ ስለሆንክ የራስህን ብቻ ታገነዋለህ እንጂ ሁሉም እንዳንተ በጥያቄ የሚኖር ነው፡፡
#በዚህ_ዓለም_ላይ_የሚያኖርህ_አለማወቅህም_ነውና ሁሉን ለማወቅ አትሻ፡፡ ነገ የሚሆንብህን ክፉ ገጠመኘ ብታውቅ መኖርህን በጠላህ ነበር፡፡
ከሰው ወገን የነገን ወዳጅህ ማን መሆኑን በእርግጠኘነት መናገር አትችልም እግዚአብሔር ግን የዘላለም ወዳጅህ ነው፡፡
ሰዎች ብዙ ደክመህላቸው ሊረግሙህ ልታስደስታቸው በጣርህ ቁጥር ሊበሳጩብህ ባደረክላቸው መጠን ላይረኩ ይችላሉ አንተ ግን አምላክህን ለማስደሰት ኑር እግዚአብሔር የሚያውቅ ይደሰትብኃል
#ደግሞም_በፈጠረው_ጌታ_ያልረካ_ሰው_በአንተ_እንዲረካ_መጠበቅ_ስህተት_ነው፡፡
ለሞተለት ጌታ ፍቅር ያልተሸነፈ ምንም ላላደረክለት ላንተ ምላሹ ይህ ቢሆን አይደንቅም፡፡
በዓለም ላይ የመከራ መከራ መደነቅና መፈለግ ነው፡፡ በክፉ አትደነቅ መደነቅ ጉልበት ይጨርሳል ጠላትህን ለሌላ ተንኮል ያነሳሳል #የሆነን_ነገር_አለመቀበል_ሞኘነት_ነው፡፡ የሰውን ደረት እየመቱ ማዘን አያምም የራስን ደረት እየመቱ ማዘን ግን ያማል አንተም በሰው ችግር ፈራጅ አትሁን፡፡
ዛሬ የምትናገረው ዘር ነው ነገ በራስህ ወይ በልጅህ ታጭደዋለህና ለምትናገረው ተጠንቀቅ፡፡
ይላል #ታዴ በስጦታ ያበረከተልኘ መፅሐፍ
አመሰግናለሁ ወንድሜ😊🙏😍
የመፅሐፉን ርዕስ የፈለገ በውስጥ መስመር ያናግረኘ፡፡
@jahABP ነኘ 😊🙏😍
በመልካምነት በመረዳዳት በፍቅር በመታገስ በተስፋ እንኑር እላለሁ፡፡
አስተያየታችሁን አድርሱኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Post #1809
840