TGViewer
Channel ✦ Verified Channel
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

@ethpress

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Subscribers
24.8K
Photos
41.4K
Videos
347
Links
5.8K

Showing posts older than #46288 · Back to latest

Older Posts 7 shown
Post #46278 2.46K
‎‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ሁሉን አቀፍ ምድራዊ ገነት!
‎
‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ’ገበታ ለትውልድ’ ውጥን አካል የሆነው ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’፤ ማህበረሰብን ለማበልጸግና ሀገራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለራዕይ መሪ የአመራር ጥበብና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ምስክር ነው።
‎
‎ ሎጅው በተለያዩ የፍራፍሬ እና የደን ዛፎች በለመለመ 78,000 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ተፈጥሯዊ የ"ሰማያዊ ዓይን" ፍልውሃ መዋኛ፣ ሁለት ግዙፍ ሰው ሰራሽ ሐይቆችና 3.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የእግር ጉዞ (ሀይኪንግ) ምቹ መንገድ አካቷል።

‎የማረፊያ ክፍሎቹንም በተመለከተ፦ የግል መዋኛ ገንዳ ያላቸው ሁለት ፕሬዝዳንታዊ ቪላዎች፣ አስራ ሁለት እርስ በእርስ የተያያዙ የመኝታ ክፍሎች እና አስራ ስድስት ባለ አንድ መኝታ ቤቶችን ይዟል። በተጨማሪም ዘመናዊ የምግብ አዳራሾች፣ የእንግዳ መቀበያ ህንፃ፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የቢሮ ክፍሎች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ እና ሁለት ሄሊኮፕተሮችን በአንድ ጊዜ ማሳረፍ የሚችል ስፍራ (ሄሊፓድ) ያካተቱ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል።
‎
‎ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ከቱሪስት መዳረሻነቱ ባለፈ፣ ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰትን በመሳብ ታላላቅ ጉባዔዎችን ለማስተናገድ ተደማሪ ዐቅም ነው። ‎በመስተንግዶ እና በአገልግሎት ዘርፎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለአካባቢው ኢኮኖሚ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ሲሆን ፕሮጀክቱ በጠንካራ አመራር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መዳረሻን የማቅረብ የገበታ ለትውልድ መርሃ-ግብር ርዕይን ሰንቆ ቀጣይነት ላለው ቀጣናዊ ዕድገት እንደ ወሳኝ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።

#PMOEthiopia #VisitEthiopia #EthiopiaDelivers
Post #46277 2K
ከሉሲ እስከ ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ፤ የአፋር ስጦታ!

‎ዛሬ በአፋር ክልል የ'’ገበታ ለትውልድ’' ፕሮጀክታችን አካል የሆነውንና የሰው ልጅ ታሪክ ከጀመረበት ጥንታዊ ምድር የተገነባውን ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ለመመረቅ ተገኝተናል።
‎
የከባቢው ጸጋ የተገለጠበት ይኽ ስራ የቱሪዝም ልህቀትና የግብርና ዘርፍ መነቃቃትን አዲስ ምዕራፍ በማብሰር፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ይበልጥ ጎልታ እንድትታይ የማድረግ ከፍተኛ ዐቅም አለው!

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Post #46272 2K
ሐዋሳ እና ብስክሌተኞቿ
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በኢትዮጵያ ከተሞች ብስክሌትን አዘውትረው የመጠቀም ባህል ካዳበሩ ነዋሪዎች መካከል የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ይጠቀሳሉ። በከተማዋ የተሰራው የኮሪደር ልማት ሥራ ዘመናዊነትን እንድትጎናጸፍ ፣ እንድትዋብና ምቹ እንድትሆን ያደረጋት ሲሆን፤ ጎዳናዎቿ ብስክሌት የሚጋልቡ አብዮተኞች እንዲበራከቱ አስችሏታል፡፡ በብስክሌት እየተጓዙ ጤናቸውን የሚጠብቁ እየተዝናኑ ነዳጅን የሚቆጥቡ የከተማዋ ነዋሪዎችም እየበዙ መጥተዋል፡፡ እርዎስ? እርስዎ የሚኖሩበት ከተማስ?
  • ❤ 1
Post #46271 1.77K
አነስተኛ ወርቅ አምራቾችን ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የማሸጋገር ሥራ እየተከናወነ ነው
+++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አነስተኛ የወርቅ አምራቾችን ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ባለቤትነት የሚያሸጋግር አሠራር በመዘርጋትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የማሸጋገር ሥራ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ናስር መሀመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በማዕድን ልማት ዘርፉ ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ አነስተኛ አምራቾችን ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ባለቤትነት የሚያሸጋግር ሥርዓት ተዘርግቷል።

አነስተኛ አምራቾችን በአምስት ሄክታር መሬት ላይ በማደራጀት ወደ ሥራ እንዲገቡ በተደረገው ጥረት እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የገለጹት አቶ ናስር፤ ይህ አደረጃጀት የአካባቢው ነዋሪዎች ያላቸውን የቆየ ልምድና እውቀት ከሕጋዊ አሠራር ጋር በማቀናጀት ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል።

አምራቾቹን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ተሻለ የኢንዱስትሪ ደረጃ የማሸጋገር ሥራ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፤ ባለሀብቶች ከአነስተኛ አምራቾች ጋር በጋራ እንዲሠሩ ወይም ከ5 እስከ 50 ሄክታር መሬት ወስደው በኩባንያ ደረጃ እንዲሰማሩ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

ከወርቅ በተጨማሪ እንደ የድንጋይ ከሰል፣ እምነበረድ እና ብረት ያሉ 17 ዓይነት ማዕድናት ለክልሉ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ እንደ ሞተር እንዲያገለግሉ ጥናት እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን
#ጋዜጣ_ፕላስ #አነስተኛ_አምራቾች #ኢንዱስትሪ#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ #ማዕድን #ወርቅ #ኢትዮጵያ
  • ❤ 2
Post #46270 2.08K
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አዲስ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታወቀ
+++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በሀገሪቱ እየታየ ያለውን የነዳጅ እጥረትና ሕገወጥ ንግድ ለመፍታት በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱን የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በነዳጅ ስርቆት ወይም "መቀሸብ" ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ይባክናል።

ችግሩ ከጅቡቲ ጀምሮ እስከ ማደያዎች ድረስ ባለው ሰንሰለት ውስጥ የሚፈጸም መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አንድ የነዳጅ ቦቴ መንገድ ላይ በመቆም ብቻ በርካታ ሊትር ነዳጅ እንደሚሰረቅና በማደያዎችም "አየር በመሸጥ" እስከ 10 በመቶ የሚደርስ ስርቆት እንደሚፈጸም ተናግረዋል።

ይህንን ሕገወጥ ዝውውር ለመግታት መንግሥት የ40/20/40 የነዳጅ ሥርጭት ቀመር አዘጋጅቶ እየተገበረ ይገኛል።

ይህ አዲስ አሠራር የኩባንያዎችን የማደያ ብዛት፣ ነዳጅ የማከማቸት አቅምንና ሕዝቡን በቀጥታ የሚያገለግሉ የዲስፔንሰር ወይም የመቅጃ መሣሪያዎችን ቁጥር መሠረት በማድረግ ፍትሐዊና ቁጥጥር የሚደረግበት የነዳጅ ሥርጭት እንዲኖር ታስቦ የተቀረጸ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም በመንገድ ላይ የሚቀሸበውን ነዳጅ ለመቆጣጠር አላርም የሚያደርግ “ሴንሰር” በቦቴዎች ላይ እየተገጠመ መሆኑን ደስታው (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ መያዙን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በ352 ማደያዎችና በ256 ቦቴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል።

በዮሐንስ መልካሙ
  • ❤ 2
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →