TGViewer
Channel ✦ Verified Channel
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

@ethpress

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Subscribers
24.8K
Photos
41.4K
Videos
347
Links
5.8K

Showing posts older than #46248 · Back to latest

Older Posts 12 shown
Post #46243 2.98K
"ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት አድርገናል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
  • 👍 15
  • ❤ 3
  • 😁 3
Post #46242 2.77K
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Photo
“ወድቆ መቅረት የለም”፤ ከሥልጣን እስከ መቄዶንያ
+++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ሕይወት እንዲህ ናት፤ ከፍታን በቀኟ ከያዘች በግራዋ ዝቅታን ይዛ እንካችሁ ማለት ልመዷ ነው።
ይህ አባባል የቀድሞው ባለስልጣን አሁን በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት የአቶ መላኩ አሰፋ የሕይወት ምስክርነት ሊሰጡበት የሚያስችል ነው።
አቶ መላኩ አሰፋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ሲወጡ ትልቅ ራዕይ አንግበው ነበር የወጡት።
በኢትዮጵያ ማዕድን ሀብት ልማት ኮርፖሬሽን ውስጥ ለ10 ዓመታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። የኢትዮጵያን ሠራተኞች ኮንፌዴሬሽንን በምክትል ፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን ወክለው ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሚኒስትሮች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተደራድረዋል፤ ተወያይተዋል።
የሰው ልጅ ሕይወት ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለምና በኋላ ግን የአቶ መላኩ ሕይወት በዚህ ልትቀጥል አልቻለችም።
አቶ መላኩን ከባድ የአዕምሮ ሕመም ገጠማቸው። ያ ሁሉ ዝና፣ ያ ሁሉ ሥልጣንና እውቀት በሕመሙ ጥላ ሥር ተሸፈነ።
በአንድ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚሟገቱት ግለሰብ፣ ሕመም አሸንፏቸው ጎዳና ላይ ለመውደቅ በቁ።
ከውድቀትም በኋላ ትንሳኤ ከሕመምም በኋላ ፈውስ አለና አቶ መላኩ በሕመሙ ተሸንፈው አልቀሩም። ወደመቄሄዶንያ ገቡ፡፡
በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር ባገኙት ፍቅር፣ እንክብካቤና ሕክምና ዳግም ለመወለድም ታደሉ። አእምሯቸው ተመልሶና ማንነታቸውን መልሰው በማግኘት ዛሬ ለመቄዶንያ ትልቅ ውለታ እየመለሱ ይገኛል።
በአሁኑ ጊዜ አቶ መላኩ በመቄዶንያ ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያና የስክሪፕት ጸሐፊ ናቸው።
በፋና እና በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚተላለፉ የመቄዶንያ የአየር ሰዓቶች ላይ ከ70 በላይ ስክሪፕቶችን አዘጋጅተዋል። በተጨማሪም ዶክመንተሪዎችንና ቃለ መጠይቆችን በብቃት ያከናውናሉ።
አቶ መላኩ መቄዶንያ ከበጎ አድራጎት ማኅበርነት አልፎ ወደ "ቻሪቲ ቪሌጅ" (Charity Village) እንዲያድግ የራሳቸውን ሙያዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ያስረዳሉ።
"መቄዶንያ የኢትዮጵያውያን የበጎነት ጥግ የታየበት፣ የሀገርን ሸክም የተሸከመ ተቋም ነው" ሲሉ መቄዶንያን ይገልጹታል።
"እኔ ድኜ ዛሬ እዚህ ሥራ ላይ ብገኝም፣ ነገ ለማንም ምን እንደሚመጣ አይታወቅም። ስለዚህ ሰውን አትናቁ፣ መቄዶንያን ደግሞ ደግፉ" ሲሉም መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ።
በክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ የተመሰረተው መቄዶንያ እንደአቶ መላኩ አይነት በርካታ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፉ ግለሰቦችን ያስጠለለ ተቋም ነው፡፡
ተቋሙ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልል ከተሞችም ቅርንጫፎችን ከፍቶ ሰውን ከጎዳና እያነሳ እየጦረ ይገኛል፡፡
መቄዶንያ ከመጋቢት 6 ጀምሮ የገበያ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህም ተቋሙ ለጀመረው ባለ 15 ወለል ሆስፒታል እና በክልል ከተማ እየተገነቡ ላሉ ቅርንጫፎች ማስጨረሻ የሚሆን ነው፡፡
መላው ኢትዮጵያውያንና ሌሎችም በገቢ ማሳባሰቢያው በመሳተፍ ተቋሙን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በሄለን ወንድምነው
  • ❤ 9
  • 👏 2
  • 🥰 1
Post #46240 2.51K
በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል። በመሆኑም ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል።
በመሆኑም የነዳጅ አከፋፋዮች፣ማደያዎችና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ፣ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በሃላፊነት ስሜት እንድንጠቀም ለማሳሰብ እወዳለው።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
  • 👍 3
  • 😁 2
Post #46231 3.29K
የዱባይ ገዢ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ግርማዊ ሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱምን አግኝቼ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
‎በሁለቱ ሀገሮቻችን እና ሕዝቦቻችን መካከል ስላለው ጠንካራ የቢዝነስ፣ ትምህርት እና ባህል ትስስር ተነጋግረናል። ከዚህች ጠንካራ፣ ውብ እና ጽኑ ከተማ ጋር ያለን ትስስር በቀጣይ ጉብኝቶችም ይጠናከራል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
‎
  • ❤ 10
  • 👍 3
Post #46230 2.36K
ቦርዱ ባደረገው ማጣራት የፓርቲ አባል በሆኑ የምርጫ አስፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ወሰደ
+++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የምርጫ አስፈጻሚዎች ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ነፃ መሆን ያለባቸው ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባደረገው ማጣራት የፓርቲ አባል ሆነው በተገኙ አስፈጻሚዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዛሬ ማምሻውን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ ቦርዱ ምርጫው ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን በትኩረት እየሠራ ይገኛል። በዚህም መሠረት በተደረገ ማጣራት የፓርቲ አባል መሆናቸው የተረጋገጠባቸው አስፈጻሚዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።
እርምጃ ከተወሰደባቸው ግለሰቦች መካከል ከፓርቲ አባልነት ባለፈ የፓርቲ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ጭምር እንደሚገኙበት ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል።
ቦርዱ በማጣራት ያገኛቸውን እነዚህን ግለሰቦች ከአስፈጻሚነት ያሰናበተ ሲሆን፤ የማጣራት ሥራውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ፓርቲዎች የምርጫውን ሂደት የሚታዘቡላቸውን ወኪሎች እንዲልኩ ጥሪ ተደርጎ ባጅ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ እስካሁን ወኪሎቻቸውን የላኩት ውስን ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸውን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።
ቦርዱ በሂደቱ የሚያጋጥሙ ማንኛውንም ችግሮች ለመፍታት ከቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ያሉ አሠራሮችን እንደሚጠቀም ተናግረዋል።
በልጅዓለም ፍቅሬ
+++++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ጋዜጣ_ፕላስ #ምርጫ_2018 #ምርጫ_ቦርድ #ገለልተኝነት #ኢትዮጵያ #ምርጫ_አስፈጻሚ
  • 👍 4
Post #46225 2.24K
"የጸና ወዳጅነት፣ በመተማመን ላይ የተመሠረተ ትብብር"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በነበረኝ የስራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተገናኝቼ ተወያይተናል።

‎ውይይታችን በኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብርና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።

ለተደረገልኝ አቀባበልና በሀገሮቻችን መካከል የፀና ወዳጅነታችንን የበለጠ ለማጠናከር ለተጋራነው የፀና አቋም ምስጋናዬ የላቀ ነው።
  • ❤ 6
Post #46224 2.56K
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

✅ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
  • ❤ 6
  • 👍 1
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →