TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46886 3.67K
"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉዞ፤ በተግባር የታነጸበት ስራ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
+++++++++++++

ዛሬ በሞጆ ተገኝተን ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት ትልቅ ሚና የሚጫወተውንና በ60 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፍያ የመጀመሪያ ምዕራፍ አስመርቀናል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በዓመት እስከ አንድ ሚሊዮን ባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮች የማስተናገድ አቅም ያላቸው ጣቢያዎችና ዘመናዊ መጋዘኖች ያሉት ሲሆን፣ የደረቅ ብትን ጭነቶችን በሀገር ውስጥ እንድናሽግ ማስቻሉ፣ የውጭ ምንዛሬን ከመቆጠብ ባለፈ ለዜጎቻችን ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

የማዕከሉን የአሰራር ፍጥነት ለማሳደግ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተተከለው የባቡር ላይ ክሬን ከባቡር መስመር የሚደረገውን የኮንቴነር ዝውውር በከፍተኛ ፍጥነት ያከናውናል።

ሙሉ አሰራሩ በዘመናዊ ዲጂታል መሰረተ ልማት የተሳሰረ በመሆኑ፣ ለተገልጋዮች ፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎትን ያሳልጣል። ይህ ማዕከል ከኢትዮ-ጅቡቲ መስመር ባሻገር ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ዩጋንዳን የሚያስተሳስረው የ‘ደሱ’ ኮሪደር አካል ሲሆን፤ ይህም ሀገራችን በዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ደረጃ ላይ ያላትን ስፍራ የሚያሻሽልና የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስራችንን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ትልቅ ድል ነው።

#EthiopiaDelivers
  • ❤ 3
More from @ethpress
  1. Sep 26, 2026የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል +++++++++++++++++ በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ…
  2. Sep 26, 2026"ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር +++++++++ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ…
  3. Sep 24, 2026‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁ…
  4. Sep 24, 2026እንደምን አደራችሁ ? #አዲስ_ዘመን_ጋዜጣ- https://press.et/e-paper
  5. Sep 18, 2026በኮሪደር መሰረተ ልማት እርጅናዋ የተገፈፈ አዲስ አበባ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - በአዲስ አበባ ከተማ ከተከናወኑት የኮሪደር ልማቶች…
  6. Sep 12, 2026ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →