TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46880 3.61K
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም ስምምነት ተፈረመ
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለው ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ተቋሙ በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የሚቋቋም ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት መሆኑን ገልጸዋል።

በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የሚስተዋለውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን የሚቀርፍ መሆኑን ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብና በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።

#ጋዜጣ_ፕላስ #የቤት_መግዣ_ብድር #ብሔራዊ_ባንክ #IFC #የፋይናንስ_ዘርፍ #የቤት_ልማት #ኢትዮጵያ
  • ❤ 6
  • 👍 3
More from @ethpress
  1. Sep 30, 2026photo post
  2. Sep 30, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማማ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰር የቦይን…
  3. Sep 30, 2026በጂኦግራፊ የተሳሰሩ ጎረቤታሞች፤ በውይይት መግባባትንና ወዳጅነትን የሚያጸኑ አጋሮች:: #PMOEthiopia #FDREGoverment #Commun…
  4. Sep 29, 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል።…
  5. Sep 29, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ፦ ኢትዮጵያን በአንድ የተወሰነ ዘመን፣ በአንድ ጊዜያዊ ፈተና ወይም በ…
  6. Sep 29, 2026photo post
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →