TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46680 2.19K
ኢትዮጵያውያን ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበትን ምርጫ አካሂደዋል - ማህሙድ አሊ ዩሱፍ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሰረት እንዲሆን ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህመድ አሊ ገለፁ።

ሊቀመንበሩ ባወጡት መግለጫ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ያላቸውን አድናቆት ገለፀው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያሳየውን ሙያዊ ብቃት እና ቁርጠኝነትም አድንቀዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በታማኝነት፣ ሰላማዊ እና ግልጽነት ባለው የምርጫ ሂደቶችን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑንም በመግለጫቸው ገልጸዋል።

ሊቀመንበሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረት በአብላጫ ድምፅ ላሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በአባል ሀገራት ውስጥ ተአማኒ፣ ሰላማዊ እና ግልጽ በሆነ የምርጫ ሂደት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማጠናከር ያለውን ጽኑ አቋም መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia #AfricanUnion #AU #Election2026
More from @ethpress
  1. Oct 5, 2026አዲስ የመንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል ++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- አዲስ የመንግሥት ምሥረታና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓ…
  2. Oct 4, 2026photo post
  3. Oct 4, 2026"የዘንድሮው የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በስኬት ተጠናቅቋል" - የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ +++++++++++ #ጋዜጣ_…
  4. Oct 4, 2026ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ #ጋዜጣ_ፕላስ #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  5. Oct 3, 2026https://youtu.be/oXi2-SwdwbY
  6. Oct 3, 2026የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ም…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →