TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46667 3.24K
"የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ግንባታ አትችሉም ለሚሉን እንደምንችል የምናሳይበት ፕሮጀክት ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | እየተገነባ ያለው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማሪፊያ ፕሮጀክት አትችሉም ለሚሉን እንደምንችል፣ የአፍሪካን አቅም ለዓለም የምናሳይበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ፕሮጀክቱ ሲታሰብ ጀምሮ በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬ እንደነበርም ጠቅሰዋል።

በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከ8ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ግንባታን በጎበኙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ የቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታ የኢትዮጵያንና የአፍሪካን የማሰብ፣ የማቀድና የመስራት አቅም ለአለም የሚያሳይ ግዙፍ ስራ ነው ብለዋል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም እንደነበሩትና በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚዘገዩት ፕሮጀክቶች ሳይሆን በከፍተኛ ክትትል የሚመራ፤ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የሚጠናቀቅ እንደሆነም ገልጸዋል።

በፕሮጀክቱ ጅማሮ ላይ ብዙዎች አትችሉም፣ ገንዘቡም አይገኝም፣ ስራውን መምራት አይሆንላችሁም፣ ለምን ታስባላችሁ የሚል የተስፋ ማስቆረጥ ምልከታ እንደነበራቸው አስታውሰው፤ እኛ ግን እንችላለን፣ ይገባናል የሚመጥነን ፕሮጀክት ነው ብለን በተግባር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የኤርፖርቱ ግንባታ በትልቅነቱ፣ በሚመደብለት ሃብትና በአጠቃላይ በሚያንቀሳቅሰው ማሽነሪ በአፍሪካ ደረጃ ትልቁ ፕሮጀክት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በግንባታው ሂደት የሚገጥሙ በርካታ ፈተናዎችን በመፍታት ፕሮጀክቱን ማሳካት እንደሚቻል በተግባር እየታየ ይገኛል ብለዋል።

በልማቱ ምክንያት የተነሱ የአካባቢው አርሶ አደሮች የቤት ግንባታና የቢዝነስ ተቋማት መደራጀታቸውንና በፕሮጀክቱ ምክንያት የሚጎዳ አርሶ አደር እንደማይኖርና ሙሉ በሙሉ ህይወታቸው እንደሚሻሻል አረጋግጠዋል።

በፕሮጀክቱ ከ8 ሺህ በላይ ሠራተኞች እንደሚገኙና እስከ 4 ሺህ የሚጠጉ ማሽነሪዎችና መኪናዎች እንደሚንቀሳቀሱ ጠቅሰው፣ ለማሽኖቹና ለመኪናዎች አገልግሎት በቀን ከ650 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ጥቅም ላይ ይውላል ብለዋል።

በብዙ ሀገራት ብሎም በኢትዮጵያ የሥራ ሐሳብና ሀብት ቢኖርም፤ የፕሮጀክት አመራር ችግር ስላለ ፕሮጀክቶች መቼ ተጀምረው መቼ እንደሚጠናቀቁና እንዴት ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው በቂ ግንዛቤ አለመኖሩን ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ በረከት ነው፤ ለልጆቻችንም ትልቅ መሰረት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በተባበረ ክንድ የኢትዮጵያን ድህነት ለመስበር፣ የበለጸገችና ያደገች ኢትዮጵያን በጋራ ለማየት በጋራ እንዲቆምና እንዲተባባር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአማን ረሺድ እና በሀብታሙ በውቀት

#ቢሾፍቱ_ኤርፖርት #ሜጋ_ፕሮጀክት #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #አፍሪካ #BishoftuAirport #AfricanExcellence #Infrastructure #AfricaRising
More from @ethpress
  1. Oct 6, 2026በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ ++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲ…
  2. Oct 6, 2026photo post
  3. Oct 6, 2026የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ +++++++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- የናይጄሪያ ም…
  4. Oct 6, 2026#የመደመር_መንግሥት "በግንባርም፣ በሚዲያም፣ በሰይፍም በሰልፍም ፣ በውሸትም፣ በሀሜትም፣ በተንኮልም፣ በሽረባም፣ ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉ…
  5. Oct 6, 20268ቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፤ ✅ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የ…
  6. Oct 5, 2026ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) +++++++++++ ‎ ዛሬ የመደመር…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →