አዲሱ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከአዲስ አበባ 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ፣ ከባሕር ጠለል በላይ በ1,910 ሜትር ከፍታ ላይ እየተገነባ ይገኛል። በመጨረሻው የማስተር ፕላን አቅሙ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ የተወጠነ ሲሆን፣ ይህም አሁን ካለው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የማስተናገድ አቅም ጋር ሲነጻጸር በ4.4 እጥፍ ብልጫ ይኖረዋል።
ይህ ታሪካዊ ፕሮጀክት፣ ሀገራችንን ከዓለም ቀዳሚ የአቪዬሽን ማዕከላት ተርታ ለማሰለፍ፣ በደረሰበት ሁሉ ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርጎ የሚያሳይና የአኅጉራችን ኩራት በሆነው በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት በአፍሪካና ከዚያም ባሻገር ያለውን ትስስር ለማጠናከር ሌሊትና ቀን በከፍተኛ ጥረት እየተገነባ ይገኛል!
#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
Post #46658
3.48K







- 👏 4