TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46647 3.52K
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ‼️

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባችንን ተከትሎ፣ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶችን የሚያሳይ የግንባታ ሳይት ጎብኝተናል።

በዚህ ሳይት ሦስት የላቁ የግንባታ ዘዴዎች በጥምረት ጥቅም ላይ ውለዋል፤ የ3ዲ ህትመት፣ የቅድመ-ዝግጅት ቀላል የአረብ ብረት ግንባታና የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች ናቸው።

እያንዳንዳቸው ግንባታዎች ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ ስንጠቀም ጥራታቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ከወራትና ከዓመታት ይልቅ በጥቂት ቀናትና ሳምንታት ውስጥ ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የታየበት ህያው ምስክር ናቸው።

‎ይህ አይነቱ የላቀ ፈጠራ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በቀላሉ ሊተገበር፣ ሊደገምና ሊስፋፋ የሚችል በመሆኑ የሀገራችንን የቤት ልማት ፕሮግራም አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ የመቀየር ኃይል አለው።

ቴክኖሎጂን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር አጣምረናል፤ መሰል በተግባር የተገለጡ ስራዎቻችን ደግሞ ለሀገር የሚገባውን ፈጣን ዕድገት እውን ለማድረግ በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ በቁርጠኝነት እየተጓዝን መሆናችንን በተግባር አሳይቷል።

#ኢትዮጵያ #ታዳሽኃይል Office of the Prime Minister-Ethiopia #technology #TechHouse
  • ❤ 12
More from @ethpress
  1. Oct 6, 2026በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ ++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲ…
  2. Oct 6, 2026photo post
  3. Oct 6, 2026የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ +++++++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- የናይጄሪያ ም…
  4. Oct 6, 2026#የመደመር_መንግሥት "በግንባርም፣ በሚዲያም፣ በሰይፍም በሰልፍም ፣ በውሸትም፣ በሀሜትም፣ በተንኮልም፣ በሽረባም፣ ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉ…
  5. Oct 6, 20268ቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፤ ✅ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የ…
  6. Oct 5, 2026ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) +++++++++++ ‎ ዛሬ የመደመር…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →