የፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት ዓመት በጀት ከሁለት ትሪሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ተወሰነ
+++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ| የፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ሁለት ነጥብ ሦስት ትሪሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሰለፈ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግስት የ2019 በጀት ዓመት የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግስታት ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የሚውል 2,339,268,126,738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሶስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ረቂቅ በጀቱ የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና አላማዎች፣ በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የመንግስትን የፋይናንስ አቅምና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮና ሃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም ተዘጋጅቶ መቅረቡ ተገልጿል።
መስከረም ሰይፉ
++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus
Post #46646
2.93K

- ❤ 3