TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46642 2.8K
56ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

✍️ የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ካሉበት ተግዳሮቶች እየተላቀቀና የኢኮኖሚው መሰረቶችም እየተጠናከሩ መጥተዋል፡፡

ማዕቀፉ በኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲያስችልና በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ታሳቢዎች ላይ በመመስረት የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት ዝግጅት መነሻ ሆኖ እንዲያገለግል ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

✍️ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት ረቂቅ አዋጅ

የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2019 የፌዴራል መንግስት በጀት የአስር አመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነው የ2019-2021 የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችንና የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና የፊሲካል ማዕቀፍን መሰረት በማድረግ፣ የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ ፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና አላማዎች እንዲሁም በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የመንግስትን የፋይናንስ አቅምና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮና ሃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

በዚሁ መሰረትም ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግስታት ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚውል 2,339,268,126,738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሶስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2019 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
  • ❤ 5
More from @ethpress
  1. Oct 6, 2026በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ ++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲ…
  2. Oct 6, 2026photo post
  3. Oct 6, 2026የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ +++++++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- የናይጄሪያ ም…
  4. Oct 6, 2026#የመደመር_መንግሥት "በግንባርም፣ በሚዲያም፣ በሰይፍም በሰልፍም ፣ በውሸትም፣ በሀሜትም፣ በተንኮልም፣ በሽረባም፣ ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉ…
  5. Oct 6, 20268ቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፤ ✅ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የ…
  6. Oct 5, 2026ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) +++++++++++ ‎ ዛሬ የመደመር…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →