ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ ትናንት የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለብዙኃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ በስኬት ተጠናቅቋል ። በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅት እና የድኅረ ምርጫ ሥራዎች በአግባቡ ተከናውነዋል።
የመራጮች ምዝገባ፣ የእጩዎች ምዝገባ፣ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የመመዝገብ እንዲሁም ለሌሎችም አካላት ፈቃድ የመስጠት የቅድመ ምርጫ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ የተጠናቀቁ ሲሆን፤ በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሒደት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አስረድተዋል።
እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ማለዳ 12:00 ክፍት ተደርገው ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል። የሲቪክ ማኅበራትም በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ታዝበዋል። የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) ታዛቢዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ ሲታዘቡ ውለዋል።
በብዙ አካባቢዎች የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ ከተጠናቀቀበት ሰዓት ጀምሮ ድምጾች የተቆጠሩ ሲሆን፤ የድምጽ አሰጣጡ ዘግይቶ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ቆጠራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቆጠራው እንደተጠናቀቀ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል። ከድምጽ አሰጣጥና ከቆጠራ ጋር በተገናኘ የሚመጡ ጥቆማዎችን በማጣራት ቦርዱ በሕግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድም ገልጸዋል።
በአብዱረዛቅ መሐመድ
#Ethiopianelection2026 #GeneralElection #EthiopiaVotes #NEBE #AfricanUnion #IGAD
Post #46626
3.9K

- ❤ 6