TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46591 2.98K
የማዳበሪያ ፋብሪካው የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንዱስትሪ እድገትና በኢኮኖሚ ራስ የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቨስትመንት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንዱስትሪ እድገትና በኢኮኖሚ ራስ የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቨስትመንት መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሰታወቁት፤ ባለፈው አመት ነሐሴ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመሆን በአመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ለማቋቋም ትልቅ የባለድርሻ ስምምነት አድርገን ነበር።

በያዝነው አመት ጥቅምት ወር ደግሞ የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ ጀምረናል። ይኽ ሥራ ከመሠረተ ልማት ግንባታም በላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንደስትሪ እድገት እና በኢኮኖሚ ራስ የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቬስትመንት መሆኑን ገልጸዋል።

የማዳበሪያ ፋብሪካው በሚጠናቀቅበት ወቅት የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ያጎለብታል፣ ከውጭ በሚገባ ማዳበሪያ ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶአደሮቻችንን ይደግፋል።

ለኢንቨስትመንትና የሥራ ዕድል ፈጠራም አዳዲስ እድሎችን ይከፍታል።

ዛሬ ማለዳ ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በጎዴ ተገኝቼ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ለመገምገም የፕሮጀክት ስፍራውን ጎብኝቻለሁ። በመላው የፕሮጀክቱ ስፍራ የሚታየው የሥራ ሂደቱ ፍጥነት አበረታች ነው።

ይኽን ግዙፍ እና እጅግ ጠቃሚ ሀገራዊ ፕሮጀክት ለመፈፀም ያለውን ቁርጠኝነት እና ትብብር በሚያንፀባርቅ ሁኔታ በተለያዩ የፕሮጀክቱ ክፍሎች ያሉት ግንባታዎች በእቅዳችን መሠረት እየተጓዙ ይገኛሉም ብለዋል።

#ግብዓትአቅርቦት #PMOEthiopia #DigitalTransformation #FinancialFreedom #fertilizerindustry
  • ❤ 3
More from @ethpress
  1. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  2. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  3. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
  4. Oct 6, 2026በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ ++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲ…
  5. Oct 6, 2026photo post
  6. Oct 6, 2026የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ +++++++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- የናይጄሪያ ም…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →