TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46578 2.89K
ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች በ“ሪሞት ጆብስ” ወይም ፍሪላንሲንግ ሥራ ተሰማርተዋል
+++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በኢትዮጵያ ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች በ“ሪሞት ጆብስ” ወይም ፍሪላንሲንግ ሥራ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ አንድ ባለሙያ ባለበት ቦታ ሆኖ ስማርት ስልክ ወይም ላፕቶፕ በመጠቀም በተለያዩ የዓለም ሀገራት ተቀጥሮ መሥራት የሚያስችለው ሥርዓት ነው።

በዘርፉ ከ80 ሽህ በላይ ወጣቶች ቴክኖሎጅን በመጠቀም እዚሁ ሁነው ሌላ ዓለም ላይ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ ገቢያቸውም እያደገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በዘርፉ በሥራ ፈጠራና ክህሎት ልማት የሰው ኃይል ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ዜጎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የዲጂታል ግንዛቤን ማሳደግና የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

የሪሞት ጆብስ (ፍሪላንስ) ስራ የዲጂታል ክህሎትና እውቀት ያለው ሰው የሚፈልግ በመሆኑ ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለመፍጠር ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የሥራ ፈጠራ ሐሳቦች እንዲስፋፉ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በእየሩስ ተስፋዬ

#የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ጋዜጣፕላስ #ዲጂታል_ኢትዮጵያ #ሪሞት_ጆብስ #ፍሪላንሲንግ #የሥራ_ፈጠራ
#ቴክኖሎጂ *#ኢትዮጵያ
  • ❤ 3
  • 🤬 2
More from @ethpress
  1. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  2. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  3. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
  4. Oct 6, 2026በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ ++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲ…
  5. Oct 6, 2026photo post
  6. Oct 6, 2026የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ +++++++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- የናይጄሪያ ም…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →