ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ-በዛሬው ዕለት ለሃገር ባለውለታ ለሆኑና በጥበብ ሞያቸው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዖ የመታሰቢያና የክብር ሃውልት በአዲስ አበባ በተለያዩ አከባቢዎች ቆሞላቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ሀገር ለጠቢባን የሕያው ሥራዎቻቸው ምስክር ሐውልት ታቆማለች። ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች ብለዋል።
ዛሬ በአርበኞች ቀን በተለያዩ መስኮች የጀግንነት ሚና የተወጡ አርበኞቻችንን በማስታወስ እየዘከርናቸው ነው ያሉት ከንቲባዋ የሀገር ባለውለታ ለሆኑና በጥበብ ሞያቸው ለኢትዮጵያ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸዋልም ብለዋል።
ሀገር በልማት ስራዎች፣ ድንበርን በመከላከል፣ በሰንደቅ ዓላማና በሕግ ብቻ አትገነባም። ሀገር የምትገነባው በሕዝብ የጋራ ትውስታ፣ በጋራ ስሜትና በታላላቅ የጥበብ ውጤቶችም ጭምር ነው። ይህ እውነት ዛሬ በቆሙት የሀገር ባለውለታ ታላላቅ ጠቢባን ሐውልቶች በአዲስ አበባ እውን አድርገናል ሲሉም ገልጸዋል።
ከተማ አስተዳደራችን በኮሪደር ልማትና በታላላቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ፣ ጥበብን ማዕከል አድርጓል ብለዋል።
ዛሬ ሃውልት የቆመላቸው ለሃገራቸው ሰላም፣ ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ፣ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ለወንድማማችነትና እህትማማችነት፣ ለፍትሃዊነት፣ ለነፃነትና እኩልነት ላቀነቀኑት አንጋፋዎቹ የሀገር ባለውለታዎች ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን፣ የክብር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ፣ ማሕሙድ አሕመድ፣ ዓሊ ቢራ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔርና ሐጫሉ ሑንዴሣ ናቸው።
ከእነዚህ በተጨማሪም ልናከብራቸው የሚገባን የሀገር ባለውለታዎች የሆኑ የጥበብ ሰዎች መኖራቸው ስለሚታወቅ ይህ ስራ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም። ጥበብ ሀገርን ትስራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታስታውሳለች ብለዋል።
እነዚህ የመታሰቢያና የክብር ሃውልቶች በጥበብ ሞያቸው ለሀገር ያበረከቷቸው አስተዋጽኦ የሚዘከርበት ነው ተብሏል።
#ሀጫሉሁንዴሳ #የጥበብኮከብ #አዲስአበባ #አፍሪካፓርክ #የኢትዮጵያአሻራ #EthiopianArt #MusicLegend
Post #46566
2.4K
- ❤ 3