TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46446 2.63K
የባሕር በር ጉዳይ የሁሉም ፓርቲዎች የጋራ አቋም ሊሆን ይገባል
+++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የባሕር በር ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነት የማያሳዩበት ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አዲስ መሀመድ ገለጹ።

ሥራ አስፈጻሚዋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ወደብና የባሕር በር ያላትን ሀገር የመረከብ ፍላጎት በሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋምና የጋራ አጀንዳ ነው፡፡

በአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ፓርቲዎች በጉዳዩ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ጠቁመው፤ የባሕር በር ጉዳይ በፖለቲካ አቋም ምክንያት ልዩነት የማይታይበትና የሁሉም ፓርቲዎች የጋራ አቋም ሊሆን የሚገባው ቀዳሚ ሀገራዊ ጥቅም ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በሯን ያጣችበት የታሪክ አጋጣሚ በሕግ ሚዛን ሊታይ እንደሚገባ የገለጹት ወይዘሮ አዲስ፤ የባሕር በሮች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶችና ስምምነቶች ሊመረመሩ የሚችሉበት አግባብ መኖሩን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን ታሪካዊ መነሻ፣ ማስረጃና የባሕር በሩን ስትጠቀምበት የነበረበትን አግባብ በአግባቡ ካቀረበች፣ በማንኛውም ዓለም አቀፍ የክርክር መድረክ የማሸነፍ ዕድሏ ሰፊ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

መንግሥት አሁን የጀመራቸውን የዲፕሎማሲ አማራጮች አጠናክሮ እንዲቀጥልና በታሪካዊ መብቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራም መክረዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች አርስ በእርስ ጣት ከመቀሳሰር ወጥተው ሀገራዊ ጥቅሞች ዙሪያ መመካከራቸው ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታውም ሆነ ለብሔራዊ መግባባት ትልቅ መሠረት እንደሚጥል አስረድተዋል፡፡

በሳሙኤል ወንደሰን
  • ❤ 9
More from @ethpress
  1. Oct 11, 2026የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ…
  2. Oct 10, 2026በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው የማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ +++++++++++++++ #ጋዜጣ ፕላስ-በኢትዮጵያ…
  3. Oct 8, 2026የመደመር መንግስት አዲሱ ካቢኔ #የመደመር_መንግሥት #PMOEthiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
  4. Oct 8, 2026አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣…
  5. Oct 8, 2026ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የሕዝብ ተወካዮ…
  6. Oct 6, 2026በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ ++++++++++++++ #ጋዜት_ፕላስ- በትግራይ ክልል ሲ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →